Tuesday, December 24, 2013

የጥራት እና ደረጃ መዳቢ ባለስልጣን መ/ቤት እና ሕ.ወ.ሓ.ት (ልዩ ትንታኔ)

ነጻነት ይበልጣል (ከጀርመን)

ዛሬ ላስነብባችሁ ያሰብኩት  ቀደም ሲል የጥራት እና ደረጃዎች መዳቢ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተብሎ ይጠራ ስለነበረው  አሁን ለአራት ተከፋፍሎ እንዲጠፋ ስለተደረገ ተቋም ነው፡፡ መስሪያቤቱ ምርት እና አገልግሎችን  በመቆጣጠር የሸማቹን ደህንነት እና ጤንነነት ማስጠበቅ የገቢና ወጪ ምርቶችን  ጥራት በመከታተል ጉልህ ድርሻ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡ መስሪያቤቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት ይመሩ የነበሩት አቶ መሳይ ግርማ ሲባሉ በውስጡ የፍተሻ እና ካሊብሬሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የሰርተፊኬሽ አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የደረጃዎች ዝግጅት ዳይሬክትሬት፣ የስልጠናአገልግሎት  ዳይሬክትሬት እና የፋይናንስ ዳይሬክትሬት እና ሌሎች የአገልግጎች ዘርፎች ነበሩት፡፡አቶ መሳይ መስሪያቤቱን 16 ዓመት በላይ አስተዳድረዋል፡፡ ድንገት ባልተጠበቀ ሰዓት ከአቶ መሳይ እውቅና ውጭ 3 ሰዎች  አቶ ተክኤ ብርሀኔ ከመቀሌ፣አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ከጅማ እና አቶ ዳንኤል ዘነበ ከሀረርጌ ተመልምለው  ወደ መስሪያቤቱ ተመደቡ፡፡
ሰዎች ሳይፈለጉ መመደባቸው ብቻ ሳይሆን በወቅቱ እንዲከፈላቸው የተፃፈላቸው የደመወዝ መጠንም በመስሪያቤቱ የደመወዝ ስኬል የሌለ፤ ካላቸው የትምህርት እና የስራ ልምድ ጋር ምንም አይነት ዝምድና ስለሌለው አቶ መሳይ መክፈል አልችልም በማለት አንገራገሩ፡፡ እነሱ መች የዋዛ ቢሆኑ እና እስከ ጠቅላይ /ቤት የተዘረጋ ሰንሰለት ስለነበራቸው በስልክ ተደውሎላቸው ሳይወዱ በግድ መክፈል ጀመሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች 2002 . ለሚካሄደው  ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ ከየክልሉ ተፈልገው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀዋርያ ሁነው ወደ ፌዴራል መንግስት የመጡ ናቸው፡፡ተክኤ በስፓርት ፣ደቻሳ በሂሳብ እና ዳንኤል በማኔጅሜንት ተመርቀዋል፡፡ ሲመጡ የሚያርፉበት የኪራይቤቶች የሚያስተዳድረው ሰፋፊ ግቢ የተዘጋጀላቸው ሲሆን ዳንኤል ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ቤት አጠገብ፤ተክኤ እና ደቻሳ ደግሞ 22 አካባቢ ባለ ሰፋፊ ግቢ እንዲኖሩ ተመቻችቶላቸዋል፡፡
ዋናው  የቅርብ ጊዜ አላማቸውም 2002 ለሚደረገው ምርጫ የመንግስት ሰራተኛውን ከኢህአዴግ ጎን ማሰለፍ እና ቀጣይ አመራሮችን ማዘጋጀት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ባሉበት ቀበሌ በምርጫ ጣቢያ ሀላፊነት ተመድበው ይሰራሉ፡፡በተጨማሪም መንግስት በቢ..አር.(business process re engineering) ብሎ ወደፊት ሊዘረጋ ላቀደው የሰራተኞች ማፈኛ መንገድ የራሱን  ታማኝ  የስለላ ሰዎች ወደ መሲሪያቤቱ ያስገባል፡፡ የአዲሶቹን ተመዳቢዎች አመጣጥ ተከተሎ በመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የፍረሃት  ድባብ ተፈጠረ፡፡እነሱ ሰራተኞችን ወደሚጭነው ሰርቪስ ሲገቡ አንድም ሰው ትንፍሽ አይልም፡፡የአውቶቡሱ ሰው ሁሉ በጸጥታ ይዋጣል፡፡ጆሮ ጆሮ እያሉ ያንሾካሽካሉ፡፡ በእረፍት ሰሀት እነሱ በተቀመጡበት አካባቢ አብሮ ተቀምጦ ሻይ ቡና የሚል የለም፡፡ሲመደቡ የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች ተብለው ሲሆን ከመስሪያቤቱ እውቅና ውጭ ከነአቶበረከት ሰምኦን ጋር በየሳምንቱ ስብሰባ እና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋሉ፡፡ከሳይንስና ቶክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር ከፈለጉ በአካል መኪና አዝዘው ካልፈለጉ በስልክ በቀጥታ መገናኘት ይችላሉ፡፡
አቶ መሳይ እና ሌሎች የመስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የማያውቁት መረጃ ከነሱ ይገኛል፡፡በዚህ የአንድ አመት ቆያታቸው በመስሪቤቱ ደጋፊዎችን ማፍራት አልቻሉም፡፡
2003. የቢ..አር ጥናት ሲጀመር አዲስ የመጡት ካድሬዎች  የጥናት ቡድን መሪ እየተባሉ ተመደቡ፡፡ ..አር ለመስራት ቀርቶ ስለመስሪቤቱ አሰራር በቂ እውቀት የሌላቸው ሰዎች መስሪያቤቱን አፍርሶ እንደ አዲስ የማደራጀት ስራ በእነዚህ ሰዎች ስር ወደቀ፡፡በዚህም ተቀራራቢ ስራዎችን በጋራ ማደራጀት በሚል ሰበብ ከብሄራዊ የጨረር መከላከያ አንዱን መምሪያ በማፍረስ፤የክሊነር ፐሮደክሽን መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ፤የሳይንስ መሳሪያዎች መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ አፈራርሰው አነዚህን መስሪያቤቶች ከደረጃ መዳቢ ባለስልጣን መስሪያቤት ጋር በማዋሀድ አራት የተለያዩ መስሪያቤቶችን ለመፍጠር ጥናቱ ተጀመረ፡፡ አዲስ የተጠኑት መስሪያቤቶች
1.Meterology institute,
2.Accreditation biro,
3 .Standards agency
4. Conformity assessment enterprise ይባላሉ፡፡
እነዚህ መስሪያቤቶች በተጠኑበት ወቅት ለጥናት ቡድኑ በየሳምንቱ በጣም ውድ በሆኑ ሆቴሎች የእራት ግብዣ  እየተዘጋጀ 6 ወር ያክል ተደከመበት፡፡ወደ መጨረሻው ምእራፍ ሲቃረብ  የጥናት ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ናዝሬት ውስጥ 10 ቀን በላይ ሆቴል ውስጥ ተቀምጠው እንዲሰሩ ተደረገ፡፡በመጨረሻም የጥናቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ  በአቶ ጁነዲን ሳዶ አማካነት አርባምንጭ ለሶስት ቀናት ድል ያለ ግብዣ ተደረገ፡፡ከአርባምንጭ መልስ ሁሉም በሳይንስ እና ቴክኔሎጂ / ስር የሚገኙ ሰራተኛ  ለገሀር በሚገኘው የመንገድ እና  ትራንስፖርት መሰብሰቢያ አዳራሽ ጠቅላላ ስብሰባ ተካሄደ፡፡በስብሰባው የየጥንት ቡድኑ ሀላፊዎች የጥናታቸውን ውጤት ይፋ አደረጉ፡፡የሀገራችን ችግሮች ተዳሰሱ፡፡ለችግሮች መፍትሄ ይሆናሉ የተባሉ አማራጮች ከየአቅጣጫው ጎረፉ፡፡
አብዛኞች ወጣቶች ተስፋ ያደረጉትን በየመስሪያቤቱ ያለውን ብልሹ አሰራር እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡በዚህ ውይይት ከተነሱት ውስጥ እስካሁን የማሰታውሳቸው አቶ ገብረጊዳን ገብረመስቀል በቅጽል ስሙ(GG) “በየመስሪያቤቱ ያለውን የተማረ የሰው ሀይል  እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገብተው እንዲሰሩ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ለምሳሌ እንደ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ አይነት ሰዎች ነበሩዋት ሌሎችም እንዲህ አይነቶች ይኖራሉ ብሎ ተናገረ፡፡በእረፍት የንግድ ሚኒስትሩ የአቶ ታደሰ ሐይሌ ባለቤት / አልማዝ ካህሳይ ይህን የተናገረውን ልጅ ጠራቸው እና ስሙን ጠይቃአንተማ የእኛው ነህ እየውልህ / ቅጣው በመንግስታችን ላይ ሊሰራ አቅዶት የነበረውን ስለማታውቅ ነው እንዲህ ያልከው፡፡በቶሎ ቀጨው እንጂ ቢቆይ በጣም አደገኛ ነበር፡፡እንዲህ አይነቱን ሰው ስሙን መጥራት የለብህምአለችው፡፡
ይቅርታ / አልማዝ እኔ እሱን አላውቅም ነበር ሲል መለሰላት፡፡ሌላው ከጠቅላይ / /ቤት የመጣ  አቶ ጸጋዬ የሚባል አንድ ተናጋሪ በንግግራቸው መሀል ጣል ያደረጉዋት ቀልድ መሰል መልክት ሁሌም ትከነክነኛለች፡፡አቶ ጸጋዬአማርኛ እጅዋን አገኘች በግል ትምህርት ቤት ውስጥ አማርኛ መናገር እና ድንጋይ መወርወር ያስቀጣል ተብሎ በጉልህ ተጽፎ አንድ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አንብቤያለሁብለው አረፉ፡፡ ሌላው ጠያቂ አብዲ ዱጋ ይባላል፡፡አብዲ ጥያቄውን ያቀረበው ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ነው፡፡ጥያቄውኦሮሚያ ክልል ውስጥ አየተካሄደ ያለው የአበባ እርሻ ልማት የአካባቢውን አፈር እና ውሃ እየበከለው ነው፡፡በዚህም የተነሳ እንስሳት ይሞታሉ ሰዎች ይታመማሉ፡፡የሰራተኞችም ህይወት አደጋ  ውስጥ ነው  የሚከፈላቸውም ገንዘብ እዚህ ግባ የሚባል አደለም፡፡እንዲያውም  ባለ ሀብቶች ከሌሎች ሀገሮች ሲባረሩ ነው ወደዚህ ሀገር የመጡት ይባላል እና ይህን እንዴት ያዩታል? ሲል ጠየቀ፡፡አብዲን የገጠመው ከፍተኛ ውግዘት ነው፡፡ለውግዘቱ መነሻም በወቅቱ የአበባ እርሻ ልማት ሲጀመር አቶ ጁነዲን የኦሮሚያ ርእሰ መስተዳድር ስለነበሩ እሳቸውን እንደተቃወመ ተቆጠረ፡፡አብዲም ያጠናው ባዮሎጂ ስለነበር ሙያዊ ትንታኔ መስጠቱን ቀጠለ፡፡ክርክሩ እየከረረ ሲሄድ ጓደኞቹ ዝም እንዲል አደረጉት፡፡ስልጠናው 5 ቀናት በፍረሃት እንደተዋጠ ተጠናቀቀ፡፡ከዚህ ሰብሰባ መልስ በቀጥታ ሁሉም መስሪያቤት ወደ ሰው ኃይል ምደባ እንዲገባ መመሪያ ተላላፈ፡፡

ስብሰባው አርብ ተጠናቆ ሰኞ ጠዋት አቶ መሳይ ከመስሪያቤቱ በፍቃዳቸው እንዲለቁ  ትእዛዝ እንደተሰጣቸው  ለሚቀርቡዋቸው ሰዎች  ሲናገሩ የኮሚኒኬሽን ሰራተኞቹ እነ ተክኤ ደግሞ  ምደባውን እንዳያስተጉዋጉል በማሰብ አስቀድሞ መባረሩን በየቢሮው እየዞሩ ያውጃሉ፡ይህን ተከትሎ መስሪያቤቱ ሰው የሞተ ያክል በኡኡታ በልቅሶ ታመሰ፡፡አብዛኖች መልካም ተግባሩን ለሰራተኛ አዛኝነቱን እያሰቡ አባታቸውን በሞት የተነጠቁ ያክል ከልብ አዘኑ፡፡በዚሁ እለት የንግድ ሚኒስትሩ የአቶ ታደሰ ሀይሌ ባለቤት / አልማዝ ካህሣዬ መስሪያቤቱን እንዲያስተዳድሩ ተሾሙ ፡፡የተለያዬ ዳይሬክተሮችን ሹመት ሰጡ፡፡በዚህ ወቅት ቀደም ሲል ወያኔን እንደሚቃወሙ የሚታወቁት እና ከአቶ መሳይ ጋር ቀረቤታ አላቸው የተባሉ ነባር ዳይሬክተሮች ተነስተው በምትካቸው የኢህአዲግ አባላትን መመደብ ተጀመረ፡፡ ምደባውም የሚካሄደው እያንዳንዱ ሰራተኛ እየተገመገመባለው ችሎታ ነው ይባል እንጅ ነገር ግን አስገራሚው እና ያን ያክል የተደከመበት ጥናት የግምገማውን 75% የሚይዘው  ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው አመለካካት የሚባል ነገር ነው፡፡ሰራተኞች በወቅቱ ያነሱት የነበረው ጥያቄ አመለካከት በምን ሊለካ ይችላል የእኔን አመለካካት ምን እንደሆነ ማን ያውቀዋል የሚል ነበር፡፡
ግምገማውን የሚሞሉት ቀደም ብየ የጠቀስኳቸው እነ ተክኤ፣ደቻሳ እና ዳናኤል ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች እንደመሰላቸው የግምገማ ነጥቡን መስጠታቸው ሳያንስ ምደባውን በዋናነት የሚመሩት እነሱ ናቸው፡፡ወደ ደረጃ መዳቢ መስሪያቤት የመጡትን የሌላ አዳዲስ  መስሪያቤት ሰራተኞች መልካቸውን ሳይቀር የማያውቁዋቸውን ሰዎች ግምገማ በድፍረት ይሞሉ ነበር፡፡በመሀል በተቃዋሚነት ያልተፈረጁትን እና አባል መሆን የሚፈልጉ ካሉ በምደባ እና በእድገት አያባበሉ ወደ ድርጅቱ የማግባባት ስራ ተከናወነ፡እኔ ስራየን እንጂ የፓርቲ አባል መሆን ፍላጎት የለኝም ያሉት ደግሞ ቀደም ሲል በተለያዩ የውጭ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ ስልጠናዎችን ተከታትለው ስራቸውን በብቃት ሲወጡ የነበሩ በርካታ ባለሙያዎች አብዮታዊ ዲሞክራሲን ባለመቀበላቸው ብቻ  ዘራቸው እየታየ ከስራቸው ከተባረሩት መካከል ከዚህ  በታች የተዘረዘሩት ለማሳያ ያክል የቀረቡ ሲሆኑ አንድም የትግራይ ብሄር  ተወላጅ አለመባረሩን አንባቢያን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ሌላው እና አስገራሚው ነገር በወቅቱ  የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን እያገለለ እየተካሄደ ያለው ምደባ ያሳሰባቸው የኢህዴድ አባላት ጥያቄያቸውን ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ቢያቀርቡም / አላማዝ ካህሳይ እያንዳንዱን ኦሮሞ እቢሮአቸው ጠርተው አርፈው እንዲቀመጡ አለዚያ እንደሚባረሩ በዛቻ ገልጸውላቸዋል፡፡በወቅቱም ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰማው አቶ ሙሉጌታ መኮነን ያለስራ ለአንድ ዓመት ደመወዝ ብቻ እየተከፈለው ሊሰራ በማይችል ዘርፍ የቡድን መሪ ሁኖ ሲመደብ በስሩ ግን ምንም ሰው አልነበረም፡፡
.
           ስም
    የነበራቸው ሀላፊነት
ብሄር
1
አቶ መሳይ ግርማ
የጥራት እና ደረጃ /ቤት ዋና ዳይሬክተር
ኦሮሞ
2
አቶ ጋሻው ወርቅነህ
የጥራት እና ደረጃ /ቤት ምክትል ዳይሬክተር
አማራ
3
አቶ ተፈራ ማሞ
የኤሌክትሪክል ላብራቶር  ሃላፊ
ኦሮሞ
4
አቶ ሀይሉ
የመሳሪያ ጥገኛ አገልግሎት ሃላፊ
ኦሮሞ
5
አቶ ደሬሳ ፉፋ
የሰርተፊኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር
ኦሮሞ
6
አቶ መስፍን
የስልጠና አገልግሎት ዳይሬክተር
አማራ
7
አቶ አዱኛው መስፍን
የጥራት ማኔጅሜንት አሰልጣኝ
አማራ
8
አቶ እንዳ
የኢንፎርሜሽን አገልግሎት ሀላፊ
አማራ
9
አቶ አመሃ በቀለ
የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ
አማራ
10
አቶ ሂርጳ
የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ
ኦሮሞ
11
አቶ መረሳ
የሰርትፊኬሽን ኤክስፐርት
ኦሮሞ
12
አቶ ቴወድሮስ ዘካሪያስ
የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት
አማራ
13
አቶ  ልኡል
የባህርዳር ቅርንጫፍ  ሀላፊ
አማራ
14
የሰርትፊኬሽን ሲስተም ኦዲተር የነበሩት
ኦሮሞ
15
የድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት
አማራ
16
የናዝሬት ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት
ኦሮሞ
17
የሀዋሳ  ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት
ደቡብ
ታማኝ የህወአት አባላት  በባትሪ  ከሌላ ቦታ ተፈልገው ያለ ልምድ  እና ችሌታቸው  በከፍተኛ አመራርነት ሲመደቡ የተለሳለሰ አቋም ያላቸውን እና የአባልነት ጥያቄ ሲቀርብላቸው ጥያቄውን የተቀበሉ ነባር የመስሪያቤቱ ሰራተኞች የፍርፍሪው  ተቋዳሽ ሁነዋል፡፡በዚህ ምደባ እስከቡድን መሪ ያለው ሀላፊነት ያለ ፓርቲ አባልነት ወይም ያለ ትግራይ ተወላጅነት በምንም መልኩ ለተራው ሰራተኛ አይሰጥም፡፡
.
 ስም
  ቀደም የነበራቸው ሀላፊነት
አሁን የተሰጣቸው ሀላፊነት
ብሄር
1
/ አልማዝ ካህሳየ
የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክተር
የደረዳዎች ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
2
አቶ ወንዶሰን ፍስሃ
የካሊብሬሽን አገልግሎት ሀላፊ
 የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
3
አቶ አርአያ
መከላከያ ኢንጅነሪንግ
የአክረዲቴሽን /ቤት ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
4
አቶ ጋሻው ተስፋዬ
የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
አቶ ገብሬ
ኝግድ እና ኢንዱስትሪ ኤክስፐርት
በደረጃዎች ኢጀንሲ ዳይሬክተር
ትግሬ
6
አቶ ብርሀኑ ተካ ረዳ
የፋይንነስ አስተዳደር ዳይሬክተር
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፋይናንስ ዳይሬክተር
ጉራጌ
7
/ ገነት /መድህን
የፍተሻ እና ካሊብሬሽን  አገልግሎት ዳይሬክተር
የአክረዲቴሽን /ቤት ዳይሬክተር
ትግሬ
8
/ ብርሀን ብሂል
የአዋሳ ቅርንጫፍ /ቤት ጸሀፊ
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሰው ሀብት እስተዳደር ሀላፊ
ትግሬ
9
አቶ ብርሀኑ ተካ
የሰርቪስ ሹፌር
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ
ትግሬ
10
አቶ ተክኤ ብርሀኔ
የኮሙኒክሽን ሰራተኛ
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር
ትግሬ
11
አቶ ዳዊት
 የሰርቪስ ሹፌር
የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የትራንትፖርትመምሪያ ሀላፊ
ትግሬ
12
አቶ ጸጋዬ
ኢንስፔክተር
የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሀላፊ
ትግሬ
13
አቶ ዘነበ
ኢንስፔክተር
የገበያ ጥናት ሀላፊ
ትግሬ

ቀደም ሲል እንደማናኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚታዩ ችግሮች ቢኖሩም የተወሰደው እርምጃ ግን የወቅቱን የትግሬዎች የንግድ እንቅስቃሴ ያላንዳች ተቆጣጣሪ እንደፈለጉት ለማሽከርከር ታስቦ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ለዚህም መነሻ የሚሆነው በተለያዩ ጊዜያት በቆርቆሮ፣በብረታብረት፣በማዳበሪያ፣በሳሙና፣በከብሪት፣በሲሚንቶ ፣በዘይት፤በጨርቃ ጨርቅ በባትሪ ድንጋይ፣በኤሌክትሪክ ገመዶች የመሳሰሉት ምርቶች ላይ ተደጋጋሚ ችግር ተከስቶ በበላይ አካል የስልክ ትእዛዝ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንዲሰራጩ ተደርጉዋል፡፡ለአብነት ያክል የአቢሲኒያ ሲሚንቶ ፋብሪካ በጥራት ጉድለት ምክንያት እንዳያመርት አገዳ መስሪያቤቱ ሲያስተላልፍ በወቅቱ የከተማ ሚኒስትር የነበሩት / ካሱ ኢላላ  ፍተሻውን ያከናወኑ ባለሙያዎችን በግላቸው ቢሮ ድረስ በማስጠራት ትክክል አደላችሁም፤ልማታችንን እያደናቀፋችሁ ነው፤ኢንቬስተሮች ወደ ሀገራችን እየመጡ እንዳይሰሩ መሰናክል እየፈጠራችሁ ስለሆነ አቁሙ ሲባሉ የመስሪያቤቱ ሀላፊዎች እገዳውን ባስቸኩዋይ አንዲያነሱ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፈዋል፡፡መስሪያቤቱም እንዲፈርስ የተደረገው ባለሞያዎችም የተፈናቀሉት ሆን ተብሎ ያለ አግባብ  መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል፡፡

 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/11179 

No comments:

Post a Comment