Sunday, September 4, 2016

(አሳዛኝ ዜና) ጳውሎስ፣ ጦር ኃይሎች እና ፖሊስ ሆስፒታሎች ከቂልንጦ እስር ቤት በመጡ 49 አስከሬኖች ተጨናንቀዋል ተባለ

(ይህን ዜና ስጽፈው እጄ እየተንቀጠቀና እምባዬ እየወረደ እንደሆነ ይታወቅልኝከዘ-ሐበሻ አዘጋጆች አንዱ)


 በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ትናንት የተነሳውን ቃጠሎ ተከትሎ የመንግስት ወታደሮች እስረኞች ሊያመልጡ ነበር በሚል በመተኮስ የገደሏቸው እስረኞች ቁጥር እያሻቀበ ነው::

ከአዲስ አበባ የመጡ የታማኝ ምንጮች ዘገባ እንደሚያመለክተው ጦር ኃይሎች ሆስፒታል፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል እና ፖሊስ ሆስፒታሎች በአስከሬኖች ተጨናንቀዋል::

እንደዘገባዎች ከሆነ በአጠቃላይ ትናንት የተገደሉት እስረኞች ቁጥር ወደ 49 አሻቅቧል:: በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አሉ የተባሉ አስከሬኖች ቁጥር እስካሁን ያልታወቀ በመሆኑ ቁጥሩ 49 በላይም እንደሚያድግ የሚገልጹት ምንጮች በጦር ኃይሎች ሆስፒታል 13 አስከሬኖች; በጳውሎስ ሆስፒታል 22 እንዲሁም በፖሊስ ሆስፒታል 14 እስረኞች አስከሬን እንዳለ ገልጸዋል:: ሟቾች ቁጥር እስካሁን አልታወቀም:: ብዙ ቤተሰብ ተጨንቆ ወደ ቅሊንጦ ቢያመራም እስረኞችን ማየት እንደማይችሉ ተገልጾላቸው ተመልሰው ነበር:: ሌሎች እስረኞች ዛሬ ሌሊት 20 መኪኖች ተጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን -ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/65275

1 comment:

  1. አይዞን ወገኔ፥ ያለመስዋዕትነት ነጻነት የለም፥
    የወገኖቻችን ሞታቸው ከንቱ ሞት እንዳልሆነ እናውቃለን፥
    ወያኔዎችና ተባባሪዎቻቸው ለእያንዳንዱ ስራቸው የሚጠየቁበት ቀን ደግሞ እሩቅ ዓይደለም።

    ReplyDelete