Saturday, September 10, 2016

አዝነናል ተከፍተናል – ቁጥራቸው ያልታወቁ በጥርጣሬ የተያዙ የፓለቲካ እስረኞች ሆነ ተብሎ በተቀነባበረ ግድያ በእሳት ተቃጥለው እና በጥይት ተደብድበው ተገደሉ

ቅዳሜ ነሐሴ 28, 2008ማክሰኞ ጳግሜ 1, 2008

የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝደጋፊ እና ጧሪ ወንድ ልጇ በግፍ የተገደለባት ኢትዮጵያዊ እናት! በእውነት ልባችን እጅግ ቆሰለ! እጅግ ተስፋ ሚያስቆርጥ ጭካኔን በዘመናችን አየን! እውን ISIS ወገኖቻችንን ሲያርድ የወያኔን ያህል ጨካኝ ነበር? እኔእንጃ እነርሱስ የገደሉት ወገናቸው ያልሆነውን በአገራቸው መጥፎ እድል ጥሎት የተገኘውን የኛን ወገንን የነርሱን ጠላትን ነው።

እውን ከአርብ የካቲት 12 1929 ጀምሮ በሶስት ቀን ጣሊያን 30,000 ኢትዮጵያውያንን ሲጨፈጭፍ የወያኔን ያህል ጨካኝ ነበር? ጣሊያን የገደለው በጠላት አገር ግዛቱን ሊያስፋፋ ነበር። የኛው መንግስት ግን በገዛ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ፣ እህቱ፣ እናቱ እና አባቱ ላይ አይኤስአይኤስ እና ፋሽስት ጣሊያን እንኳን የሚሰቀጥጣቸውን ክፉ ስራ በደካማ እስረኞች እና በወላድ ላይ ሰርቷል፣ ላለፉት ዓመታት ንፁሀንን በየቀኑ ገድሏል መሪዎቻችንን በሙሉ አስሯል፣ ገድሏል እንዲሰደዱም አድርጓል አሁንስ ወያኔ ኢትዮጵያውያንን ማይገድልበት ቀን ብርቅ ሆኗል። 

ወያኔ ሰላሳ ሚሊዮንን አይደለም የአፍሪካን ህዝብ መደምሰስ የሚችል ሀይል አለኝ ብሎ በህዝብ ላይ የጦርነት ክተት አዋጁን በመሪው አስነግሯል። ራሳችንን ምንጠይቅበት ጊዜ አሁን ነው በወያኔ ባርነት ስር እስከመቼ? 25 ዓመታት ሲከፋፍልና ሲገድል የኖረ የትግሬ መንግስት ከዚህ በኋላ ይስተካከላል ብለን ምንም የምጠቀው ነገር ስለሌለን ወያኔን ከሥር መሰረቱ ለመገርሰስ መነሳት ያለብን ሰዓት አሁን ነው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለዘለዓለም ይኖራሉ፡፡

ልቦና ይስጠን
http://www.satenaw.com/amharic/archives/20892

No comments:

Post a Comment