Friday, October 18, 2013

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ላይ ተቃውሞ አሰማች


ከኢሳት የተገኘ ዜና

ጥቅምት (ስድስት)ቀን ፳፻፮ / -በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32 መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተ ክርስቲያኑዋ ታሪክ ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይይህ መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል።

የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ገለጻ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት ነው ተቃውሞው የተሰማው።

እድሉን ያገኙት ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም የሰሜን ወሎ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቄርሊዮስ የምእራብ ወለጋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ ሄኖክ፣ የጋሞ ጎፋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤሊያስ፣ የወላይታ ዳውሮ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ብጹ አቡነ ማርቆስ፣ የደቡብ ጎንደር ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድሪያስ የመንግስትን ፖሊሲ እአነሱ ትችት አሰምተዋል።

በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ፣ ግድያና ጫና መጨመሩን የተነጋሩት አባቶች፣ ፓትሪያርኩም እውነት ነው ይህ ሁሉ ጫና አለብን በማለት በሊቀ ጳጳሳት የቀረቡውን ሀሳብ ደግፈዋል።

ከመላው አለም የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀይማኖቱ መሪዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን የሀይማኖት ታሪክ በማሳነስ ባቀረቡበት ወቅት የሀይማኖት አባቶች ስሜት በተቀላቀለበት ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።

የህዝቡን መሬት ነጥቃችሁ፣ ህዝቡንም መሬቱንም የመንግስት ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ኢትዮጵያዊው ሀብትና ንብረት እንዳይኖረው አደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩት መንግስታት በባሰ ህዝቡን ያስጨነቀ ይህ መንግስት ነው በማለት አባቶቹ ተናግረዋል።

በአጼዎችም ዘመን ቢሆን ይህችን አገር ስትረከቡ እስከ ታሪኩዋ ነው፣ ታሪኩዋን አላጠፋችሁም ወይ?” በማለት ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ሲናገሩ ከተሰብሳቢው ከፍተኛ ድጋፍ ተችሮአቸዋል።

የሀይማኖት አባቶች የቤተክስርቲያኑዋን ታሪክ አዛብታችሁዋል፣ ቤተክርስቲያኑዋንም ታሪኩዋን አጥፍታችሁዋል በማለት ወጥረው መያዛቸው ታውቋል።

  Posted By.Dawit Demelash

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8446

No comments:

Post a Comment