·
digg
·
·
EmailS
·
በጎጃም ጎንቻ ሲሶ፣ ሁለት እጁ እነብሴ እና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ሰሚ ያጣ ህዝብ በሚል መንግስት ጥያቄዎቻችንን ባስቸኳይ ካልመለሰልን የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡ በተለይ ነዋሪዎቹ ቢቸና፣ደጀን፣ሞጣ ባህርዳር ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ለማስራት ከዚህ ቀደም የሞቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ቃል ቢገቡም እስካሁን አልተሰራም፤ አሁን ደግሞ የመንገድ ግንባታው ተሰርዟል ተብለናል በሚል መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ማታ በወረዳዎቹ ከተሞች ላይ በራካታ መፈክሮች ያሉት ፖስተሮችን ለጥፈው አድረዋል ሲል የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ዘግቧል።በደል የወለደው ቁጭት በሚል ርዕስ ግብር ያለልማት ብዝበዛ ነው፣አንድ መንግስት መንገድ ለመስራት ስንት ዓመት ይፈጅበታል፣ የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በርካት ጥያቄዎችንም ማንሳታቸው ታውቋል፡፡ይህንም የአካባቢው አመራሮች መስከረም 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት አይተው በመደናገጥ ፖስተሮችን ያስቀደዱ ሲሆን፤ ህዝቡ አሁንም ጥያቄያችን ካልተመለሰ በአካባቢያችን ያሉ ትምህርት ቤቶች፣ ሶቆችና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተዘግተው የተቃውሞ ሰልፍ እንወጣለን ሲሉ በማስጠንቀቃቸው እስካሁንም በአካባቢው ውጥረቱ አይሏል፡፡ በዚህ ጉዳይ የአካባቢውን ባለስልጣናት ዘሐበሻ ለማናገር ያደረገችው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡
No comments:
Post a Comment