አብሮ አደግ በሽታ ዛሬ ባለንበት በ21ኛው ሴንቸሪ በሕክምና የማይወገድበት ምክንያት ሊኖር አይችልም። ዳሩ ምን ይባላል መሰላችሁ አበው « በሽታውን የሸሸገ መድኃኒት አይገኝለትም » ይላሉ ። አቶ ስብሃትም ሊድን የሚችለውን በሽታ ሸሽጎ አጠነከረው በደሙ ውስጥ ገብቶ ሥር ሰደደበት ፤ ሱስ እንዲሆነው አደረገው ሰው የመግደል ፤ የማሰቃየት ፤ የመዝረፍ ፤ የማንጓጠጥና አስንሶ የማየት አገርንና ዘርን የማጥፋት ተንኮል የመምከር ሱስ!! በዚህ ምክንያት ነው ርእሱን የመረጥኩት፦ ይህ በሽታ ስብሃትንም ካልሞተ አይለቀውም።
ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ እንዲሁም አንዳንድ ድሕረ-ገጾች የህወሃት አባላት ወደ አሜሪካ እንደሚመጡ በተደጋጋሚ የዜና ሽፋን ሲሰጡ መሰንበታቸው ይታወሳል። እንደተባለውም የተጠቀሱት የህወሃት አባላት ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ይመስላል እዚህ መጥተው እመሃላችን ይገኛሉ።የመጡበት ሥራቸውንም እያከናወኑ ይገኛሉ። ከመጡት መካከልም የንጹሃንን ደም በማፍሰስ የሚታወቀው የገዳዮች ፊታውራሪ ስብሃት ነጋ የገኝበታል ። ስብሃት ነጋ ፀረ-ኢትዮጵያ በተለይም ጸረ- አማራና ጸረ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አቋም ካላቸውና ለ40 ዓመታት ያህል ይህ የማፍረስ በሽታ ባህሪያቸው ከሆኑት ዋናውና ቀንደኛው መሆኑ ግልጽ ነው። ስብሃት ነጋ ከበርሃ ጀምሮ በሀገር ቤት ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ባለው የኢትዮጵያ ግዛት የሚገኙ ውድ ኢትዮጵያውያንን በተለይም በጦርነት ምርኮ የተያዙ ፤ እጃቸውን የሰጡ ትውልደ ዓማራ የደርግ ወታደሮችን ጭካኔ በተሞላበት አረመኔያዊ ግድያ የፈጸመ፤በዓላማ አብረውት የተሰለፉና የትግል አጋሮቹን ለምን ኢትዮጵያዊ የሆነ አጀንዳ አነሳችሁ በማለት በቀጥታ ትእዛዝና ግልጽ ባልሆነ መመሪያ በሽዎች የሚቀጠሩ የትግራይ ህዝብ ልጆችን እየበላ የመጣ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል የመሀል አገሩን ሕዝብ በሃይምኖት ፤ በዘር እያናከሰ እሱ ካሳደገው ሥርዓት ጋር ለ22 ዓመታት ያህል ዘልቋል።ስብሃት በድርጅቱም ሆነ በህወሃት መንግሥት ከሥርዓቱ ማዕድ ተገለለ ቢባልም የጥፋት መርሁን ባርኮና ቀድሶ ተፈጻሚነት እንዲያገኝ በማድረግ ከፍተኛ ድርሻ የተወጣና አሁንም በዚህ መንገድ እየሄደ እዚህ መድረሱን የማይቀበል ቢኖር እኔ ከዚህ አይነት አመለካከት እለያለሁ ።ስብሃት ነጋ ከዚህ ከመጣ በኋላ እያደረጋቸው (እየፈጸማቸው) ያሉት ድርጊቶች ደግሞ እጅጉን የሚያሳፍሩና ጠብ አጫሪ መሆናቸው ሰውየው ፍጹም በሽተኛ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው።የሚገርመው ግን ራሱ ስብሃትም ሆነ የሱ አጃቢዎች ምን ያህል እንሰሳዎች እንደሆኑ የሚያሳየው የቆሙበትን መሬት የት እንደሆነ ሳያውቁ የተለመደውን የወንጀል ተግባር መፈጸማቸው ነው። ስብሃት ከዚህ በፊት ወደዚህ አገር በተደጋጋሚ እንደሚመጣ እሰማ ነበር። ሲመጣ ለምን እንደሚመጣና ምን አድርጎ እንደሚመለስ የያዝኩት መረጃ ባይኖረኝም ከሰውየው የግል ባህሪ ስነሳ አገር ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገውን ፤በእስራት ያንገላታውን ፤ሀብቱን ዘርፎ ያደኸውን ፤አፈር ረጭቶ ውሃ ተራጭቶ ካደገበት መንደሩ ያፈናቀለውን ምስኪን ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሰላሙን የሚነሳ መርዝ ረጭቶ ከመሄድ ያለፈ እንደማይሆን በግሌ አምንበታለሁ።
ኢትዮጵያዊ ማለት ቅንና እውነተኛ ፤ ሀይምኖተኛ(ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው)፤ ጥበብን በልቡ ያሳደረ ፤ጠንካራ መከራን የሚችልና አስተሳሰቡ ጤነኛ ፤ደፋርና ሀገር ወዳድ ጀግና ፤ አትንኩኝ ባይ ሲነኩት አሻፈረኝ ባይ ፤ ትውልዱን አክባሪ ሲሆን ወላድ በድባብ ትሂድና !! ኢትዮጵያ ዛሬም አልመከንሽም ልጆች አለንልሽ እያሏት ነው ። ከድሮውም ቢሆን ይሻላቸው እንደሆነ እያለ ነገሮችን በትዕግስት አቅቦ የያዘው ኢትዮጵያዊ ወገኔ ነገር ሲብስበትና ሲጠናበት እስከ መቼ? የሚል ጥያቄ የማንሳቱ ጉዳይ የማይቀር እንደነበረና ያም ምጽአቱ ደርሶ እነሆ እውነተና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆቿ ትግላችውን ጀምረው በዐለም አቀፍ ደርጃ በፍጥነት ተጠናክሮ እየገሰገሠ እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው። ጋዜጠኛ ሰዲቅና አክቲቪስት መስፍን በስብሃት ላይ ያሰሙትን ተቃውሞ ስሠማ የተሰማኝ ኩራት ወሰን አልነበረውም። በርግጥ ይህ ቅጥረኛና ቅሌታም ሽማግሌ በወንድማችን መስፍን ላይ ጉዳት ማድረሱ የሚያሳዝን ትራጀዲ ነው።መስፍን ግን አይደለም ይህን ሞትም ቢመጣ እንደ ስብሃት ነጋ የመሰሉትን ፋሽስቶች ሊፋለማቸው ቆርጦ የተነሳና ባለፈው ዓመት አበበ ገላው የከፈተውን አካውንት ቋቱ እንዲሞላ አስተዋጽኦ ያደረገ ጀግና ድምጻቸው ለታፈነባቸው ወገኖቹ ድምጽ የሆነ አኩሪ ሥራ የሰራ በመሆኑ የደረሰበት ጉዳት እንደማያመው እርግጠኛ ነኝ። በሽዎች የምንቆጠር ወንድሞቹና እህቶቹም እንደ አበበ ገላው ከፊቱ ከኋላውና ከጎኑ የማንለይ መሆኑንም ጠንቅቆ ያውቃልና ከዚህ የበለጠ ድል ሊያስመዘግብና ወገኖቹን ተብትቦ ከያዘው እግረ ሙቅ እስራት ርሃብ ፤ ስደት ኋላ ቀርነት ነፃ እንዲወጡ እንደሚታደጋቸው ተስፋ አደርጋለሁ።
ሌላውና ማጠቃለያየ ይህን ጉዳይ ጉዳቱ ለደረሰበት መስፍን ብቻ መተው እንደሌለብንና በውጭ የምትገኙ የተቃዋሚ ኃይሎች ፤ የስቪክ ማህበራት፤የሶሻል ሚዲያ አዘጋጅዎች ( የመገናኛ ብዙሃን)ባለቤቶች ይህን ከአገር ርቀን ከወዳጅ ዘመድና ከቤተሰብ ተለይተን እንድንኖር ያድረገ ልክፍታም ሰው እቤታችን ድረስ መጥቶ ሰላም በማደፍረሱና ወንጀልም በመፈጸሙ ተይዞ በሕግ እንዲጠየቅና ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድበት በትኩሱ መረባረብ ስለሚገባ እጃችን የገባ ጠላት ደሙ ጠርቶት ከመጣና አብሮት ያደገው የመግደልና በሰው ስቃይ የመደሰት ባህሪው እዚህ ሕግና ሥርአት በተከበረት አገርም የማይመልሰው ከሆነ የእውነተኛ ሕግ እንዴት በተግባር እንደሚተረጎም ማየት ይኖርበታል ሌሎቹም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስተማሪያ ይሆናል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም በክብር ትኖራለች!!!
ሞት ለነብሰ ገዳዮች!
አንድነትና ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
ቸር ይግጠመን።
Posted By.Dawit Demelash
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8361
No comments:
Post a Comment