oct 19.2013
(ዘ-ሐበሻ) በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በመንግስት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተካረረ መሄዱ ታወቀ። የሃይማኖት ልብስ ለብሳችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባት አትችሉም በሚል መንግስት በክርስቲያን እና በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ባወጣው አዲስ መመሪያ የተነሳ ተናሪዎቹ የምግብ ጥራትን እና ሌሎች ጉዳዮችን አክለው በትምህርት ቤቱ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበረ ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል። ዛሬ ከደብረ ማርቆስ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሰረት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የትምህርት ቤቱ አካባቢም በፌደራል ፖሊሶች ተወሯል። ፎቶቹ የሚከተሉት ናቸው። ዝርዝሩን ተከታትለን እንዘግባለን።
Posted By.Dawit Demelash
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8483
No comments:
Post a Comment