Thursday, January 30, 2014

በጎንደር የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች ታሰሩ

(-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ በጎንደር ከተማ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ወጥቶ ለሱዳን በሚሰጠው መሪት ዙሪያ ድርጊቱን እንዲቃወም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ከተማ መታሰራቸው ተሰማ።
-ሐበሻ ከሰማያዊ ፓርቲ አካባቢ የደረሳት መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።
ፖሊስ የሰልፉን ቀስቃሶች ካሜራ እና ላፕቶፖችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችን መውሰዱን የጠቆመው ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኘው መረጃ ፖሊስ ዛሬ በቅስቀሳ ላይ የነበሩትንእሁድ የሚደረገው ሰልፍ ሕጋዊ ፈቃድ ስለሌለው መቀስቀስ አትችሉምያላቸው ሲሆን አስተባባሪዎችምበሕገመንግስቱ መሠረት ሰልፍ ለማድረግ ማስፈቀድ የለብንም። ቀድመን ማሳወቅ እንጂ። ይህን ደግሞ አድርገናልቢሉም ፖሊስ ማስተዋወቅ አትችሉም በሚለው አቋሙ ጸንቶ መደብደብ መጀምሩም ተሰምቷል።
የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ደጋፊዎች ከድብደባው በኋላ ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው መታሰራቸውንና ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አለመፈታታቸውም ታውቋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12366

No comments:

Post a Comment