Sunday, February 23, 2014

ዛሬ በባህርዳር የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ፤ ሕዝቡ በባዶ እግሩ በመውጣት በብአዴን/ኢሕአዴግ ላይ ቁጣውን ገለጸ


(
-ሐበሻ) የአማራው ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን የሚመሩትን የአማራ ሕዝብ በጸያፍ ቃላት መሳደባቸውን ተከትሎ አንድነት እና መኢአድ ፓርቲዎች በጋራ በባህርዳር ዛሬ በባህርዳር የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በሰላም ተጠናቀቀ።ህዝቡ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላልሲል ለብአዴን/ኢህአዴግ ተቃውሞን አሰማ።
10 ሺህዎች የሚቆጠሩ የባህርዳር ነዋሪዎች ቁጣቸውን ለመግለጽ በወጡበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ በአቶ አለምነው የተሰደበውን ለማስታወስና ቁጣውንም ለመግለጽ በባዶ እግሩ እንደነበር ከስፍራው መረጃ ያደረሱን የዘ-ሐበሻ ተባባሪዎች ገልጸዋል።ሰልፈኛው ጫማውን አንገቱ ላይ በማንጠልጠል በሰላማዊ ሁኔታ በባዶ እግሩ በመሄድ በአዲስ የተቃውሞ ስልት ድምጹን አሰምቷልያሉት በስፍራው የነበሩ የሰልፉ ታዳሚዎች እንዲህ ያለው የትግል አገላለጽ የሚደነቅና ወደፊትም ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለዋል

ባህር ዳር በፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰራጭተው የዋሉ ሲሆን ከከተማዋ አጎራባች አካባቢዎች ጭምር የተሰባሰቡት ልዩ ሃይሎችና የክልሉ ፖሶች በነዋሪው ላይ ውጥረት ለመፍጠርና በሰልፉ እንዳይሳተፍ በከፍተኛ ሁኔታ ቢሞክሩም ሕዝቡ ግን በአቶ አለምነውና በብአዴን ላይ ቁጣውን ከመግለጽ አላገደውም ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎችወያኔ ለውድቀቷ አማራን ትሳደባለችበሚል ቁጣ ካለምንም ፍራቻ አደባባይ ወጥተዋል ብለዋል።


በተለይ ኢሕአዴግ በባህር ዳር ከተማ ሕዝቡ ሰልፍ እንዳይወጣ 51 ጠርናፊና ተጠርናፊዎችሰልፉ ተሰርዟልየሚል ሃሰተኛ ወሬ በማውራት ሕዝቡን ለማደናገር መጣሩን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የአንድነት እና የመኢአድ መሪዎች እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ በመኪና እና እግር በመሄድ ሕዝቡን በመቀስቀስ የዛሬውን ሰልፍ ለስኬት አብቅተውታል ሲሉ ዘግበዋል። በተለይም የከተማዋን የባጃጅ ሾፌሮችን በማህበራቸው አማካኝነት ኢሕአዴግ ሰብስቦ ይህን ሰልፍ የምታጅቡ ከሆነ ፈቃዳችሁን ትቀማላችሁ የሚል ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም አቶ አለምነው አማራውን ከሰደቡት ስድብ አይበልጥም በሚል ባጃቻቸውን አስቀምጠው ሰልፉን መቀላቀላቸውን ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል።



በባህር ዳር በተደረገው በዚህ ትልቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር በትላልቅ ስፒከሮች ለሰልፈኛው በድጋሚ የተሰማ ሲሆን ሰልፈኛውም በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን በአንድ ድምጽ አሰምቷል።
ገበሬው በገዛ መሬቱ ስደተኛ አይሆንም

ክብራችንን የደፈሩት የብአዴን አባላት ለፍርድ ይቅረቡ

ነፃነታችን በእጃችን ነው

ህዝቡ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል

የመሬት ቅርምቱ ይቁም

አማራውን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ለመለየት የሚደረገውን የኢሕ አዴግ ሴራ በጥብቅ እናወግዛለን

ብአዴን/ኢሕአዴግ አማራውን የመምራት የሞራል ልእልና የለውም የለውም

ሕዝብን ከእርስቱ ማፈናቀል ይቁም!”

የሚሉና አቶ አለምነው ለፍርድ እንዲቀርቡና ይቅርታ እንዲጠይቁ የሚጠይቁ መፈክሮች በዛሬ ፌብሩዋሪ 23 ቀን 2014 ሰልፍ ላይ ተሰምቷል።

በባህርዳር ግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 የሚገኘው አንድነት ፓርቲ /ቤት መነሻውን አድርጎ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የተጀመረው ይሄው የተቃውሞ ሰልፍ ከግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 ተነስቶ በድብ አንበሳ አካባቢ ዞሮ ወደ ክልሉ መስተዳድር /ቤት ያመራ ሲሆን በሰልፉ ላይ ንግግር ያደርጉት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው አቶ አለምነው መኮንን ይቅርታ የማይጠይቁና ከስልጣናቸው የማይወርዱ ከሆነ ፓርቲያቸው በድጋሚ በባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራና ባለስልጣኑን በፍርድ ቤት እንደሚከስ አስታውቀዋል። የህዝቡን ከፍርሃት መላቀቅ ያደነቁት ኢንጂነር ግዛቸው በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኘውን ሕዝብ አመስግነዋል። በተጨማሪም በዚህ ሰልፍ ላይ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ ንግግር አድርገዋል። አቶ አበባው በንግግራቸው አቶ አለምነው መኮንን በህግ እንዲጠየቅ፣ ብአዴን የአማራ ህዝባ ወኪል ነኝ ማለቱን እንዲያቆምና አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ አስረግጠው ተናግረዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13073

No comments:

Post a Comment