Tuesday, February 18, 2014

የጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛው ከአንድነት ጽ/ቤት ሲወጣ በመኪና ተገጨ


(ፍኖተ ነፃነት) ጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ዮሃንስ /እግዚያብሄር ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በመኪና እንደገጩትናገና እንገድልሃለንየሚል ዛቻ እንደሰነዘሩበት ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡
ጋዜጠኛው ከአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ጋር በፓርቲው /ቤት ቃለምልልስ አድርጎ ወደ መገናኛ አካባቢ ሲደርስ ኮድ 1 የታርጋ ቁጥር18345 የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ሆነ ብሎ አደጋ አድርሶበታል፡፡ገጭታቸሁኝ ወዴት ትሄዳለትሁበማለት ሲጠይቃቸውምገና እንገድልሃለንብለውት እንደሄዱ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡

ጋዜጠኛው ላይ የመኪና አደጋ ያደረሰው ታክሲ ውስጥ ሹፌሩና አንድ ግለሰብ ብቻ እንደነበሩም ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ ዮሃንስ /እግዚያብሄር በአሁኑ ሰአት ጉዳዩን ለፖሊስ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡

     https://www.zehabesha.com/amharic/archives/12903

No comments:

Post a Comment