የትግራይ ህዝብና ታጋዮቹ የህ.ወ.ሃ.ት ትጥቅ ትግል የተጀመረበት ቀን ከ1967 ዓ/ም የካቲት ወር ጀምሮ እስከ 1983 ዓ/ም በየአመቱ ለምትመጣዉ የካቲት 11 ለማክበር በናፍቆት የሚጠብቁት ነበር። በአሉን ለማክበርም የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ የሚለበስ ያላቸውን ሃብት በማሟጠጥ አስቀድመዉ ይዘጋጁበት ነበር የትግራይ ህዝብ ይቅርና በነፃ መሬት በጠላት ውስጥ በስደት በተለይ ደግሞ በ1977 ዓ/ም በድርቅ፣ በደርግና በሻዕቢያ ወረራ ወደ ሱዳን ተሰዶ በለጋሾች በተሰጣቸዉ ዱቄትና ስንዴ ጠላ ጠምቆ ዳቦ ጋግሮ በሰላማዊ ሰልፍ ያከብራት ነበር። በአውሮፓ፣ በአሜሪካ በሌሎች ክፍለ አለማት በስደት ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችም በተለያየ መንገድ ያከብሩ ነበር።
ይህ የሆነበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በፋሽስታዊ ደርግ ይደርስበት ለነበረዉ ግፍ በየላቲት 11 የተወለደዉ ህ.ዋ.ሃ.ት ከችግሬ ያላቀቀኛል ከሚል መንፈስ ነበር የካቲት 11 ሲያከብር የነበረዉ። የትግራይ ህዝብ የካቲት 11 ከአማልክት በላይ ያመልካት ነበር የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎችም የህዝቡን ስሜት በመጠቀም እንደ የመነሳሻ ጊዜ በመጠቀም ይጠቀሙበት ነበር ህዝቡም በህ.ዋ.ሃ.ት ተጠቃሚ እንሆናለን ከሚል ስሜት ደርግ ከተወገደ በኃላ የህ.ዋ.ሃ.ት ካድሬዎችና መሪዎች የሚሉትን ይሰማ ነበር ለትግራይ ህዝብ ብለዉ ለመላዉ የሃገራችን ህዝብ የገቡለት ቃል የክህደት ሁኔታ ስላሳዩት የካቲት 11 በአል የማክበር ስሜቱ እያሽቆለቆለ መጣ። በአሉን አክበር ሲባል እምቢታ አሳየ። እየተገደደ ወደ ሰልፍ ሲገባም የመሪዎች ዲስኩር ሲጀመር እየጠላቸዉ ፈርሶ ይሄድ ነበር። በክልል ደረጃ በዞን ፣ በወረዳ፣ በቀበሌ ህዝቡ እየተገደደ ገንዘብ በማውጣት በግብዣ ይምበሻበሽ ነበር። በዛን ጊዜ የ.ህ.ዋ.ሃ.ትመሪዎችና ጥቂት ካድሬዎች ኪሳቸዉ ይሞላ ነበር ህዝቡ የካቲት 11 ለማክበር ይጓጓ የነበረዉ ሌላ ቀርቶ ልጆቹን ወደ ትግል ሜዳ ለመስዋእት ሲሸኝ በየካቲት 11 ነበር ያነበረዉ እምነትና አምልኮት የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ምንም የማይጠቅሙት መሆናቸዉን እያወቀ ሲመጣ ፍላጎቱ ተሟጦ የካቲት የራሱ እንዳልሆነች በማወቁ በአሉን ላለማክበር ተቃውሞ እያሳዩ መጣ።
እነዚህ ዘመናዊ ግራዚያኒ መሰል መሪዎች ግን ህዝቡን ያለፍላጎቱ አስገድደዉ ሰልፍ እያሰወጡ በህ.ዋ.ሃ.ትና የመንግስት ብዙሃን መገናኛ በማስተጋባት ለአለም በማደናገር በህዝብ ተወዳጅ እንደሆኑ ያደናግራሉ። የኃላ ኃላ ደግሞ ለህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ወደ ስልጣን ያወጡት የህዝብ ልጆች አገር አትሽጡ ብለዉ ተቃውሞ ባሳዩ ታጋዮች በጅምላ አሰርዋቸዉ ያለ አንዳች መቋቋሚያ ጣልዋቸዉ በዛን ወቅት የትግራይ ህዝብ ጥላቻዉን ገለፀ ቆየት ብሎም በትግራይ የሚገኙ 120 ሺ አካለ ጉዳተኞች በስማቸዉ የተለመነ ሃብት ቀምተዉ ሜዳ ላይ ጣልዋቸዉ የህዝቡ ጥላቻ ተባባሰ ። በቃ የካቲት 11 የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎችና የጥቂት ተጠቃሚ ካድሬዎች መፈንጠዣ ሆነች ደርግ ከተወገደ ከ1983 ዓ/ም ወዲህ የካቲት 11 በአል ለማክበር የባከነ ሃብት መበቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል የሚከፍቱት ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶች ያሰራ ነበር ይህ የአብዮት በአል እየተባለ የሃገር ሃብት ማባከን በህ.ዋ.ሃት መሪዎች ታጥሮ የቀረ አልነበረም። በአፋር፣ በአማራ፣ በሱማሌ፣ በጋንቤላ፣ በደቡብ ህዝቦች የፓርቲዎች የልደት በአል እየተባለ ለማክበር በቢሊዮን የሚገመት ሃብት ባክነዋል እነዚህ ፓርቲዎች በአላቸዊ ሲከበር የአውሮፕላን፣የመኪና ትራንስፖርት የመንግስት መኪኖች በዛ በአል ማክበር ተጠምደዋል ባጠቃላይ የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች የጀመሩት የሃገር ሃብት ማባከን እንደ ወረርሽን በሽታ አገር ኣጠፉ ።
ያለፈዉ አልፎ የዘንድሮ 2006 የካቲት በአል አከባበር
የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች በአሁኑ ጊዜ የየካቲት 2006 የበአል አከባበር ምክንያት በማድረግ ህዝቡን የህ.ዋ.ሃ.ት ስርአት በፈጠረበት ችግር ልቡ ስለሸፈተ ለውጥ ፈላጊ በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ በ58 ወረዳዎች በ7 ዞኖች ለሁሉም ቀበሌዎች ህዝብ የውል አበል እየተሰጠ በስብሰባ በመናጥ ህ.ወ.ሃ.ት አለች ወይ በሚል ጥያቄ ሲያወያዩት ህዝቡ ደግሞ ህ.ዋ.ሃ.ት የለችም ከድታለች ነዉ ያላቸዉ።
በሌላ በኩል ህዝቡ በሁሉም የወረዳና ዞኖች ፣ ከተሞች ተገዶ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግና ለሰላማዊ ተቃውሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለመነጠል ዘመቻ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል። በተጨማሪም በሺ በሚቆጠሩ ቀበሌዎች በካድሬዎች እየተገደዱ ጠላ ተጠምቆ፣ እንጀራ ተጋግሮ ግብዣ እንዲደረግ እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ሁሉም ከተሞች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ስለ ህ.ወ.ሃ.ት ታሪክ አጀንዳ በመያዝ በፕላኔት ሆቴልና በሃወልቲ ሰማእታት አዳራሽ የትግራይን ክልል እድገት ተሞክሮ እና የህ.ዋ.ሃ.ት ታሪክ ይሰለጥናሉ። በመላዉ ክልልና ዞን ቀበሌዎች እንደ አዲስ የተበረዘና አሁን ላሉ መሪዎች ታሪክ በሚያድስ መንገድ ታሪክ እያስተማሩ ይገኛሉ።
በተለይ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ የትግራይን ተሞክሮ ለመውሰድ ተብሎ ከመላዉ ኢትዮጵያ ክልሎች የኢ.ህአ.ዴ.ግ.ና አጋር ድርጅቶች ወጣት ዜጎች በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ለአንድ ወር ያህል ምግብና ውል አበል ተዘጋጅቶላቸዉ የውሸት ታሪክ እየሰለጠኑ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ የሚደረገዉ አሁን ያለዉ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የተበላሸ ስርአትና በህዝቡ ያለዉ ችግር እንዳይታወቅና ለመሸፈን የሚደረግ አሻጥር ነዉ።
የየካቲት ውጤት
ከ1983 የካቲት 11 እስከ 2006 የካቲት 11 የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ምን ተጠቀመ? ሁሉም ህዝብ የገጠርና የከተማ የመሬት ባለቤትነት የተቀማበት፣ ዜጎች በግላቸዉ መሬት አግኝተዉ መጠለያ ሰርተዉ እንዳይኖሩባት የተደረጉበት፣ መብታቸዉ ተነጠቁበት፣ ዜጎች የግል ሃብት የማፍራት መብታቸዉ የተከለከሉባት፣ ከግለ-ሰብ እስከ ብሄር -ብሄረሰቦች ህዝቦች መብታቸዉ ፍፁም የታፈኑባት፣ በስም ብሄር ወኪሎች የኢህአዴግ ቡድን የሚፈነጩባት፣ የህግ የበላይነት መከበር ቀርቶ ከዳኛ በላይ የፖሊስ ስልጣን የነገሰበት፣ እቺ ለሁሉም ክልሎች እንደሰርቶ ማሳያ ሞዴል የተባለች ትግራይ የስራ አጥነት ተስፋፍቶ አምራች ሃይል ወጣቶች ወደ ስደት የፈለሱባት፣ ህዝብ ነፃተኑን አጥቶ ተጨቁኖ የሚኖሩባት፣ ህዝቡ ወደ ኃላ ተመልሶ ልጆቹን ለመስዋእት መክፈሉ የሚቆረቆሩባት፣ የተማሩና ያልተማሩ ወጣቶች ስራ አጥተዉ በጎዳና የተዘረጉባት ፣ ዜጎች ምክንያቱ ባልታወቀ ሞተዉ በጎዳና የሚገኙባት፣ ሁሉም ህዝብ በ1ለ5 በ1ለ10 በ1ለ30 እየተደራጀ በስለላ መርበብ የታፈነባት፣ ነዋሪ ህዝብ አስተማሪዎች መላዉ የመንግስት ሰራተኛ በከባድ የኑሮ ውድነት ምክንያት ሊኖሩ የማይችሉበት ሁኔታ የተፈጠረበት ፣የህዋህት መሪዎችና ጥቂት ካድሬዎች የሚናጥጡበት የካቲት 11 አካል ጉዳተኞችና የተሰዉ ታጋይ ወላጆች አረጋውያንን ለልመና የተዳረጉበት፣ የህፃናት መብት የማይከበርበት፣ህፃናትና ቦዘኔዎች ተደራጅተዉ በዝፅ ደንዝዘዉ ለሰላማዊ ፖለቲካ ፓርቲ የሚደበድቡባት፣ የሰላማዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የታገዱባት ፣የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋዜጠኞች በእስር ቤት የሚማቅቁባት፣ የፓርቲ አባላት በግልፅ ባደባባይ የሚደበደቡበት፣ የተማሩና ያልተማሩ ሴቶች በድህነት ምክንያት ወደ ዝሙት ስራ የተሰማሩባት፣ ትምህትቤት መስጊድ ፣ቤተክርስቲያን፣ ዩኒቨርሲቲዎች የህ.ዋ.ሃ.ት የፖለቲካ ማደራጃ የሆኑባት ፣የትምህርት ጥራት ትግራይ ኃላ የተሰለፈችበት የአስተማሪነት ስራ የተጠላበት፣ የሃይማኖት መብት የማይከበርባት የካቲት 11 2006
ህዝብ ታሞ ህክምና ኣጥቶ ወደ ጥንቆላና ደፍተራ ጥገኛ ሆኖ የቀሩባት የህ.ዋ.ሃ.ት አባል ፓርቲ ያልሆነ ስራና የትምህርት እድል ሌሎች እንደ ዜጋ ሊያገኘዉ የሚገባ ጥቅማ ጥቅም የተነፈጉባት፣ የተበላሸ አስተዳደርና የፍትህ አጥነት የነገሰባ፣ት የሃገራችን ሃብት በባለስልጣናትና ጥቂት ባለ ሃብቶች የተመዘበሩባት፣ የካቲት 11 የንግድ ስራ የቀዘቀዘባት፣ በመሬት ፖሊሲ ምክንያት የግል ኮንስትራክሽን ስራ ፍፁም የተቋረጠበት፣ መላዉ ትግራይ በውሃ እጦት የተቸገረበት፣ ጥቂት ሰዎች በምቾት የሚኖርባት ብዙሃኑ በረሃብ የሚታረዙባት፣ ቂም በቀልና ውሸት የነገሰበት፣ በውሸት ልማት የበለፀገች፣ የዲሞክራሲ ሽታ የማይታይባት የካቲት 11
በወሊድ ምክንያት ብዙ እናቶች የሚሞቱባት፣ ትላልቅ ከተሞች ከገጠር በሚሰደዱ አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ህፃናት በልመና የተሰማሩባት፣ የክለሉ ሃብት በህ.ዋ.ሃ.ት አመራር ቁጥጥር ስር የገባበት፣ ለህፃናት ለፍትህ ፣ ለእኩልነት ብለዉ የተሰዉ ጀግኖች የተከዱባት የካቲት 2006 በሚሊዮኖች መስዋእት የፀደቀዉ ህገ-መንግስት ፍፁም የተናደባት ፣በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በስደት የተዋረዱባት፣ የሃገራችን ሉአላዊነት የተቆራረሰባት፣ ከፌዴራል እሰከ ቀበሌ የተዘረጋ የህ.ወ.ሃ.ትና የአጋር ፓርቲዎች አመራር በሙስና የተበላሹበት፣ የካቲት 2006 የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ፋሽስታዊና ፀረ-ዲሞክራሲ ባህሪያቸዉ የተጋለጡባት የህ.ዋ.ሃ.ት ቁንጮዎች የሃገራችን ሃብት አሟጠዉ ውጭ ያሰፈሩባት ቤት ሰርተዉ ለልጆቻቸዉ ውጭ ያሰፈሩባት ፣ ህዝቡ አማራጭ አጥተዉ በጨለማ ቁጭ ያለባት፣ የሃገራችን ምሁራን ተገልለዉ ሃገሪቱ በጥቂት መሃይም ካድሬዎችና በቀበሌ ቦዘኔዎች የምትመራበት፣ ከስዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ዜጎች ማቋቋሚያ አጥተዉ ተመልሰዉ ወደ ስደት የፈለሱባት የካቲት 2006 ባጠቃላይ የካቲት 2006 ለህዋሃት መሪዎች ጨለማ ለህዝብ ብሩህ ተስፋ ሊፈነጥቅበትየሚያስችል ሁኔታ ነዉ ያለዉ ምክንያቱም የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች መዋቅራቸዉ ከድቷዋቸዉ የተቃውሞ ሃይል እየበረታ በመምጣቱ ስጋት ላይ ይገኛሉ።
ሁኔታዉ እንደዚህ እያለ የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ለመጭዉ 2007 ምርጫ ታሳቢ በማድረግ በኢትዮጵያ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝበ ጋር እንዳይገናኙ ለህዝብና ለፓርቲዎች አፍኖ መፈናፈኛ አሳጥቷቸዋል ይህ ተግባር ከወዲሁ ከህዝቦች የተባበረ ትግል ማገቻ ማግኘት አለበት እላለሁ።
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/12808
No comments:
Post a Comment