Saturday, February 15, 2014

ግብጽ ከሩሲያ ጋር የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ተደራደረች

February 15, 2014 06:00

በመጪው ምርጫ የግብጽ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ የሚባሉት የግብጽ ጦር ዋና አዛዥ ፊልድ ማርሻል አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ከሩሲያ ጋር 2ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ድርድር ላይ መሆናቸው በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡
ረቡዕ ሞስኮ የገቡት አል-ሲሲ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር የመሣሪ ውሉን በተመለከተ የሁለት ለሁለት ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ ከግብጽና ከሩሲያ በኩል የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ  ሚኒስትሮች የድርድር ውሉ ዋና አካላት ናቸው፡፡
ጉብኝታችን በግብጽና ሩሲያ መካከል የወታደራዊና የቴክኖሎጂ ልማት ስምምነት በማድረግ አዲስ ምዕራፍ መክፈት ይሆናልያሉት አል-ሲሲ ትብብሩን ለማፋጠን ተስፋ እንዳለቸው ጠቁመዋል፡፡
ይጸድቃል የተባለው ይህ ስምምነት ከሩሲያ በኩል ድጋፍ እንዳለው ፕሬዚዳንት ፑቲን አል-ሲሲን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ጠቁመዋል፡፡የግብጽ ፕሬዚዳንት ለመሆን የምርጫ ውድድር ለማድረግ መወሰንዎን አውቃለሁ፤ በራሴና በሩሲያ ሕዝብ ስም መልካሙን ሁሉ እመኝልዎታለሁብለዋል ፑቲን፡፡

በዚህ ስምምነት መሠረት ግብጽ ዘመን ያለፈባቸውን ሩሲያ ሰራሽ የጦር መሣሪያዎቿን በአዳዲስና ዘመናዊ መበተካት ወታደራዊ ብቃቷን በከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ እንዳሰበች ማረጋገጫ ነው የሚሉ ወታደራዊ ተንታኞች ይህ የግብጽ አካሄድ በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ አፍሪካ የሚያመጣው ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ እንደሚሆን አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ስምምነቱ ይፋ ከሆነ በኋላ በሚወጡ መረጃዎች ዝርዝሩ የሚታይ እንደሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች እንዲህ ዓይነቱ ሚሊታሪዝም (ወታደራዊ ተስፋፊነት) ግብጽ በተለይ በአቅራቢያዋ ባሉ አገራት ላይ ልታራምደው የምታስበውን ፖሊሲ የሚጠቁም እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ብዙዎቹንም ከፍተኛ የዓቅም ፈተና ውስጥ ይከታቸዋል ተብሎ ይገመታል፡፡

 http://www.goolgule.com/egypt-negotiates-2-billion-arms-deal-with-russia/

No comments:

Post a Comment