በዛሬው እለት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአንድነትና የመኢአድ
አባላት በሞንታርቦ ጠንካራ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡ በተለይ በራሪ ወረቀት የሚያድሉ አባላት የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም
በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩና የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶችን እያደሉ ነው፤ የከተማው ነዋሪም አጋርነቱን
እየገለፀ ይገኛል፡፡
ጫማ በማውለቅ በብአዴን ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል
በረዳት አንስፔክተር ክንፈ ሀይሌ ጉልላት የሚመራ የፖሊስ ሀይል በተለምዶ ከአባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ
የመኪና ላይ ቅስቀሳ እናዳይደረግ ማይክራፎን መበስበር ጭምር ሙከራ ቢያደርግም የከተማዋ ነዋሪዎች የፖሊሶቹንና የትራፊኮቹን
ህገወጥ ድርጊት አስቁመዋል፡፡ አካባቢው “ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” በሚለው ዜማ
ደምቋል፡፡
ፖሊሶቹ ከህጉ ይልቅ ለአለቆቻቸው ታማኝነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸው ትዝብት ውስጥ
ጥሏቸዋል፡፡ ህዝቡ ቀስቃሾቹ ሊነኩ አይገባም በማለት ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል ረዳት ኢንስፔክተሩ ተጨማሪ ሀይል እንዲመደብላቸው
ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም በህዝቡ ጫና የቅስቀሳ ቡድኑ ስራውን ቀጥሏል፡፡
http://ethioforum.org/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A5-%E1%89%A0%E1%88%B0%E1%8B%B0%E1%89%A0%E1%8B%8D-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%88%98%E1%8A%AE/
No comments:
Post a Comment