Sunday, December 14, 2014

ጀግኖችን እያሰብን የበኩላችንን እንወጣ!! በመስዋዕትነት ነፃነት ይረጋገጣል፤ ሰላም ይሰፍናል። (በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ)


መምሀር የኔሰው ገብሬ በዳውሮ ከተማ ነዋሪና ትጉህ መምህር ነበር። እንደማንኛውም አገር ወዳድና የወገን
ተቆርቋሪ እርሱም የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓተ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ገደብ የለሽ ሰቆቃ መቀበል
ባለመቻሉ ፣ በአንፃሩ በተቃውሞ አቋሙን በአደባባይ የሚገልጽና ይህ እኩይ ድርጊት እንዲቆም ታግሎ ለማታገል
በጽናት ስለቆመ የሥርዓቱ ሰለባ ሆነ። እስራቱና እንግልቱ አልበቃ ብሎ ከሥራ መደቡም ተገለለ ። በዚያው ላይ
ፍትህ ለማግኘት የሚያስብ ሕሊናና የሚሰማ ጆሮ እንደሌለ ተረድቶ ለአሰቃዩትም ለአጠቃላይ ሕዝቡም መራር
መልእክት ያስታላልፋል ብሎ ያሰበውን መስዋዕትነት መርጦ ራሱን በጋዝ አንድዶ ሕዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም
መስዋዕት ሆነ። ይህ ተግባሩ ቀደም ሲል ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ሉዓላዊነት ፣ ለመምህሩ መብትና ጥቅም
መከበር ሲታገሉ መስዋዕት የሆኑትን፣ በእስራት የማቀቁትን፣ ከእናት አገራቸው ተሰድደው በባዕድ አገር
ያለውዴታቸው የእንግልትና የናፍቆት ኑሮ የሚገፉትን መምህራን፣ የሙያ ማህበሩ የኢመማ መሪዎችን፣
ደጋፊዎቻቸውንና ተባባሪዎቻቸውንም የሚያስመካ አንጸባራቂ መስዋዕትነት ሆኖ አልፏል። መቼም ቢሆን ነፃነት
ያለመስዋዕትነት ተገኝቶ አያውቅም። በሕዝቡ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ የሚገኘውን ጨካኙን፣ ዘረኛውን፣ ግፈኛውን፣
ገዳዩንና አገር አጥፊውን ወያኔን ቆርጠን በመታገልና በመስዋዕትነት ብቻ ነው ነፃነታችንን ልናገኝ የምንችለው።
በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ መምህር የኔሰው ገብሬ ራሱን መስዋዕት
ያደረገበትን ሕዳር 1 ቀን በክብር ያስታውሳል፤ ቀጥሎ ያለውንም ግጥም በመታሰቢያነት ያቀርባል።

ከአመታት በፊት - ከአምናው ከአቻምናው፣
ከጻፍን-ካነበብነው- ካየን ከሰማነው፣
አጀብ ነው ይገርማል- ያሁኑስ የጉድ ነው ፣
የመምህሩ ትግል ልዩ ነው ከወትሮው፣
ከሥራ መባራር-መታሰር ግድያ---ሁሉን ተጋፈጥነው፣
ይኽን ችሎ መኖር- ሕይወት ትርጉም የለው፣
ብሎ ወሰነና- ቆራጥ ሆኖ አቅዶ፣
ጋዙን አርከፍክፎ- ራሱን አንድዶ፣
ሕዝብን አስተማረ - ጠላት እንዲያጠፋ ዱር ገድል አሳዶ።
የኔሰው ገብሬ - የሙያ አጋሬ ፣

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37147

No comments:

Post a Comment