Saturday, December 6, 2014

ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል * ማዕከላዊ አጠገብ የሚገኝ እስር ቤት ተወስደዋል

(ነገረ ኢትዮጵያ) በሰልፉ ሰልፉ ወቅት ታፍሰው ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ እጅና እግራቸውን እንደተሰበረ እማኞች ገልጸዋል፡፡ ታሳዎቹ መጀመሪያ ከነበሩበት ጨርቆስ አካባቢ የሚገኝ እስር ቤት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ሶስተኛ ወደተባለው እስር ቤት ሲዘዋወሩ እያነከሱና በሌሎች ታሳሪዎች ደግፈዋቸው ታይተዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት እጁን እንደተሰበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር ብርሃኑ ተክለያሬድና ሌሎች በርካታ ታሳሪዎች በሌሎች ታሳሪዎች ተደግፈው ታይተዋል፡፡
በሌላ ዜና በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የታፈሱት አመራሮች ማዕከላዊ አጠገብ ወደሚገኘው እስር ቤት ተዛወሩ::

9ኙ ፓርቲዎች በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ የታፈሱትና ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ታስረው የነበሩት የፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ማዕካለዊ ጥግ ወደሚገኘውና በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ ወደሚጠራው እስር ቤት መዛወራቸው ታወቀ፡፡

ታሳሪዎቹ ከጨርቆስ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ሶስተኛ የተዛወሩት ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ ሲሆን ሶስት ሰዓት ተኩል አካባቢ በሶስትትልልቅ አውቶቡሶች የታጨቁ ታሳሪዎች ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መድረሳቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በሌላ አውቶቡስ የተጫኑ እስረኞች ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸው ታውቋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ለታሳሪዎች እራትና ልብስ ሊያድሱ ወደ እስር ቤት ያቀኑት ቤተሰቦችና የትግል አጋሮች ምግብ እንዳያስገቡ መከልከላቸውን ገልጸዋል፡፡ በሌላ ካሳንቺስ አካባቢ የሚገኘውና ስድስኛ ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት አካባቢ ሌሎች ታሳሪዎች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ጨርቆስ እስር ቤት ታስረው የነበሩት ሁሉም አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ወደ ሶስተኛ ወይንም ሌላ እስር ቤት ይዛወሩ አይዛወሩ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ተሳታፊዎች ከታፈሱበት ጊዜ ጀምሮ ሶስት ያህል እስር ቤቶች እንደተዛወሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/36893

No comments:

Post a Comment