Saturday, September 19, 2015

ዜጐችን ከቀያቸው ማፈናቀል የልማታዊነት መገለጫ አይሆንም !!

ዳዊት ደምመላሽ ( ኖርዎይ
   
     (ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

የህወሃት/ኢህአዴግ/ መራሹ መንግስት ዜጐችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ልማታዊ መንግስት ነኝ እያለ ነጋ ጠባ ይደሰኩርልናል አንድ መንግስት እንደ መንግስት መናገር የሚችለው ህዝቦቹን ከድህነትና ከኌላ ቀርነት እንዲሁም ከስደት ሲያላቅቅና የህዝቦችን አንድነት መልካም ግንኙነት ሲያጠናክር የሀገር ሉሃላዊነትንና ዳር ድንበርን ሲያስከብር ነው ።

ህዝቡ በኑሮ ውድነት የሚሰቃይበትና የበይ ተመልካች በሆነበት ቁርሱን በልቶ ምሳውን በማያገኝበት ወጣቱንና አገር ተረካቢውን ትውልድ ለስደት በመዳረግ በሰሃራና በሜድትራንያን ባህር እንዲሁም በተለያዩ ጐረቤት አገራት በእስር ቤት ውስጥ ታጉረው የመንግስት እያሉ ሰሚ ሳያገኙ ለአደጋዎች በተጋለጡበት የጐሳ ስሜት ተንሰራፍቶ አንዱ የበላይ ሌላኛው የበታች አንዱ ጐሳ አንዱን እንዲጠላና ሰላሙ እንዲናጋ ህዝቡ ወልዶ ከብዶ ከኖረበት መንደሩ በሐይል እየተፈናቀለ እንዲበታተን የሚያደርግ ቡድን የሚመራው መንግስት ጥፋታዊ እንጂ ልማታዊ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም ።

የህዝብን መብት ገፎ የሚፅፉ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮችንና አባላቶችን አገሪታ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች አጉሮ የአገሩን ሀብትና ለም መሬት ጭምር ቆርሶ ለባዕድ አሳልፎ እየሰጠና ተባብሮ የአገሪታን አንጡራ አብት እየመዘበሩ በውጭ አገራት ባሉ ትላልቅ ባንኮች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው በመቶ ቢሊዬን ዶላሮችን ዘርፈው እያስቀመጡ ባሉበት አገር ውስጥ ልማታዊ መንግስት አለ ብሎ ማመን ቀርቶ መናገሩ የስህተት ስህተት ነው ።

ለራሱ ህዝብ አክብሮትና ብሔራዊ ስሜት የሌለው ቡድን ከድሃው የኢትዬጵያ ህዝብ በተዘረፈው ገንዘብ የውጭ አገር ተባባሪዎቹን ለማስተናገድና ለመሳብ በአገሪቷ ውስጥ ትላልቅ ሆቴሎችንና መንገዶችን በመገንባቱ ብቻ ልማታዊ መንግስት ነው ብሎ መቀበልና ማስተጋባት ድንቁርና መገለጫ ነው።

በአጭሩ ልማት ሲተረጐም የህዝብ ኑሮ መሻሻልን፣ የሰብዓዊ መብት መከበርን፣ የዜጐችን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና መኖርን ፣የዲሞክራሲና የዜጐች መብትን መረጋገጣቸወን ማሳየት ይኖርበታል ።

ህዝቡ በሀገሩ ጉዳይ የማይመክርበት ፣ የማይወስንበት ሁኔታ ካለ ትርጉም የሚሰጥ ልማት ሊሆን አይችልም ልማት ማለት የጥቂቶቹን ከርስ ሞልቶ ማደር ብቻ ሳይሆን በህዝብ ውስጥ የመንፈስ እርካታም ጭምር ሲኖርና የሀገር ዜግነትና ባለቤትነት ሲገለጽ ብቻ ነው  ።

ይህ ከዚህ በላይ በአጭሩ ጠቅለል አድርጌ በዝርዝር የጠቀስኩት ሐሳብ የህወሃት / ኢህአዴግን ፖሊሲዎችን ምንነት ቁልጭ አድርጎ ከሚያሳየን መገለጫዎቹ አንኳር ነጥቦች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው በቀጣዩ ጽሁፌ ተመልሼ እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት ።

ኢትዬጵያ ለዘላለም
ትኑር !!

1.http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46772

2.http://ethioexplorer.com/2015/09/19/%E1%8B%9C%E1%8C%90%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%8A%A8%E1%89%80%E1%8B%AB%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%88%9B%E1%8D%88%E1%8A%93%E1%89%80%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%88%8D%E1%88%9B%E1%89%B3%E1%8B%8A%E1%8A%90%E1%89%B5/
3.

No comments:

Post a Comment