Sunday, March 31, 2013


በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ! 

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻና የበቀል ስሜት እንጂGinbot 7 press release in Amharic የኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ከወጣትነት ግዜያቸዉ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ጥርሳቸዉን የነከሱ የወያኔ መስራቾች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለቻዉ ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም።
የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ያከበረዉ ወይም የኤኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅሙን ያስጠበቀለት ብሔረሰብ ባይኖርም በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን የወያኔ ዘረኞች የአማራን ህዝብ ከተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ ነጥለዉ ለማጥቃትና የስነ ልቦና ዘይቤውን ለመስበር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። በአጠቃላይ የወያኔ ዘረኛ ባለስልጣኖች አማራውን በተከታታይ ሲዘልፉ ቆይተዋል፤አዋርደው አስረዋል፤ ከአገር እንዲሰደድ አድረገዋል፤ አፈናቅለዋል ገድለዋል። ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ብቻ አሶሳ፤ በደኖና አርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል።
ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡና እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። የወያኔ ባለስልጣኖችና በየአካባቢዉ የኮለኮሏቸዉ ምስለኔዎች አካባቢዉን በግድ እንዲለቅ የተደረገ ህግ አክባሪ ዜጋ የለም፤ የተባረሩት ህግ የጣሱ ግለሰቦች ብቻ ናቸው፣ በማለት አሳፋሪ ድርጊታቸዉን ለመደበቅ ሲሞክሩ ታይተዋል። ሆኖም ከጉራ ፈርዳና ከአካባቢዉ ተፈናቅለዉ ወደ መጣችሁበት አካባቢ ተመለሱ ተብለው በየሜዳው ያለምግብ፣ ውኃና፤መጠለያ የተበተኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ለወገኖቻቸውና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ የድረሱልን ጩኸት ሲያሰሙ መሰንበታቸዉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነዉ።
ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል። ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ተደርገዋል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ቢኖር በገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ዉስጥ አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ዝም ብሎ መመልከቱ ብቻ ሳይሆን ባለፈው አመት ከጉራ ፈርዳ ዘንድሮ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባረሩ እየወጡ ባሉ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ወንጀል ላይ ተባባሪ መሆኑን አሳይቷል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያደረሰውንና በማድረስ ላይ ያለውን ይህ ነዉ የማይባል ግፍና መከራ ከዚህ ቀደም እንዳደረገዉ ሁሉ አሁንም አጥብቆ ያወግዛል። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ በዚህ በኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የትግል ምእራፍ ውስጥ በደም የተቀባ፣ የቀለመ አኩሪ ታሪክ ያለውን የአማራውን ህዝብ መልሶ መላልሶ የሚያጠቃውና ይህንን ታላቅ ህዝብ ከየቦታዉ የሚያፈናቅለው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከአማራዉ ህዝብ ጋር ብቻ በማያያዝ አገራችንን ለማዳከምና አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላዉ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና መከራ “ምን አገባኝ” ብሎ እንዲመለከት ለማድረግ ባለው እጅግ አደገኛ ዕቅድ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ በጥብቅ ያሳስባል።
ከዚህም በተጨማሪ በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ ያላችሁ ወንጀለኞችና ተባባሪዎች፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።
በአማራው የደረሰው ጥቃት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጥቃት ነው እንላለን። ግንቦት ሰባት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበትን ነጻነት የምናስጠብቀው በህብረት ነውና ወያኔ በአሁኑ ግዜ በአማራው ወገናችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ፤ መከራና መፈናቀል በእያንዳንዳችን ላይ እንደደረሰ በመቁጠር ይህንን ግፍ በመፈጸም የማይሰለቸውን ዘረኛ አገዛዝ በተባበረ ህዝባዊ ትግል ከአገራችን ለማስወገድ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል ጥሪ ያስተላልፋል።
    Posted By.Dawit Demelash

አንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ወያኔ





Saturday, March 30, 2013


     ለማያዉቅሽ ታጠኚ

ማስረሻ መኮንን ነኝ ከቃሊቲ
እንደምን ሰነበታችሁ ግንቦቶች - እቺ ደብዳቤዬ እንደምትደርሳችሁ አልጠረጠርም፤ ካልደረሰችም እርግጠኛ ነኝ እናንተዉ ፈልጋችሁ ታገኟታላችሁ። ለመሆኑ እንደምን ከረማችሁ? ዘረኞቹ የወያኔ ካድሬዎች በዚያ ሰሞን ዉጭ አገር ካሉ ሽብርተኞች ጋር ትገናኛለህ ብለዉ ዘብጥያ ወርዉረዉኝ ይሄዉና ሳላናግራችሁ ሳታናግሩኝ ድፍን አንድ አመት አለፈን። መቼም የማይለመድ ነገር የለም መታሰርም ኑሮ ሆኖ ይሄዉና እስር ቤቱን ለመድኩት። ደሞስ የወያኔ እስር ቤት ለምን አይለመድ! ባልታሰር የማላገኛቸዉን ጓደኞቼን፤ ምሁራንንና፤ የእስልምናና የክርስትና እምነት ሊቃዉንትን እዚህ እስር ቤት ዉስጥ ነዉ እንዳሰኘኝ የማገኛቸዉ። ለሁሉም ምን አለፈችሁ ምን አነበብክ፤ ምን ጻፍክ፤ ምን አሰብክ፤ ማንን አሳደርክ እያለ የወያኔ ካድሬ በየቀኑ ከሚጨቀጭቀኝ እዚህ የአገሪቱ ምሁርና አዋቂ የበዛበት እስር ቤት ዉስጥ ብኖር ይሻላል ብዬ አትፍቱኝ ብያቸዋለሁ . . . . . . . የሚሰሙኝ ከሆነ!
ግንቦቶች የዛሬዉ ጉዳዬ የእስር ቤት ኑሮዬን መተረክ አይደለም፤ ጉዳዬ ሌላ ነዉ። ግን ስለ ልጅነት ጓደኛዬ ስለ ታሪኩ ሳልነግራችሁ ባልፍ ቅር ይለኛል። ታሪኩ የወያኔን ፖሊሶች ግልምጫ ከምንም ሳይቆጥር ሁሌ እየመጣ የሚጠይቀኝ የልጅነት ጓደኛዬ ነዉ። ታሪኩ የሚበላ ምግብ ብቻ ሳይሆን የሚነበብ ጸሁፍም ይዞልኝ ይመጣል፤ እኔም የጻፉኩትን ለአንባቢ ያደርስልኛል። የሚገርመዉ ታሪኩ የኮድ ስሙ ሳይሆን እናቱ ያወጡለት ትክክኛ ስሙ ነዉ፤ ስሙን ልደብቅለት ስሞክር . . . ስሜን ይወቁት ምን ያደርጉኛል ብለህ ነዉ . . . . አንተዉጋ ነዉኮ የሚያመጡኝ. . . . . . ደግሞስ በየቀኑ ከምመላለስ አንዱኑ አብሬህ ብታሰር ይሻላል የሚል ቆራጥ ሰዉ ነዉ ታሪኩ።
ጓደኛዬ ታሪኩ በዚህ ሳምንት ይዞልኝ የመጣዉ መጣጥፍ ገና ገልጬ ሳላየዉ ያ እጅ እጅ ያለኝ የኢህአዴግ አርማ ከሩቁ ታየኝና ቀና ብዬ ምነዉ ታሪኩ አልኩት። አንብብ አለኝና ድምጹ ራቀኝ። ምን ሆነ ብዬ ቀና ብዬ ስመለከተዉ ፖሊሶቹ እየገፈታተሩ ከእንግዳ መቀበያዉ ክፍል አስወጡትና ሳይሰናበተኝ ዝም ብሎ ሄደ። እኔም ወደ መኝታ ክፍሌ ገባሁና መጣጥፉን ማንበብ ጀመርኩ። ታሪኩ ሰጥቶኝ የሄደዉ ወረቀት የሚጀምረዉ የኢህአዴግ 9ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ “በመለስ አስተምህሮዎች፤ ጠንካራ ድርጅትና የልማት ሀይሎች ንቅናቄ ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል ባህርዳር ዉስጥ ይጀምራል እያለ ነዉ። ወረቀቱ ላይ የሰፈረዉ የዉሸት ብዛት እንኳን እኔን አንባቢዉን ጽሁፉን የተሸከመዉን ግዑዙን ወረቀትም የሚቀፍፈዉ ይመስለኛል። ዮሐንስ ወንጌል ላይ የዉሸቶች ሁሉ አባት የተባለዉ ዲያቢሎስ ትዝ አለኝ። እርግጠኛ ነኝ ወያኔ ያኔ ቢኖር ኖሮ ዉሸት ሌላ አባት ይኖረዉ ነበር። በሦስት ገጾች ተቋጥሮ ከተቀመጠዉ የወያኔ የዉሸት ድሪቶ ዉስጥ አይኔ ያረፈዉ “በመለስ አስተምህሮዎች”፤ “ጠንካራ ድርጅት” ና “የልማት ሀይሎች ንቅናቄ” በሚሉ ሦስት ቱባ ቱባ ዉሸቶች ላይ ነበር። የወያኔዎች ነገር አንዳንዴ በጣም ይገርመኛል። ጥጋባቸዉና ትዕቢታቸዉ ሲፈጠሩ ጀምሮ የተደፈነዉን ጀሯቸዉን ጨምሮ ደፍኖታልና የኢትዮጵያን ህዝብ አይሰሙም እንበል . . . . . . ግን እንዴት የክርስትና እምነታችን መሠረት የሆነዉ ትግራይ አፈር ላይ የበቀሉ ሰዎች ፈጣሪያቸዉን አይሰሙም! እግዚአብሔር እኮ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ታግሷቸዉ የገሀዱን አለም የመለስ ዜናዊን አስተምህሮ ብቻ ሳይሆን የአባ ጳዉሎስን የመንፈሳዊ አለም አስተምህሮም ስለተጠየፈ ነዉ ሁለቱንም ሰዎች ተራ በተራ የወሰዳቸዉ። ታድያ መምህሩንና ደቀመዝሙሩን ለሀያሉ እግዚአብሔር ቁጣ ያጋለጠዉን ክፉ አስተምህሮ እንደገና እዚህ ምስኪን ህዝብ ላይ ለመጫን የሚሞከረዉ ለምንድነዉ? ለመሆኑ የመለስ አስተምህሮ ምንድነዉ . . . . . . ስድብ፤ንቀት፤ ጥላቻ፤ ዘረኝነት፤ኢትዮጵያንና ታሪኳን መጥላት፤ አማራን በየሄደበት ማሳደድ፤ የኑሮ ዉድነት፤ ስደት፤ እስር፤ ግድያ፤ የመሬት ቅርምት፤ ብሔራዊ ዉርደት፤ . . . . . . እስኪ ወያኔዎች እናንተ አራሳችሁ ንገሩኝ ምንድነዉ የመለስ ቅርስ ዬቱ ነዉ የመለስ አስተምህሮ?
ግንቦቶች እዚህ ወረቀት ላይ ካነበብኳቸዉ ነገሮች ሁሉ የሰቀጠጠኝና አይኔን ማመን ያቃተኝ . . . . . . . 9ኛዉ የኢህአዴግ ጉባኤ የአገራችን የልማትና የዲሞክራሲ ጉዞ መሐንዲስ የነበሩት ጓድ መለስ ዜናዊ የሚታሰቡበት ጉባኤ ነዉ” የሚለዉን ሳነብብ ነዉ። ሃያ አንድ አመት ሙሉ የመጻፍና የመናገር መብቶችን አፍኖ፤ የሚቃወመዉን እየገደለና በአንድ አናሳ ብሄረሰብ የበላይነት ዙሪያ 90 ሚሊዮን ህዝብን ረግጦ የገዛዉ መለስ ዜናዊን የዲሞክራሲ መሐንዲስ ማለት ወይ ዲሞክራሲን ወይም ምህንድስናን አለዚያም ሁለቱንም አለማወቅ ይመስለኛል። ደግሞም እዉነቱን ለመናገር መለስን የዲሞክራሲ መሐንዲስ ከማለት መንግስቱ ሀ/ማሪያምን የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም አባት ማለት የሚቀል ይመስለኛል . . . . . . . . ትዝ የሚለን ከሆነኮ ኢትዮጵያ ዉስጥ የመጀመሪያዎቹ የክልል መንግስታት መንግስቱ የፈጠራቸዉ የትግራይ ራስ ገዝ፤ የኤርትራ ራስ ገዝ፤ የአሰብ ራስ ገዝና ኦጋዴን ራስ ገዞች ነበሩ።
ለመሆኑ. …. የመለስን ራዕይ ከግቡ ማድረስ ኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ለምን አገሩን ለቅቆ እየተሰደደ በየዉቅያኖሱና በየበረሃዉ የእሳት እራት ሆኖ ይቀራል? እሲኪ ንገሩኝ እናንተ ወያኔዎች ምርጫችን የመለስን ፈለግ መከተል ቢሆን ኖሮ ቁጥሩ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ለምን “ድምጻችን ይሰማ” እያለ በየአደባባዩ በእናንተ ዱላ ይደበደባል? ደግሞስ በየቀኑ ስለማሪያም ስሙኝ እያለ የማትሰሙት የኢትዮጵያ ህዝብ እሱ እናንተን ለምን ይሰማል? እናንተ ወያኔ በአምሳያዉ የፈጠራችሁ የኢህአዴግ ቡችሎች እናንተም ስሙ . . . . . . . እስኪ ምን ይሁን ብሎ ነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የናቀዉን፤ የሰደበዉን፤ ያዋረደዉን፤ የገደለዉንና በዘረኝነት አለንጋ የለበለበዉን ሰዉ ራዕይ ከግቡ ለማድረስ ቃል የሚገባዉ? ወያኔም ሆነ ኢህአዴግ ወይም አግአዚ ጆሮ ካላችሁ ስሙ . . . . . የኢትዮጵያ ህዝብ ቃል የገባዉ እናንተ በፈቃደኝነት ከተነቀላችሁለት ፈቃዳችሁን ለማክበር አለዚያም እሱ እራሱ ነቅሎ ሊያጠፋችሁ ነዉ።
ኢህአዴግ ለ9ኛዉ ጉባኤ ሲዘጋጅ መሪ ቃል ብሎ ካስቀመጣቸዉ ሦስት ትልልቅ የዉሸት ድሪቶዎች ዉስጥ ሁለተኛዉ “ኢህአዴግ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት ነዉ የሚለዉ አባባል ነዉ። ነገሩ “ከቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ”.. . . . እንደሚባለዉ ተረት ሆኖ ነዉ እንጂ ገና ከጧቱ ሲፈጠር ጀምሮ ኢህአዴግ መች ጠንካራ ድርጅት ሆኖ ያዉቃል? የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የሚወክሉትን ህዝብ ብዛትና ያላቸዉን የፖለቲካ ጡንቻ ተገንዝበዉ እንቅስቃሴያቸዉን ከፖለተካ ጡንቻቸዉ ጋር ማገናዘብ ቢችሉ ኖሮ እዉነትም የኢህአዴግ ጠንካራ ድርጅት ተብሎ ሊጠራ ይችል ነበር፤የኛም ትግል ወያኔ የፈጠረዉን ስርአት ለመደምሰስ ሳይሆን እንማንኛዉም በሰለጠኑ አገሮች ዉስጥ እንደሚታየዉ የፖለቲካ ህደት ትግላችን በምርጫ ህዝባዊ ሀላፊነትን ለመቀበል ብቻ ይሆን ነበር።ኢህአዴግ በወያኔ አንጎል የሚያስብ፤ በወያኔ አፍ የሚናገርና የወያኔን መንገድ የሚከተል ተሳቢ ድርጅት በመሆኑ ነዉ ዛሬ አገራችን እጅግ በጣም አደጋኛ ቦታ ላይ የምትገኘዉ።
ደግሞስ ዘረኞቹ የህወሀት መሪዎች የዘረፉትን መካፈል አቅቷቸዉ ሲጣሉ፤የኦህዴድ አባላት በአራት ቡድን ተከፋፍለዉ አንዱ የወያኔ ባሪያ ሆነን እንቀጥል ሲል ሌላዉ ደግሞ ነጻነቱን ለማወጅ እየተዘጋጀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ምኑ ታይቶ ነዉ የህአዴግ ጠንካራ ድርጅት ነዉ የሚባለዉ? የሚንገዳገዱና በዉስጣቸዉ በተነሳ ቅራኔ የተነሳ ለመፍረስ አንድ ሐሙስ የቀራቸዉን ድርጅቶች ያቀፈዉ ኢህአዴግ እንዴት ሆኖ ነዉ ጠንካራ ድርጅት ሊሆን የሚችለዉ?ባለፉት አምስትና ስድስት ወራት በግልጽ እንደተመለከትነዉ ህወሀትና ኦህዴድ እርስ በርሳቸዉና አንዱ ከሌላዉ ጋር በፈጠሩት ከፍተኛ ቅራኔ የተነሳ ሁለቱ ድርጅቶች የረባ ስብሰባ እንኳን ማካሄድ አልቻሉም፤ እንግዲህ ይህ ኢህአዴግ ነዉ ጠንካራ ድርጅት ነዉ ተብሎ የሚነገረዉ።
ይገርማችኋል በዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሁሉም ነገር የተገላቢጦሽ ሆኗል። ዘላን ለክረምት እንደሰራዉ ቤት ለመፍረስ አንድ ሳምንት የቀረዉ ኢህአዴግ ጠንካራ ድርጅት ተብሎ ይወደሳል፤ የኢትዮጵያ ምሁር መዋያዉ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ቀርቶ ቃሊቲ ሆኗል፤ ጋዜጠኛም መደበኛ ስራዉ መጻፍ ሳይሆን መታሰር ሆኗል።ድምጻችን ይሰማ ብሎ የጮኸ ሽብርተኛ ተብሎ ይታሰራል፤ በምሽት በር እየሰበረ ህዝብን የሚያሸብር ጀግና ተብሎ ይሞገሳል። እንግዲህ ግንቦቶች የወያኔ ጉድ ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል? እንዲያዉ በደፈናዉ እነዚህ ዘረኞች አገራችንን ጉድ በጉድ አደረጓት ማለቱ የሚበቃ ይመስለኛል።
የጋምቤላን ገበሬ መሬት ለትግራይ ባለሀብት ሰጥተዉ ጋምቤላዉ መሬቴን ሲል “ግንቦት ሰባት” ነህ ብለዉ ይጨፈጭፉታል። ፋሺስት ግራዚያኒ መታሰቢያ ሐዉልት አያስፈልገዉም ብለዉ የተቃወሙ ኢትዮጵያዉያንን አስረዉ መረጃ ካልሰጣችሁንና የብሔር ማንነታችሁን ካልተናገራችሁ አትፈቱም እያሉ ይደበድቧቸዋ። የሚገርመዉ ነጮቹ ፋሺስቶች እንኳን ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያዉያንን በአንድ ጀምበር ሲጨፈጭፉ ያልጠየቁትን የብሔረ ማንነት ዛሬ ጥቁሮቹ ፋሺስቶች አባቶቻቸዉን የጨፈጨፈ ሰዉ እንዴት መታሰቢይ ይሰራለታል ብለዉ የተቃወሙ ኢትዮጵያዉያንን አስረዉ የዬትኛዉ ብሔር አባል ነህ ብለዉ መጠየቃቸዉ በእርግጥም ማርሻል ግራዚያኒ ሀዉልት ሳይሆን የቆመለት እሱ እራሱ መልኩን ለዉጦ የመጣ ነዉ የሚመስለዉ።
እንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ልብ ብለህ ነገሮችን አስተዉል . . . . . ኢነዚህ ዳግማዊ ግራዚያኒዎች ናቸዉ በየክልሉ በአምሳያቸዉ የፈጠሯቸዉን አሻንጉሊቶች አቅፈዉና እራሳቸዉን ኢህአዴግ ብለዉ ሰይመዉ ከዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ድረስ ጉባኤ፤ እድገት፤ ህዳሴ፤የመለስ ራዕይና ትራንስፎርሜሺን እያሉ እያደነቆሩህ የሚከርሙት። እነዚህ ከመልካም አስተዳደር ጋር ሆድና ጀርባ የሆኑ ጉዶች ናቸዉ ሰልመልካም አስተዳደር ለሰብኩህ የሚሞክሩት። ለኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ኢህአዴግ ብዙ የሚነገረዉ ያለ አይመስለኝም . . . . . ሃያ አንድ አመት ሙሉ እንደቋጥኝ ተጭነዉበት ጀርባዉን አጉብጦታልና ያዉቀዋል። ኢህአዴግ የራሱ የሆነ ማንነት ያለዉ እዉን የሆነ ድርጅት ሳይሆን ህወሀት የራሱን እዉነተኛ ማንነት ለመሸፈን እንደብረት ቀጥቅጦ የሰራዉ የማታለያ ሽፋን ነዉ። ለዚህም ነዉ በድምሩ 439 የፓርላማ ወንበር ያላቸዉ ሦስቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች 38 ወንበር ላለዉ ለህወሀት እየሰገዱ የሚኖሩት። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አህያ ሜዳ ለሜዳ ሳሯን እየጋጠች ብትበላ ወይም እንደሰዉ ልጅ ምግብ ተሰርቶላት በሳህን ብትበላ አህያ መባሏ አይቀርም . . . . . . ኢህአዴግም እንደዚሁ ነዉ። ዘጠኝ ግዜ ቀርቶ ዘጠና ዘጠኝ ግዜ ጉባኤ እያለ ቢሰበሰብና የራሱን ብጤ ደካማና አድር ባይ ምሁራንን በየጉባኤዉ ቢያሳትፍ አህያ ለመሸከም እንደተፈጠረች ሁሉ ኢህአዴግም እንደጋሪ ለመጎተት የተፈጠረ ድርጅት ነዉና ኢህአዴግነቱን አይለቅም።ከዛሬ ጀምሮ እስከማክሰኞ ድረስ በቴሌቪዥን የምንመለከተዉ ድራማ አላማዉ አንድና አንድ ብቻ ነዉ . . . . . . እሱም አስቀያሚዉን ኢህአዴግ ሊፕስቲክና የፊት ማሳመሪያ ቅባት እየቀቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳየት ነዉ . . . .መቼም የወያኔ ነገር ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ እንደሚሉት ሆኖ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብማ ኢህአዴግ ገና ጉባኤዉን ሳይጀምር ነዉ .. . . . . ለማያዉቅሽ ታጠኚ ብሎ የተረተበት።
                     Posted By.Dawit Demelash

ኢህአዴግን “አድርባይ” አመራሮች አስግተውታል

አባላት “አድርባይነት የመመልመያ መስፈርት ነው” አሉ!!

eprdf 9th meeting
ኢህአዴግ አመራሮቹን “አድርባይነት የተጠናወታቸው” ሲል ፈረጀ። የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት የሆነውን ፍረጃ የሰሙ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንደሆነ አመለከቱ።
በባህር ዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረ ጋዜጠኛ በምሥጢር የላከው ዜና “አድርባይነት” ኢህአዴግን በሚፈታተን ደረጃ መስፋፋቱ መገለጹ አብዛኞችን የድርጅቱን አባላትን አስገርሟል።
ኢህአዴግን የፈጠረውና ከላይ ሆኖ የሚመራው ህወሃት “ነጻ” አመለካከት የማይወድ፣ የነጻ አስተሳሰብ ባህል የሌለው፣ ራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶችን፣ ፓርቲዎችንና ማህበራትን አጥብቆ የሚጠላ፣ ሁሉም ለሱ እያጎበደዱ በሚሰፈርላቸው ቀለብ እንዲኖሩ ሌት ከቀን የሚሰራ መሆኑ እየታወቀ ማንን? ለምንና እንዴት አድርባይ በሚል እንደሚፈርጅ አብዛኞች ግራ መጋባታቸውን የደረሰን ዜና ያመለክታል።
ህወሃት በፈለፈላቸው ድርጅቶችና የአፈና ተቋማቱ አማካኝነት በሂደት የኢትዮጵያን አብዛኛውን ህዝብ “አጎብዳጅ” የማድረግና “አድርባይ” ሆነው የሚኖሩትን ቁጥር ማብዛት ዋናው ስትራቴጂው እንደሆነ እየታወቀ “አድርባይነት” እንዴት ለድርጅቱ በሽታ ሊሆን እንደቻለ ያልገባቸው እንዳሉት “አድርባይነት አስጊ ደረጃ ከደረሰ ህወሃት የለፋበትን ያገኘና በስኬት ጎዳና ላይ ለመሆኑ ማሳያ ነውና ስጋት ሊገባው አይገባም” የሚል የለበጣ አስተያየት መስጠታቸው ተጠቁሟል።
በስብሰባው ላይ በይፋ አስተያየት ከሰጡት መካከል አቶ አባይ ጸሐዬ ይጠቀሳሉ። በህወሃት የመከፋፈል ዘመን ቀደም ሲል ከውህዳኑ ጋር ያበሩ መስለው ሁለት ሳንጃ በመያዝ የተጫወቱት አቶ አባይ አሁን አድርባይ ተብሎ የተፈረጀው የኢህአዴግ አባል በሙሉ ወደ መካከለኛ አመራርነት ከተሸጋገረ አደጋው ከፍተኛ እንደሚሆን ተናግረዋል። ቀደም ሲል አባሉ በተመለመለበት ደረጃ ተግባሩን ሲያከናውን ባግባቡ አለመመዘኑ የአደጋው መነሻ ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል።
ኢህአዴግ አባሎቹ “አድርባይና አጎብዳጅ” እንደሆኑበት የገለጸው ስትራቴጂዎችን የመፈጸም ችግር ስላጋጠመው ነው። በጉባኤው ኢህአዴግን ያስደነገጠው ጉዳይ “አደገ” የተባለው የሰብል ምርት ሪፖርት ጉዳይ በዋናነት የሚጠቀስ ነው። አቶ በረከት በቀጥታ ተጠያቂ ያደረጉት ከፍተኛ ደረጃ ያለውን አመራር ነው። እንደሳቸው አባባል ታላቅ ንቅናቄ ሊፈጥር የሚችል የልማት ሰራዊት ያልተገነባበት ምክንያት ሊገመገም ይገባል።
በአሁኑ ወቅት ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ የተመዘገቡ አባላትን ያቀፈውና የቻይናን ኮሙኒስት ፓርቲ ሞዴል ወርሶ “በመለስ ውርስ ወደፊት” እያለ የሚጓዘው ኢህአዴግ አባላቱ “ፊት እያዩ የሚደፉ” መሆናቸው አደጋ መሆኑ ታምኖ መፍትሄ የተበጀለት ቢሆንም የቁርጠኛነትና በራስ ያለመተማመን ችግሩ ሰፊ ስለሆነ በቀላሉ ሊቀረፍ የሚችል እንዳልሆነ ተመልክቷል።
በተመሳሳይ ጉዳይ ሪፖርተር ባቀረበው ዜና አቶ ስዩም መስፍን “የራሱን የውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሕይወት ያላስጠበቀ ካድሬ ወይም አመራር የሕዝቡን መብትና ዲሞክራሲ ሊያስጠብቅ አይችልም። ራሱ ነፃ ያልወጣና እየተሸማቀቀ የሚኖር ካድሬ ወይም አመራር የሕዝብን መብትና ጥቅም አስከብራለሁ ብሎ መንቀሳቀስ አይችልም” በማለት አድርባይነትን የፓርቲው አባላት እንዲታገሉ ማሳሰባቸውን አስነብቧል።
ወ/ሮ አዜብ በኢቲቪ አማካይነት በዚሁ ጉዳይ ሲነገሩ እንደተሰማው ችግሩ የቁርጠኛነት ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል። “የሚባለው” በማለት የሰሙት መሆኑንን በመግለጽ ወ/ሮ አዜብ እንዳሉት “ለእንጀራና ለምደባ” ሲባል አድርባይነት መንገሱን ገልጸዋል። “ያሉት ክፍተቶች ቀላል አይደሉም” በማለት ማብራሪያቸው የሚያስከትሉት ወ/ሮ አዜብ፣ “ራሳችንን ማጽዳት፣ ግለኝነትን መታገል፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን መዋጋት ያስፈልጋል” ካሉ በኋላ አስገራሚ አስተያየት ሰንዝረዋል።
“ቀናነት” እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ “ስትራቴጂው አለ። ሲፈጸምም አይተነዋል” አሉ። በዚህ ንግግራቸው ባለቤታቸውን ያስታወሱት ወ/ሮ አዜብ “መቻቻልና አድርባይነት መጥፋት አለበት” የሚል መፈክር አሰምተዋል። በዚህ አላበቁም “እስከመጨረሻው፣ ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን፣ በቁርጠኛነት የሚያደናቅፈንን መቻቻልና አድርባይነት ከመድረክ ላይ መጥለፍ መቻል አለብን” ብለዋል። “መድረክ” ሲሉ የጠሩትን ግን አላብራሩም።
የኢህአዴግ ጉባኤ ሲጠናቀቅ በተለይም የእህል ምርት በሚገባውና በተቀመጠበት ደረጃ ማደጉ ቀርቶ አፈጻጸሙ ደካማ መሆኑ እንዳሰጋው፤ ምናልባትም የከፋ ድርቅ ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት ህዝብን እንዳያነሳሳበት መፍራቱን ምንጮች አመልክተዋል።
የመላው ኢትዮጵያዊ ገቢ መጨመር እንዳለበት አቋም ቢያዝም በተለይም ጡረተኞችን፣ የቤት አበል የሚቀበሉ ቤተሰቦችን፣ እጅግ አነስተኛ በሆነ የደሞዝ ጣሪያ የተቀጠሩትንና በቀን ስራ የተሰማሩትን ስለማካተቱ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። በኢትዮጵያ በደርግ ጊዜ ቤት ተወርሶባቸው በ30 እና 40 ብር አበል ላለፉት አርባ ዓመታት ተረስተው የኖሩ ዜጎች ቁጥር ቀልል የሚባል አይደለም። እነዚህ ወገኖች ለአፈር ግብር እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ከሚያገኙት አበል በላይ መሆኑም ይታወቃል። አንዳንድ ቦታ ተከራዮች ከባለቤቶቹ (በውርስ ንብረታቸው ከተወሰደባቸው) በላይ ተከራይቶ በማከራየት ተጠቃሚ ናቸው። ዜናውን የላከልን እንዳለው ያገባናል የሚሉ ሁሉ አስቀድመው በዚህ ጉዳይ ላይ ከህዝብ ጋር በመነጋገር እንዲሰሩ አሳስበዋል። (ፎቶ: Ethiopian Herald)

    Posted By.Dawit Demelash

Thursday, March 28, 2013


ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?

ethiopia

Tuesday, March 26, 2013

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ


የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።
ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በዘረኝነት ገመድ አስሮ እየረገጠ የሚገዛዉ ወያኔ ለዚህ የበቃዉ በዘረኝነትና በጥላቻ አነሳስቶ ያሰታጠቃቸዉ ገበሬዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ነዉ ያለዉ ይሄዉ ህዝባዊ ኃይል ሠላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከእነዚህ የቀን ጅቦች ለማላቀቅና አገራችንን የእኩሎች አገር ለማድረግ ማንኛዉንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የፍትህ፤የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ግቡን እንዲመታ የመጀመሪያዉን እርምጃ የወሰደዉና ትግሉ የሚፈልገዉን የደም መስዋዕትነት ለመክፈል የትግሉ ግንባር የመጀመሪያዉ ደጃፍ ላይ የተሰለፈዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ካሁን በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔን ዘረኝነት፤ዝርፍያ፤ጥላቻና ንቀት ለማስቆም መፍትሄዉ ከአገር እየተሰደዱ በየባህሩና በየበረሀዉ መሞት ሳይሆን ለስደታችን፤ ለመዋረዳችንና ለመረገጣችን ቀንደኛ ምክንያት የሆነዉን የወያኔ ስርአት እዝያዉ አገር ቤት ዉስጥ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ብቻ ነዉ ብሏል።
የወያኔ እህአዴግ ዘመን አብቅቷል፤ከአሁን በኋላ ዘመኑ የኛ የኢትዮጵያዉያን ነዉ ያለዉ የግንቦት ሰባት ዝብባዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ይህንን የኛ የሆነዉን ዘመን እዉን የምናደርገዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ከዘረኝነት ነጻ የምናወጣዉ እንደአንድ ሰዉ ቆመን በጋራ ስንታገል ነዉ እንጂ የአገር ማዳኑንና የመስዋዕትነቱን አደራ ለተወሰኑ ወገኖች ብቻ በመተዉ አይደለም ብሏል። በመቀጠልም ወያኔን ፊት ለፊት ተፋልሞ ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአባቶቹ በአደራ የተረከባትን ኢትዮጵያን ለልጆቹ ለማስተላለፍ የሚናፍቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከዛሬ በኋላ ዬት ሄጄ ወያኔን ልታገል የሚል ስጋት እንዳይሰማዉ አሳስቧል።ባለፈዉ ታህሳስ ወር እራሱን ለህዝብ ይፋ ይደረገዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ አያሌ ኢትዮጵያዉያን በየቀኑ እየተቀላቀሉት ሲሆን ይህንን የህዝብ ተገንና አለኝታ የሆነ ኃይል በመቀላቀል የአዲስቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ለመሆን የምትፈልጉ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዉያን ህዝባዊ ኃይሉ በተከታታይ ለሚያወጣቸዉ መግለጫዎችና ህዝባዊ ጥሪዎች ምላሽ በመስጠት እንዲትተባበሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ጥሪዉን ያስተላልፋል።

       Posted By.Dawit Demelash

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ”

March 25, 2013 1:04 pm
DSCN0070-አቶ ታዲዎስ ታንቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ ኢትዮጵያውያን ነው፡፡
በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድ ወሰንን፡፡
ተቃወቅሞውን ለማቅረብ ያነሳሳችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን ነበር?
ብዙውን ጊዜ እኔ በጋዜጦች ስለ አርበኞች ታሪክ ያነበብኩትንና ያወቅሁትን እፅፋለሁ፣ እመረምራለሁ፡፡ የጣሊያኑ ፋሽስት ግራዚያኒ ሀገራችንን በመውረር በአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አሰቃቂ እንደነበር ስለተረዳሁ፤ ያ ሲቆጨኝ ደግሞ አሁን በጣሊያን ሀገር ለእሱ ሙዚየምና ሐውልት የመሰራቱን ወሬ ከኢንተርኔት ምንጮች ስላየሁ በጣም ተናድጄ እንደውም ተቃውሞ ማሰማት አለብን ብዬ ተነሳሁ፡፡ በኋላ ደግሞ እኛም የአንተ ዓይነት ሐሳብ ነበረን ብለው የባለ ዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር አነጋገሩን፡፡ ከዛ በመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንስራ የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያት ሶስቱ አካላት በጋራ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ጣሊያን ሀገር ጨረቃም ላይ ቢሆን ሀውልት እንዲሰራ አንፈቅደም፡፡
በጊዜው ሩዶልፍ ግራዚያኒ ወንጀለኛ በመሆኑ የነበረው ፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተገፎ ከወታደርነቱ ተባሮ በጦር ወንጀል ተከሶ 19 ዓመት ተፈርዶበት ቅጣቱን ሳይጨርስ ከእስር ቢለቀቅም እ.አ.አ. በ1955 ዓ.ም. ሞቷል፡፡ ታዲያ ይህ በጊዜው ወንጀለኛ ለተባለው ሰው ሐውልትም ሆነ የመታሰቢያ ሙዚየም ማሰራት ኢትዮጵየውያንን መናቅና የአባቶቻችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ ሊሰራለት አይገባም፤ እንደውም ለፈፀመው እልቂት ጣሊያን በቂ ካሳ ስላልከፈለች ካሳ መክፈልና በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይገባታል የሚል አቋም ይዘን ነው የወጣነው፡፡ ስለዚህ ግራዚያኒ ከነ አዳፋ ታሪኩ ሌላው እንዳይደግም ሲወሳ መኖር አለበት እንጂ እንደ ጀግና ሐውልት ሊሰራለት፣ሊወደስና ሊመሰገን አይገባም እንላለን፡፡
በወቅቱ የደረስው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይቻላል?
በወቅቱ ግራዚያኒ በፊርማው በግፍ ኢትዮጵያውያንን ያስጨፈጨፋቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ከነደብዳቤው አለ፤ የዚህ ቅጂ እኔም ጋር አለ ይታወቃል፡፡ በተለይ የካቲት 12-14 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን በግፍ አዲስ አበባ ላይ እራሱ ግራዚያኒ አስጨፍጨፏል፡፡ ከ250 በላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ መነኮሳትን አስጨፍጭፏል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በ1938 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ያቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው 760,300 ሺህ ዜጎች ወዲያው ሲገደሉ 525,000 ደግሞ ከነቤት ንብረታቸው እንዲቃጠሉ ተደርጎ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሁለት ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው መነኮሳት ተገድለዋል፣ በርካታ ቅርሶች ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡ በርግጥ ከተዘረፉ ቅርሶቻችን መካከል እስካሁን የተመለሰው የአክሱም ሐውልት ብቻ ነው፤ ሌሎቹ ግን አሁንም እዛው ናቸው፤ ሊመለሱልንም ይገባል፡፡ ከዛ ውጭ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶች በወቅቱ ተዘርፈው ተወስደዋል፤ 7 ሺህ ግመሎችም ተገድለውብናል፡፡ ይህም በሰነድ በተደገፈ ማስረጃ ለዓለም አቀፉ የሰላም ጉባዔ የቀረበ ነው፡፡ በወቅቱ ሰነድ ያልቀረበባቸውና ሰፊ ጥናቶች ሊደረግባቸው የሚገቡ በርካታ ጥፋቶች ተፈፅመዋል፡፡
ይህንን ተቃውሞ በዋነኝነት ማቅረብ የነበረበት መንግስት ነበር የሚሉ ወገኖች አሉ፤ እርስዎስ ምን ይላሉ?
እኔም እስማማለሁ፤ ነገር ግን መንግስት ማዘጋጀት ካልቻለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማዘጋጀት ይችላል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ መንግስት ተቃውሞ ያላቀረበው ከጣሊያን የሚያገኘው ዕርዳታ ይቀርብኛል በሚል ይመስለኛል፡፡ እኔ እስከማውቀው ይሄ መንግስት ዕለታዊና የፖለቲካ ገበያ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ወደፊት ትውልድ የሚኮራበትን ስራ የመስራት ዓላማ የለውም
፡፡ ከዚህ በፊት የቀደሙ አባቶቻችን የሰሩትን በጎ ታሪኮች ሲያንቋሽሽ የኖረ መንግስት ስለሆነ እንዲህ ዓይነት የአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ታሪክና ክብር የሚያስጠብቅ ስራ ይሰራል ብዬ አላስብም፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው፣ ብሔራዊ ስሜትን የጠበቀ ህዝባዊ መንግስት ቢሆን ኖሮ ህዝቡን አስተባብሮ ይሄንን ስራ በቀዳሚነት መስራት የነበረበት እሱ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያደርግም ዜጎች ይህንን ሰልፍ የማድረግ መብት ስላላቸው እኛም ሰልፉን አድርገናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሀውልት ግንባታውን አለመቃወሙ ምን ያስረዳናል?
ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በእጅ አዙር ለሀውልት ግንባታው እውቅና እንደሰጠ ይቆጠራል፤ ይህንን እኔም አምናለሁ፡፡ ከዚህም በላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ ናቸው፡፡
እንደውም ነፃነታችንን ባወጅንበት ሁለት ዓመት ሳይሞላ በአርበኞች ላይ ጦርነት የከፈቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለግራዚያኒ የጀግና ሐውልት መሰራቱን ባይቃወሙ አይገርመኝም፤ ምክንያቱም እነሱ የማን ልጆች ናቸው? እስኪ በስልጣን ላይ ካሉት (ከኢህአዴግ) መካከል ለሀገሩ እና ለወገኑ ብሔራዊ ስሜት፣ ነፃነትና ክብር የተዋጋ የአርበኛ ልጅ አንድ ሰው ካለ ንገረኝ? አንድም ሰው የለም፡፡ ስለዚህ የባንዳ ልጅ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ እውቅና በመስጠት ድጋፍ ቢያደርጉ አያስደንቀኝም፡፡
እናንተ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረጋችሁ አንድ ቀን በፊት መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ክስተት በሰልፉ ወቅት እስር እንደሚኖር አልጠቆማችሁም?
እሱን አውቀንም ነው ሰልፍ የወጣነው፡፡ አንድ ቀን አስቀድሞ ሌሎች ቢታሰሩም መውጣት አለብን ብለን ነው የወጣነው፤ እኛም ብንታሰር ሌሎችም እንደሚወጡ እናውቃለን፡፡ ችግር ይፈጠራል ብለን አልተውንም ፤መተውም የለብንም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የሀገርና የወገን ጉዳይ ነውና፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰልፉ ላይ የተገኙትን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
የታሰራችሁት ምን ወንጀል ሰርታችኋል ተብላችሁ ነው?
ፍቃድ አልጠየቃችሁም ፣ አላስፈቀዳችሁም በሚል ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ በነበሩ የአጼ ኃይለስላሴ፣ በደርግ ዘመንም ሆነ አሁንም በወያኔ አገዛዝ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ፈቃድ ይጠየቃል የሚል የተፃፈ ህገመንግስትም ሆነ አዋጅ አልነበረም፤የለምም፡፡ ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናደርግ ማሳወቅና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ ማድረግ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አይደለም፡፡ ይህንንም ለእኛ ጥቅም እንጂ እነሱን ለማስደሰት አይደልም፡፡ እኛ ደግሞ የሀገሪቱን የተፃፈ ህግ ተከትለን ሰልፉን ከማድረጋችን 10 ቀናት አስቀድመን አሳውቀናል፡፡
ኢትዮጵያውያንን በግፍ ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ የተሰራለትን ሐውልት በመቃወማችሁ በኢትዮጵያ መንግስት መታሰራችሁ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ?
ለእኛ የበለጠ የተነሳሽነት ስሜት ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዩንም አጠናክረን እንድንሄድ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ሆኖናል፡፡
ከእስር ሲለቋችሁ ምን ብለው ነው?
ምንም ሳይሉን ለሁለት ሰው አንዳንድ ዋስ በማስጠራት ለቀውናል፡፡ ምክንያቱን ግን አልነገሩንም፤አላወቅንም፡፡ ከዛ ስትፈለጉ ትመጣላችሁ ብለው በዋስ ለቀውናል፡፡
በታሰራችሁበት ወቅትስ የገጠማችሁ ችግር አለ?
በርግጥ እኔ ላይ ድብደባ አልፈፀሙም እንጂ ተመትተው ፊታቸው በተለይም አፋቸው አካባቢ የደማ ወጣት አይቻለሁ፡፡ ፊታቸው ያባበጠ ወጣቶችንም አይቻለሁ፡፡ ሌሎችንም ወጣቶች እንደደበደቧቸውም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ደህንነቶች ማታ መጥተው በግል እያስጠሩ በቢሮ ያናግሩ ነበር፡፡ ስራው ግን የፖሊሶች እንጂ የደህንነቶች አልነበረም፡፡
በታሰርንበት ዕለት ያለምግብና ውሃ ቀን ሙሉ እንድንውል ተደርገናል፡፡ በተለይ እስር ቤቱን ስቃይ አራዳ ፖሊስ መምሪያና ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ያለውን ስታይ ዕቃ ለማስቀመጥ ሆነ ለሌሎች እንሰሳቶች ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዲቆዩበት አይመችም፡፡ እስር ቤቱን ስታይ በጣም ያሳዝናል፤ እዛ የገቡ እኮ ጤነኛ ሆነው የመውጣታቸው ዕድል እራሱ አነስተኛ ነው፤ለበሽታ የሚያጋልጡ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ብቻ በጣም ያሳዝናል፡፡
ይሄ ደግሞ የወንበዴ ስራ ነው፤ ይሄንን መንግስት ማረም አለበት፡፡ ሌላው መርማሪ ፖሊሶችና ደህንነቶች ያልተገቡና ከእስሩ ጋር የማይገናኙ የግል ህይወትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፣ የኢ-ሜይል የይለፍ ቃል ይጠይቃሉ፣…ብቻ ብዙ ነው፡፡ በግል እኔን ደግሞ ፊታቸውን በኮፊያ የሸፈኑና ጥቁር መነፅር ያደረጉ ደህንነቶች ዋስ ጠርቼ ከወጣሁ በኋላ አንተ የአርበኞችን ታሪክ እያነሳሳህ ወጣቶችን እያነሳሳህ ስለሆነ ብታርፍ ይሻልሃል፤ በግል ልናናግርህ እንፈልጋለን እያሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ እኔ ግን በህጋዊ ደብዳቤ ያውም ያመንኩበት ካልሆነ ብትጠሩኝ አልመጣም፤ አላናግርም ብያለሁ፡፡
ከዚህ በኋለስ ይህን ተቃውሞ ለመቀጠልስ እቅዱ አላችሁ?
አዎ አለን፡፡ ይህ ተቃውሞ ምላሽ አግኝቶ ያሰብነው እስኪሳካ እንቀጥላለን፡፡ ነገር ግን ዝርዝር ሁኔታውን በተመለከተ እያጠናን ስለሆነ ወደፊት ሀገር ውስጥ ያለነው ውጭ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመመካከር ምን መልክ መያዝ እንዳለበት ስንወስን ይፋ እናደርጋለን፡፡
በመጨረሻም የሚሉት ነገር ካለ ዕድሉን ልስጥዎት
ህዝቡ ዓላማችን ከግብ እንዲደርስ የተለመደ ድጋፉን ከመስጠት ወደ ኋላ እንዳይል አደራ እላለሁ፡፡

     Posted By..Dawit Demelash

Monday, March 25, 2013

ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ የተሰጠ መግለጫ

london church
ቀን፤ 21/03/2013
ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤ እንዲሁም በUK እና በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሁሉ።
የተቀበሉትን የክህነት ኃላፊነት ጠብቀው በንጽሕና በመቆም እግዚአብሔርንና ሰውን ከማገልገል ይልቅ ሥጋዊ ጥቅምን አስቀድመው የተነሱ ጥቂት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ካህናት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና በምእመኑ መካከል ጸብና ጥላቻ ቀስቅሰው ሁከት እንዲሰፍን በማድረግ ባለፈው ሳምንት ለንደን ወደ ሚገኘው የኢህአዲግ መንግሥት ኤምባሲ በመሄድ ቤተ ክርስቲያንን ያህል ነገር እንደ ግል ንብረት ለማስረከብ እንፈልጋለን በማለት ከጠየቁ በኋላ ከዛ በማስከተል ቤተ ክርስቲያኗን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በመባል በኢህአዲግ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ለንደን ላይ ለተቋቋመው አካል አሳልፎ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደርና ንብረት ለማስረከብ በድርድር ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ይህ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት (ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH DIOCESE OF NORTH WEST EUROPE) በሚል መጠሪያ የተቋቋመው ከ11 November 2011ጀምሮ ሲሆን በቻሪቲ ቁጥር 1144634 መሠረት በቻሪቲ ኮሚሽን ተመዝግቦ የሚገኝ ነው።
የዚህ ለሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ተብሎ የተቋቋመ ሀገር ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ አዕላፍ ተወልደ ገብሩ ሲሆኑ፤ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ደግሞ አቡነ እንጦስ የተባሉ አባ ጳውሎስ በህይወት ሳሉ በጎሳና በመንደር ልጅነት መርጠው ጵጵስና በመሾም ወደ ለንደን የላኳቸው ናቸው። በዚሁ ሃገረ ስብከት ውስጥ በትረስቲነት (Trustees) ሆነው የተዋቀሩት ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2005 ዓ/ም ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ጥለው በመሄድ ሌላ ቤተ ክርስቲያናትን የመሠረቱ ሰዎች ናቸው።
ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለንደን ላይ ከተመሠረተች 40 ዓመታትን ያስቆጠረች ሲሆን በዚህ ረጅም የስደት ታሪኳ ወቅት ካለፈው ከደርግ መንግሥትም ሆነ አሁን ካለው የኢህአዲግ መንግሥት ጋር ሳትወግን በልጆቿ ጥረትና ተጋድሎ ከማንኛቸውም የመንግሥትና የፓለቲካ ተጽዕኖ ራሷን ነጻ በማድረግ ሁሉም በእኩልነት የሚያመልክባት ቤተ ክርስቲያን ሆና ኖራለች።
በዚህ የፓለቲካ ወገንተኝነት በሌለው አቋሟም ቤተ ክርስቲያኗ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለሚከሰቱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሁሉ ነጻና ፍትሐዊ የሆነ መሥመርን በመከተል ከክርስትና ሃይማኖትና ከቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅን የእውነት ተግባራት ስታከናውን ቆይታለች።
ዛሬ በሕይወት ያሉና በህይወት የማይገኙ አባላቶቿ ካህናትና ምእመናን ላለፉት 40 ዓመታት ባደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ድካምም በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያኗ በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ለከፍተኛ የእድገት ደረጃ የበቃች ከመሆኗም በላይ ወደፊትም ከማንኛቸውም የመንግሥትና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ በመሆን የበለጠ በማደግና በመስፋት ለስደተኛው ሕዝብና በስደት ላይ ለሚፈጠረው ትውልድ የምትተላለፍ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፤ ሃብትና ቅርስ ሆና የምትኖር ነች።
ይህንን የመሰለውን የቤተ ክርስቲያኗን ያለፈ ታሪክና የወደፊት ራዕይ በማፍረስ በአሁኑ ወቅት አስተዳደሯንም ሆነ ሃብትና ንብረቷን ዛሬን ኖሮ ነገ በሚያልፍ የኢህአዲግ መንግሥት የእጅ አዙር ቁጥጥርና ተጽዕኖ ሥር ለማዋል የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና ተከታዮቻቸው በመፈጸም ላይ ያሉት የክህደት ሥራ ቤተ ክርስቲያኗን ለዚህ ያበቋት አባላቷም ሆኑ ደጋፊዎቿና መላው በስደት ዓላም የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚታገሱትና የሚቀበሉት አይሆንም።
በዚህ መሠረት ይህችን በሕዝብ ጥረትና ድካም ደርጅታ በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ለከፍተኛ የእድገት ደረጃ የበቃች ቤተ ክርስቲያንን ያለ ሕዝብ ፍቃድ፤ እውቅናና ይሁንታ በስውር በመደራደር ለሌላ አካል አሳልፎ በመሸጥ መሾሚያና መሸለሚያ ለማድረግ መሞከር አጠቃላይ ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ ከማዋረድ አልፎ በቁመናው እንደ መግደል ስለሚቆጠር የቤተ ክርስቲያኗ አባላት፤ የማርያም ወዳጆችና በአጠቃላይ በስደት ዓለም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የተሰነዘረበትን ጥቃት በመረዳት የተንኮሉን ገመድ በመበጣጠስ ሴራውን አክሽፎ ከእግዚአብሔር በታች የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤት፤ አዛዥና ወሳኝ ሕዝብ ብቻ መሆኑን በተግባር የማረጋገጥ ሃይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ ግዴታ አለበት።
በዚህ መሠረት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት፤ ወዳጆችና በUKና በመላው ዓለም የምትገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሕግን ተከትሎ በመሄድ ቤተ ክርስቲያኗን ለማዳን የሚደረገው ጥረት ገንዘብ፤ ጊዜና አቅምን የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት አስተባባሪ ኮሚቴው በሚያወጣው መርሃ ግብርና ጥሪ መሠረት አቅማችሁ የፈቀደውን ሁሉ እንድታደርጉ በቅድስት ማርያም ስም ጥሪአችንን እናስተላልፋለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

       Posted By.Dawit Demelash

      

Sunday, March 24, 2013

የመለስ ታጋዮች እና የህወአት ታጋዮች ፍጥጫ

በሚል ርዕስ አንድ ሰፋ ያለ ጽሁፍ ብጽፍ ድስ ይለኝ ነበር፡፡፡፡አንድ ቀን እግዜር ካለ አደርገው ይሆናል፡፡ ዝምብሎ መቸክቸክ ሳይሆን ለአቅመ መጻፍ ስደርስ አይሆንም አልልም፡፡በነገራችን ላይ ህወአት ተጠነካረ ነው የሚባለው ወይንስ ተመነቃቀረ፡?፡ እኔ ግን ሳስበው ምንቅርቅሩ ነው የወጣው፡፡ ደግሞ ለምን እንደሆነ አላውቅም የአቶ አባይ ጎጆ ቤት ጣሪያ ተቀዶ ዝናብ የሚያፈስ የሚያፈሰ ይመስለናል፡፡ ይሄ የእኔ ምኞትና እይታ ነው፡፡ለምን እንዲህ አልክ የሚለኝ ካለ ብዙ ባይሆንም እስቲ እ ዝም ብዬ የሆነ ነገር ልበል፡፡ በመጀመሪያ በአሁኑ ሰአት የመለስታጋዮች እንጂ የህወአት ታጋዮች የሉም ብዬ ልነሳ፡፡መለስ ከመሞቱም በፊት ገና አየሎም አርአያ ተገደለ የተባለ ሰሞን ነው አሁን ..የመለስ ራእይ ነው የምናስፈጽመወው.. የህወአት ራእይ ነው ..የምናስፈጽመው ብለው የሚከራከሩት፡፡ ይህንን ነገር የሰማሁት አንድ ጊዜ የሳሞራ የኑስ የጀነራልነት ሹመት ጉዳይ አስመልክቶ.. የመለስ አምልኮ ከሚለው መጽሀፍ ነው ከፍትህ ጋዜጣ፣፣ ከሁለቱ አንዱ እያነበብን እያለ በተነሳ ክርክር የተነሱ አንዳንድ ነጥቦች እንደ ዋዛ የሚታዩ አልመሰለኝም፡፡ አንዱ እውነቱን ነው ተመስገን ደሳለኝ አሁን ሳሞራ የኑስ ምን ሰርቶ ነው ጀነራል የተባለው ብሎ ጥያቄ ያነሳል፡፡ አንድ የሹመቱ ደጋፊ ደግሞ እና አማራ እንዲሾም ነበር የፈለከው እሱ እኮ ስንትና ስንት ተአምር የሰራ ሰው ነው ብሎ እያወራ ሳለ ሌላናው ሰው ጣልቃ ገብቶ ምን ሰራ .መለስንከሞት ስላዳነ የተሰጠው ገጸበረከት ነው ለምሳሌ እንክንፈ ገ/መድህን እነ ስዬ አሴሩት የተባለው ልክ መለስ ዜናዊ ከውጪ ሲመጣ እሱን የጫነችውን አውሮፕላን በአየር ላይ መተ የመጣል ወይም መቀሌ ላይ እንዲያርፍ ተደርጎ ገና ወጣሁ ሲል ጭጭ ሊያደርጉት ነበር የተባለው መረጃ በመስጠት ያከሸፈው ሳሞራ የኑስ ነው -ያ በማድረጉ ደግሞ የተሸለመው የተባለው ሹመት ነው ሲል ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ሳይሆን አይቀርም ብዬ የጠረጠርኩት ደግሞ ያ ለሳሞራ አግዞ ይከራከር የነበረው ሰው.. እሱማ ያለፈ ነገር ነው..ሲል ስለ ሰማሁት ነው፡፡ ዛሬ ተቃዋሚዎች ስዬን የሚያደንቁት ያኔ መለስን ሊገልላቸው ስላሰበ አይደል እንዴ ሌላማ ምን ምክንያት አላቸውና ሲልም ሰምቻለሁ፡;የመለስ ታጋዮች ስራቸው የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡ መለስ በህይወት እያለ … የታጋዮቻችን ደም ተረሳ፣ እናቶቻችን ልጆቻቸው አምነው የሰጡን እንደዚህ አይነት ግፍና ጭቆና እንዲኖር አልነበረም ምናምን ይሉ ነበር የተባሉትን የሚሉትን ታጥኮና አስታጥኮ እስኪበቃቸው አሳዷቸዋል ይባላል፡፡ የቱ ጋ እንዳሳደዳቸው ለእኔ ባይተየኝም፡፡ አሁን ከሞተ በኋላ ግን አንዳንድ የሚታዩ ነገሮች አሉ፡፡የመለስ ታጋዮች እና የህወአት ታጋዮች አንድ እንዳልሆኑ በዚህ ሰሞን ከተደረጉት ..አረንጓዴ የመለስ ካርድ እየሰጡ የማስገባትና ቀይ የመለስ ካርድ እየሰጡ የማስወጣት ነገር አይተናል፡፡መተካካት በሚል የመመንጠሪያ ጫወታ፡፡መንጣሪዎች የትግል አርማችን አላማ ግባችን መለስ ነው የእሱን ራእይ እናስፈጽማለን ሲሉ ነበር የሚባል ነገር እየተሰማ ነው፡፡ የትኛው መለስ ስንል በአሁኑ ወቅት የምናውቀው ሁለት ነገር አለ፡፡ ከመሞቱ በፊትና ከሞተ በኋላ ያለው መለስ፡፡ ሳይሞት በፊት መለስ አሁን እንደሚወራለት እንዲህ የቅዱስ ገብርኤል እኩያ አልነበረም የሳጥናኤል እንጂ፡፡ አሁን ግን እየተወራ ያለው ነገር የተለየነው መለስ ከስብእናው አንስቶ ሁለነመናው ቅዱስ ተደርጎ እንደ ግሪኩ ቅዱስ ጊዮርጊስና እንደ ኢትዮጵያዊው ተክለሐይማኖት በቅዳሴ ሰአት በቤተ መቅደስ ውስ ጥ ምስሉ ጠለጥፎ የአምልኮ ና የጸሎትና ስግደት ሳይቀር ሳይደረግለት አይቀርም፡፡ አሁን የኔ ጥያቄ የመለስ ታጋዮች ለየትናው መለስ ነው ለመታገል የወሰኑት የመለው ጥያቄ ነው፡፡ዛሬ እንኳን ወደ ጦር ሀይሎች አካባቢ ብትመጡ የፎቶግራፍ አውደርአዕይ ተብሎ የተተከለው ድንኳን ሁሉ በመለስ አምልኳዊ ምስል ነው የተሞላው፡፡ በቃልም በምስልም ሁሉም ነገር መለስ ነው፡፡ አንድንድ ሚረባ ነገር ሰሩ ተብለው ይሸለሙ የነበሩ ሰዎችም የአባታቸውና የጌታቸው መለስን ምስልን ምስል እየሳሙና እጠሳለሙ ነበር የሚቀበሉት፡፡ እንዴት ነው ነገሩ፡? ሁላችንም እንዲህ ለቆመው ምስል ለማሰገድ ነው ትግሉ፡፡ አልገባንም፡፡ እኔ ህወኣት የየሚባል ቅዱስ አለ እያልኩኝ ግን አይደለም፡፡ሲወራ እንደ ሰማሁት ግን የአየሎም አርአያ ራእይና የመለስ ራእይ በጣም ተራኒ ናቸው ሲባል ፡፡እንዳውም ሀየሎም የኤርትራን ሁሉ መገንጠል የማይደግፍና የህወአትም አላማ የኢትዮጵያ ነጻነትና አንድነት ማስጠበቅ አለበት የሚል እንደ ነበር ብዙ ሰዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ እዚህ ፌስቡክ ላይ ሳይቀር፡፡ አሁን እኔን እያስጨነቀኝ ያለው ጥያቔቄ እነዚህ የሀህወአት ታጋዮች ወይም የሀየሎም አላማ አራማጆች እጅእግራቸው አጣጥፈው እንደዛ የወደቁለትና የተዋደቁለት አላማ ለአንድ ግለሰብ ክብርና ስም አሳልፈው ይሰጣሉ ወይ ነው፡፡እኔ አይመስለኝም( ይቅርታ ነገ ብጨርሰው ይሻለኛል)
       Posted By.Dawit Demelash

Friday, March 22, 2013

“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም

 

ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል
hidassie dam
“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።
ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።
49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ባንኮችና የተለያዩ ግለሰቦች በትዕዛዝ አክሲዮን መግዛታቸውን ያስታወሱት እኚሁ ዲፕሎማት “በግድቡ ዙሪያ ከሚፈራው የጸጥታ ችግር በላይ አስጊው ጉዳይ የባለድርሻዎች ምስጢር መሆን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
መንግስት ለግንባታው የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ከአውሮፓዊቷ አገር ማግኘቱን ያመለከቱት የጎልጉል ምንጭ፣ “ከአገር ውስጥ በአክሲዮን ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአገር ውስጥ በጀት ማሟያና ለመንግስት የስራ ማከናወኛ የሚውል ነው” ብለዋል።
መንግስት በተለያየ መድረክ በተደጋጋሚ ፕሮጀክቱ “በአገር ውስጥ ባለሙያ፣ በአገር ውስጥ ሃብት፣ የሚከናወን የህዳሴ መገለጫ ነው” በሚል ብሄራዊ መነቃቃት የተፈጠረበት የአቶ መለስ ማስታወሻ እንደሆነ ከመግለጽ ውጪ ስለ አክሲዮን ድርሻና አክሲዮን ስለገዙ አገራት እስካሁን የተናገረው የለም።
ግድቡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ መገለጹ ይታወሳል። የአባይ ግድብ ከሱዳን ድንበር 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቤኒሻንጉል ክልል እንደሚገኝ መንግስት የግድቡን ሥራ ይፋ ሲያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እያለ ፋና በዛሬው እለት ባሰራጨው ዜና “የወንዙን ተፈጥሯዊ የፍሰት አቅጣጫ የማስቀየሩ ስራ እየተሰራ” መሆኑን የገለጸ ሲሆን፥ “ወንዙ ይሄድበት የነበረውን ቦታ 1780 ሜትር ከፍታ ያለው ግድብ የመካከለኛው ክፍል የሚያርፍበት እንደሚሆንም” የፕሮጀክቱ ሥራአስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው መናገራቸውን ጠቅሷል። “አቅጣጫውን የማስቀየሩ ስራ ከመጭው ክረምት በፊት” ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን መሃንዲሱ ጠቅሰው፥ በቅርቡም ዕውን ይሆናል ብለዋል። ግድቡ ግንባታው የተጀመረበት 1ኛ ዓመት በዓልም ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ፥ እንዲሁም መጋቢት 24 ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ስፍራ በተለያዩ ስነ ጥበባዊ ዝግጅቶችና ‘መለስ ቃልህ ይከበራል፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብም በህዝባችን ተሳትፎ እውን ይሆናል’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል” በማለት የዜናው ዘገባ ገልጾዋል።
 
             Posted By.Dawit Demelash

Thursday, March 21, 2013

         በአፋር ህጻነት በርሀብ እየረገፉ ነው

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በክልሉ ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ የተከሰተው ከፍተኛ ረሀብና የውሀ እጥረት የበርካታ ህጻናትን ህይወት መቅጠፉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ምንም እንኳ 60 በመቶ በሚሆነው የአፋር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሀ እጥረት ቢከሰተም ፣ ችግሩ ከሁሉም ወረዳዎች አስከፊ ሆኖ በቀጠለበት የእዳ ወረዳ 6 ህጻናት በአንድ ወር ውስጥ ሞተዋል። ይህ አሀዝ በአንድ ሰፈር ብቻ የተጠናከረ እንጅ በአጠቃላይ በወረዳው በተከሰተው ረሀብና የውሀ እጥረት የሟቾች ቁጥር በብዙ መቶዎች ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል።
አንድ ጀሪካን ውሀ በ60 ብር ለመግዛት መገደዳቸውን የገለጹት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የእዳ ወረዳ ነዋሪ፣ የአካባቢው ነዋሪ ፍየሎቹና ግመሎቹ አልቀውበት ወደ አሳይታ ስደት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ አሳይታ በሰላም የደረሱት በህይወት ሲትረፉ ሌሎች ደግሞ በመንገድ ላይ አልቀዋል ።
የመንግስት እርዳታ እንዳልመጣላቸው የተነጋሩት ነዋሪዎቹ ፣ አስቸኳይ እርዳታ ካልደረሰ አስከፊ እልቂት ይፈጠራል ብለዋል።
በአካባቢው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘው የአፋር ጋድሌ ሊ/መንበር ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ለኢሳት እንደገለጡት ከፍተኛ ረሀብ በአካባቢው መግባቱን ድርጅታቸው እንደሚያውቅ ገልጸዋል።
በዚህ አመት ከአፋር ሌላ በሶማሊና በተለያዩ የአማራ፣ የደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ድርቅ መግባቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአዲስ አበባ ህጻናት በምግብ እጦት ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ ሸገር ኤፍ ኤምን በመጥቀስ ኢሳት ትናንት መዘገቡ ይታወሳል።
በግብርናው መስክ ከፍተኛ እመርታ እንዳገኘ ከመናገር ተቆጠቦ የማያውቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ፣ ላለፉት 21 አመታት ኢትዮጵያን በምግብ ራሱዋን እንደሚያስችል ቢናገርም እስካሁን ድረስ የታየ ለውጥ የለም። በቅርቡ ይፋ ሆነ አንድ ጥናት እንዳለመከተው ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በምግብ ለስራ ታቅፈው ከአለም ባንክና ከአውሮፓ ህብረት በሚለገስ ስንዴ እየተደጎሙ ነው። በዚህ አመት የአስቸኳይ ምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በመላው አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የውሀ እና የምግብ እጥረት ቢከሰተም ገዢው ሀይል በቅርቡ 200 ሚሊዮን ብር በማውጣት የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አክብሮአል። ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ደግሞ የመከላከያ ቀንን አክብሮአል።

   Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, March 20, 2013

ህወሃት አባረረ፣ ብአዴንና ደኢህዴን ባሉበት ቀጠሉ
tplf meeting
ድሮ “ላዩ ካኪ ውስጡ ውስኪ” እየተባለ በኢሰፓ አባላት ዩኒፎርም ይቀለድ ነበር። ዛሬ ደግሞ ኢህአዴግ ተመሳሳይ ልብስ አልብሶ በየክልሉ የሰየማቸውን ፓርቲዎችና አመራሮቻቸውን የተመለከቱ “ስቱኮ” እያሉ እንደሚቀልዱባቸው ተሰምቷል።
“ስቱኮ” ግልብጥና ግጭት የበዛበት መኪና ተቀጥቅጦ አልስተካከል ሲል፣ የተገጣጠበና አልመሳሰል ያለ ግድግዳ “በግድ” ለማመሳሰል የሚያገለግል ቶሎ የሚፈረካከስ ጭቃ መሰል የቀለም አይነት ማጣበቂያ ነው።
“ኮሚኒስቶች በችግርና በቅራኔ ውስጥ ሆነው በግድ ለመመሳሰል አንድ ዓይነት መለያ መልበስ ይወዳሉ። ኢህአዴግም በተመሳሳይ በችግር ውስጥ ተዘፍቆ ሳለ፣ ለተመልካችና ለካሜራ ተመሳሳይ ልብስ ለብሶ በግድ አንድ ነኝ ሲል ማየቱ ብዙም የሚገርም አይደለም” የሚለው አስተያየት በስፋት እየተሰጠ ነው። “በግድ አንድ” ሆነው በየክልሉ ስብሰባ የሚያካሂዱት እህት ፓርቲዎች የለበሱትን መለያ የሚያመርተው ደግሞ የህወሃት የንግድ ድርጅት አልሜዳ ጨርቃጨርቅ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ባህር ዳር ላይ ለሚያካሂደው ጉባኤ በዝግጅት ላይ ያሉት “እህት” ፓርቲዎች በየክልላቸው በስብሰባና በምርጫ ተጠምደው ሰንብተዋል። ውሉ ያልታወቀውና ምስጢር የተደረገው የኦህዴድ ጉባኤ የምርጫውን ውጤት ማጠናቀቅ አልቻለም። ህወሃት በመተካካት ስም ነባሮቹን አራት አመራሮች ሲያሰናብት፣ አቶ በረከትና አዲሱ ለገሰ የኢህአዴግ የመተካካቱ ስልታዊ በትር ሳይነካቸው ማለፉ ተደምጧል። ደኢህዴን በነበረበት እንደሚቀጥል ይፋ ሆኗል።
ኦህዴድን ለመምራትና ሰባት አመራር በሚሰየምበት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለመሆን አባ ዱላ ገመዳ፣ ግርማ ብሩ፣ ድሪባ ኩማ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ አለማየሁ አቶምሳ፣ አስቴር ማሞና ደግፌ ቡላ ከተጠቆሙት መካከል ይገኙበታል። የህወሃት የንግድ ተቋምና አንደበት የሆነው ሬዲዮ ፋና “የተጠቆሙትን አመራሮች ለማሳወቅ የድምጽ ቆጠራው ጊዜ ስለሚወስድ ለነገ ተላልፏል” የሚል ዘገባ አሰራጭቷል።
ፋና ይህን ይበል እንጂ የጎልጉል ምንጮች ከስፍራው እንዳሉት የኦህዴድ ስብሰባ ከፍተኛ ንትርክ የተስተናገደበት ሆኗል። ምንጮቹ እንዳሉት የበታች አመራሮች፣ የቀበሌና ወረዳ የስር መዋቅሮች በድፍረት የድርጅቱን አመራሮች ነቅፈዋል። በራሳቸው ውሳኔና መንገድ የማይመሩበት ምክንያት መነሻና ይህ አካሄድ መቼ ሊያቆም እንደሚችል ሊገባቸው እንዳልቻለ የተናገሩ አሉ።
“ውርስና ቅርስ” እየተባሉ የሚወደሱት አቶ መለስ በህይወት እያሉ ህወሃት ድምጽ ነፍጎ ሲያባርራቸው “መለስ ይሁን” በማለት የተሰጣቸውን የህወሃት ሊቀመንበርነት ስልጣን ላለመቀበል ያፈገፈጉት አቶ አርከበ እቁባይ በመተካከት ስም ከህወሓት መሰናበታቸው ይፋ ሆኗል። ዊኪሊክስ ይፋ ባደረገው መረጃ ህወሃትን እንዲመሩ ተመርጠው የነበሩት አቶ አርከበ አዲስ አበባ ፎቶግራፋቸው ከተለጠፈበት ጊዜ ጀምሮ “የድስትና ማማሰያ” ምሳሌ በመሆን ጥግ ተደርገው ከተረሱ በኋላ በመጨረሻ አማካሪ ተብለው ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ተዛውረው ነበር።
አቶ በረከትን ተከትሎ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ዘርአይ አስገዶምና አቶ ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ህወሃትን በይፋ መሰናበታቸው ታውቋል። ፋና “በክብር ከማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰናብተዋል” ሲል አሞካሽቶ መርዶ አብስሯል። ፋና በነካ እጁ የዋናውን የሚዲያ ፊት አውራሪ አቶ በረከትን ዜና ይፋ አደርጓል።
መለስ ያዘጋጁት “የማጽጃ በትር” የሚባለው መተካካት ብአዴን ውስጥ ተግባራዊ አልሆነም። ታማኞቹ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ቡድን የሆኑት አቶ በረከት፣ ሰሞኑን በተዘጋጀ ዶክመንታሪ ፊልም በትግርኛ ተረት ሲያወርዱ የታዩት አቶ አዲሱ ለገሰ፣ አቶ ጉዱ ካሳና ፓርላማ ውስጥ የስነስርዓት ጥያቄ ሲቀርብላቸው “ታዝዤ ነው፣ ከታዘዝኩት ውጪ የማደርገው የለም” በማለታቸው የሚታወቁት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በአዲሱ ምርጫ ተካተዋል።
ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ደኢህዴንን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ምክትል ሆነው እንዲቀጥሉ ተሰይመዋል። በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት የሞባይል ስልክ ማነጋገር አስቸጋሪ እንደነበር የጎልጉል መረጃ አቀባይ ከስፍራው አስታውቋል። አቶ ሃይለማርያም የአገሪቱ መሪ ከሆኑ በኋላ ሃዋሳ ሲገኙ ለደህንነት በሚል የስልክ መስመሮች ላይ ማዕቀብ መደረጉን ተገልጋዮች በቅሬታ ሲገልጹ ተሰምቷል።
ከሁሉም ጉባኤዎች ጎልቶ የወጣው የህወሃት ጉባኤ ሲሆን የትግራይ ክልል ሃብትና እድገት በታላቅ ትዕይንት ከጉባኤው በፊት ለህዝብ እንዲተላለፍ መደረጉ የተለያየ አስተያየት እየተሰነዘረበት ነው። መቀሌ በትዕይንት አቅራቢ ህዝብ ተጨናንቃ ሲጨፈርና ከበሮ ሲደበደብ ያሳየው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዳለው ትዕይንቱ የተዘጋጀው መለስን ለመዘከር ነው። ዜናው በተመሳሳይ ሌሎች ክልሎች የደረሱበትን የልማትና የዕድገት ደረጃ የሚያሳይ ትዕይንት እንመራዋለን ለሚሉት ህዝብ በይፋ ያላሳዩበትን ምክንያት ግን አልገለጸም።
ጋዜጠኛ ተመስገን “ሽክ” ብሎ ፊቱ ላይ ርካታ እየተነበበት ያነጋገረው ጋዜጠኛ መቀሌ ባየው ነገር መገረሙን ደጋግሞ አመልክቷል። በተሽከርካሪ ላይ በተዘጋጁ ሞዴል ማቀናበሪያና ምስሎች ትግራይ የደረሰችበትን ደረጃ የተመለከቱ “ልማት ያስደስታል። ከሰባ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚያለቅስበት ልማት መሆኑንን ስናስብ ያሳዝነናል” ሲሉ ተደምጠዋል።
አርቲስት መሐሙድ አህመድ “ትግራይ ልትሰምጥ ነው የሚባለው ውሸት ነው” በማለት የተናገረውን ያስታወሱ አስተያየት ሰጪ፣ “ብሶት ሁሉም ቦታ፣ በየትኛውም ጊዜና ወቅት የሚከፋቸውንና በቃን የሚሉ ዜጎችን ይፈጥራል። የትግራይ ህዝብም ብሶት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ትግራይ ብቻዋን ስትለማና ስታድግ ሌላው እየተረገጠ መሆኑንን በመገንዘብ ከመጨፈር ይልቅ በማስተዋል በስማቸው የሚፈጸመውን ግፍ እንዲቆም የመጠየቅ ሃላፊነት አለባቸው” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

   Posted By.Dawit Demelash

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ አደረጉ

March 19, 2013 11:30 am


img_4680
የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የትምህርት ማቆም አድማ ላይ እንዳሉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡
እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ተማሪዎቹ በአመራር ላይ ያለው አስተዳደር ብቃት የለውም፣ የምግብ አቅርቦትና ጥራት ችግር አለ፤ ምላሽ ግን የሚሰጥም ሆነ ለማነጋገር ፈቃደኛ የሆነ አካል የለም በማለት የኮሌጁ የቀን ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ለማድረግ ተገደዋል፡፡ ተማሪዎቹ ለኮሌጁ አስተዳደር ካነሷቸው ጥያቄዎች በተጨማሪ፣ በኮሌጁ በርካታ ኃይማኖታዊ የአሰተዳደር ችግር እንዳለ ቢጠቅሱም በአስተዳደሩ ምላሽ አለመሰጠቱን ገልፀውልናል፡፡
በነዚህ ምክንያቶች ተማሪዎቹ ጥያቄዎቻቸው እስኪመለሱ ድረስ ትምህርት እንዳቆሙና አንዳንድ ተማሪዎችም መልቀቂያ (ክሊራንስ) እየሞሉ መውጣታቸውን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የማታ ተማሪዎችም ከሐሙስ መጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ለኮሌጁ ደህንነት በሚል በአስተዳደሩ ትምህርት እንዲያቋርጡ መደረጋቸውን ተማሪዎቹ ለፍኖተ ነፃነት አረጋግጠዋል፡፡
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍልም የኮሌጁ ትምህርት የተቋረጠበትን ምክንያትና ተማሪዎቹ አነሷቸው የተባሉትን ጥቄዎች በተመለከተ የኮሌጁን አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ሆኖም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ህዝቄልን ጠይቀናቸው “ትምህርት መቋረጡን ገና ከእናንተ አሁን መስማቴ ነው፤ የደረሰኝ መረጃ የለም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ምንም እንኳ ከጠቅላይ ቤተክህነቱ ዋና ፅህፈት ቤት እስከ ኮሌጁ ድረስ ያለው እርቀት በግምት ከ600 ሜትር ባይበልጥም የቤተክህነቱ ዋና ፀሐፊ ስለትምህርት ማቆም አድማው የሰሙት እንደሌለ ገልፀውልናል፡፡
ይህ መረጃ እስከተዘገበበት መጋቢት 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ በኮሌጁ ትምህርት እንዳልተጀመረ አረጋግጠናል፡፡

  Posted By.Dawit Demelash

Tuesday, March 19, 2013

ጀርመናዊዉ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በወያኔ ጫና ስራቸዉን ለመልቀቅ መገደዳቸዉ ተሰማ

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲን ለረጂም ግዜ በፕሬዚዳንትነት የመሩት ጀርመናዊዉ ፕሮፌሰር ዩኪአም ሄርዚግ ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣኖች በስራቸዉ ላይ ጣልቃ እየገቡ ስላስቸገሯቸዉ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ባስገቡ በሦስት ቀን ዉስጥ መቀሌን ለቅቀዉ ወደ አገራቸዉ መጓዛቸዉን መቀሌ ዉስጥ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን ከሰሞኑ በላኩልን ዜና ገለጹ። ፕሮፌሰሩ ለምክትል ጠ/ሚነስተር ደመቀ መኮንን ባስገቡት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ላይ ስራቸዉን የሚለቅቁት ባጋጠማቸዉ የጤና ችግር ምክንያት እንደሆነ ቢገልጹም ለመቀሌ ዩኒቨርስቲ ቅርበት ያላቸዉ ብዙ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ፕሮፌሰር ሄርዚግ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በቅርቡ ዩኒቨርሲቲው ዉስጥ በተካሄደ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግምገማ ፕሬዚዳንቱ ሀላፊነታቸዉን አልተወጡም በሚል በተደረገባቸዉ ግፊት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ፕሮፌሰር ዩኪአም ሄርዚግ ከዚህ ቀደም በሁለት የዩኒቨርስቲዉ ምክትል ፕሬዚዳንቶች አሿሿም ላይ ዩኒቨርሲቲውን በበላይነት ከሚመራው ቦርድ ጋር አለመግባባት መፍጠራቸው የሚታወቅ ሲሆን ሁለቱን ተሿሚዎች በተመለከተ ለቦርዱ የጻፉትን ደብዳቤ በአስቸኳይ እንዲቀለብሱ ማስገደዱ ይታወቃል። አንድ ስማቸዉ እንዳይገለጽ የጠየቁ የዩኒቭርሲቲዉ ከፍተኛ ባለስልጣን ቦርዱ ፕሮፌሰር ሄርዚግ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት ያጩዋቸውን ግለሰቦች ሳይቀበልና በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሳይሰጥበት ለሦስት ወራት ያህል ቆይቶ አሁን ግን ሃያ አራት ሰአት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ለመሾም መቿኮሉ የሚገርመና ግራ የሚያጋባ ነዉ ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ቴድሮስ ሓጎስ ለዩኒቨርስቲዉ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሄርዚግ ከኃላፊነታቸው የተነሱት የትራንስፎርሜሽኑን ዕቅድ በሚገባ በስራ አልተገበሩም በሚል እንደሆነ ሲሆን ከእሳቸዉ ሌላ የዩኒቨርሲቲው ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ምክትል ፕሬዚዳንት ወልፍ ቫን ፊርክስንና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶክተር ዩአኪም ሌንገርትን ቦርዱ ከኃላፊነታቸው ማንሳቱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ሁለቱም ጀርመናውያን ከኃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም የአቅም ማነስና የአፈጻጸም ችግር የሚል መሆኑንም የዩኒቨርሲቲው መምህራን ገልጸዋል፡፡


  Posted By.Dawit Demelash

በሲዊዲን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

March 19, 2013 8:36 am
20130315_142609በስቶኮልም ሲዊድን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን የሰልፍ አስተባባሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም የተደረገው የተዋውሞ ሰልፍ አላማ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን በደል ለመቃወም መሆኑን የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ከ 200 በላይ በስቶኮልምና በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መገኘታቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
ሰልፉን ያስተባበሩት በስዊዲን የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎች ጋር በመተባበር ሲሆን ሰልፉን የክርስትና እምነት ተከታዮችም በርከት ብለው በመታደም አጋርነታቸውን ገልፀውበታል፡፡
በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተደረገው በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ “ድምጻችን ይሰማ በስቶኮልም ከተማ”፣ “ሀገር በህግ እንጂ በሀሰት ፊልም አይመራም”፣ “ኢትዮጵያ የሁላችንም ሀገር ናት”፣ “ኮሚቴዎቻችን ህጋዊ ናቸው፤ እነሱን አሸባሪ ማለት ሁሉንም የኢትዮጵያ ሙስሊም አሸባሪ ማለት ነው” የሚሉና የተለያዩ መፈክሮችም ተስተጋብተዋል፡፡
    Posted By.Dawit Demelash

Ethiopia 'blocks' Al Jazeera websites

Google Analytics shows the English website's traffic declined from 50,000 hits
 in July 2012 to 117 in September
Al Jazeera’s English and Arabic websites are reported to have been blocked in Ethiopia,
 raising fresh fears that the government is continuing its efforts to silence the media.
Though the authorities in Addis Ababa have refused to comment on the reported censorship,
Google Analytics data accessed by Al Jazeera shows that traffic from Ethiopia to 
the English website had plummeted from 50,000 hits in July 2012 to just 114 in September.
Traffic data revealed a similar drop for the Arabic website, with visits to the site dropping to 2 in
 September from 5,371 in July.
A blogger, who cannot be identified for his own safety, said Ethiopian censors
 had been targeting Al Jazeera since the Qatar-based network began airing
 coverage of ongoing protests against the way
 in which spiritual leaders are elected in the Horn of African nation.
The steep decline in web traffic began on August 2 last year, the same day
 that Al Jazeera Mubasher aired a forumwith guests denouncing the government's
 "interference" with Muslim religious affairs, and three days after Al Jazeera English published
 an article detailing deadly ethnic clashes between two of the country's southern tribes.
Attempts by Al Jazeera to get an official response from authorities failed.
Poor track record
Ethiopia is ranked 137 out of 179 surveyed nations on the latest Press Freedom Index
 of Reporters Without Borders (RSF), an international advocacy group for press rights.
Both RSF and the Committee to Protect Journalists (CPJ) have tied Ethiopia's deteriorating media 
environment, in part, to a 2009 anti-terrorism law that has been used to sentence 11 journalists
 since its ratification.
"The usage and practice of this law is illegal. It has a clause that makes whoever
 writes about so-called terrorist groups, which are mostly normal opposition groups,
 a terrorist," CPJ's East Africa Consultant Tom Rhodes told Al Jazeera.
"Now it's got to the point that the law is being used to label those in the Muslim community
 conducting peaceful protests to defend their right to choose their spiritual leaders as terrorists.
 It's a sad state of affairs."
CPJ says Ethiopia is the second-highest jailer of journalists in Africa after neighbouring Eritrea,
 were seven journalists are currently detained.
Both the RSF and CPJ have expressed concern over reports that the country has begun
 using much more sophisticated online censorship systems over the last year,
 including ones that can identify specific internet protocols and block them
Since Ethiopia's government owns the sole telecommunications provider in the country,
 Ethio Telecom, it allows authorities to tightly control internet freedom.
 
    Posted By.Dawit Demelash

ህጻናት እየራባቸው መማር አቅቷቸዋል!

"ምሳ ያላቸው ሲበሉ እኔ የቤት ስራ እሰራለሁ"
students in addis
ህጻናት እየራባቸው ትምህርት መማር እንዳቃታቸው ሸገር አዲስ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው መምህራንና ተማሪዎች ተናገሩ። ሸገር ያነጋገራቸው ተማሪዎች በየተራ እንደተናገሩት በምግብ ችግር ትምህርታቸውን መከታተልና ክፍል ውስጥ ትኩረት ማድረግ ተስኗቸዋል።
“ሌሎች ምሳ ያላቸው ምሳ ሲበሉ እኔ የቤት ስራ እሰራለሁ። ወይም ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ” በማለት አንድ ተማሪ ሲናገር፣ ሌላኛው ምሳ የሚባል ነገር እንደማያውቅ ገልጿል። በርሃብ ምክንያት ትምህርታቸውን በወጉ መከታተል ያልቻሉ ተማሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው መምህራኑ ሲናገሩ ሸገር አስደምጧል። በሰሙት ዜና ረፍት ያጡ በርካታ ወገኖች ስልክ በመደወል ተማሪዎቹ በትምህርት ቤታቸው ውስጥ የምሳ አገልግሎት እንዲያገኙ የበኩላቸውን ለማድረግ ሲነጋገሩና ቃል ሲገቡ ለመስማት ተችሏል።
አዲስ አበባ በኑሮ ውድነት ሳቢያ የሚበሉ ያጡ፣ በክፍል ውስጥ ረሃብ እያዞረ ክፍል ውስጥ የሚጥላቸው፣ በየጥጋ ጥጉ አጥርና ጥላ ስር ቀን የሚገፉ፣ የባሰባቸው ቤተሰቦቻቸውን ለማትረፍ ያለ እድሜያቸው ስጋቸውን ለመሸጥ እንደሚገደዱና ቤተሰብ፣ በተለይም እናቶች ልጆቻቸውን ለገበያ ወሲብ ማበረታታት እየተለመደ መምጣቱን የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ አመልክቷል። (ፎቶ: ተማሪዎች በአንድ የአዲስ አበባ ት/ቤት)

   Posted By.Dawit Demelash

Monday, March 18, 2013

30 000 ኢትዮጵያውያንን ለጨፈጨፈው ለግራዚያኒ የተሠራውን ኃውልት መቃወም ያስከብራል!


በኢጣልያ፤ ከሮማ ወደ ምሥራቅ ደቡብ በምትገኝ፤ አፊሌ በምትሰኝ ትንሽ ከተማ፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” ለተሰኘው፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ ነሐሴ 4 ቀን 2004 ዓ/ም የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት የተመረቀለትን የክብር መታሰቢያና መናፈሻ በመቃወም፤ እስከ የኢጣልያ ኤምባሲ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ/ም ስድስት ኪሎ የተሰበሰቡትን 43 ሰዎች፤ ዶር. ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጭምር፤ ፖሊስ አፍሶ ማሰሩና በማግስቱ፤ መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ/ም መልቀቁ ታውቋል።

አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን፤ ከነዚሁ ውስጥ በሶስት ቀኖች ብቻ፤ በአዲስ አበባ ከተማ 30፣000 ሕዝብ ላስጨፈጨፈው፤ እነአቡነ ጴጥሮስን፤ የደብረ ሊባኖስን መነኮሳትና ሌሎችንም በጭካኔ ለረፈረፈ፤ እንዲሁም 2000 ቤተክርስቲያኖችንንና 525፣000 ቤቶችን ላስወደመው፤ በተጨማሪም በብዙ አይሮፕላኖች ባስነሰነሰው የመርዝ ጋዝ ብዙ ሕዝብ ከመግደሉ በላይ እጅግ የከፋ የአካባቢ ብክለትና 14 ሚሊዮን እንስሶችን ላወደመው የጦር ወንጀለኛ፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ የተሠራውን መታሰቢያ መቃወም ለሐገር የሚያኮራና የሚያስመሰግን እንጂ የሚያሳስር አይደለም።

እንደሚታወቀው፤ ለዚህ ዓመት የየካቲት 12 ክብረ-በዓል፤ የፋሺሽቶችን የጦር ወንጀልና የግራዚያኒን መታሰቢያ በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ፤ 30 ከተሞች፤ ማለት፤ ሮማ፤ ኒውዮርክ፤ ዋሺንግተን ዲ.ሲ.፤ አትላንታ፤ ቴል አቪቭ፤ ወዘተ. የሚገኙ የብዙ ሐገሮች ዜጎች፤ ኢጣልያውያን ጭምር፤ ሰላማዊ ሰልፎች፤ ስብሰባዎች፤ ጸሎቶች አከናውነዋል። አዲስ አበባም የከተማው አስተዳደርና የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር በእለቱ ለክብረ-በዓሉ መታሰቢያ ማከናወናቸው ታውቋል።

ስለዚህ፤ በኢጣልያ ለጦር ወንጀለኛው ለግራዚያኒ መታሰቢያ እስከ መሥራት የደረሰ የፋሺሽት መንሰራራት ሊያሳስበንና ሊያስቆጨን የሚገባው፤ ዋናዎቹ የግፉ ተበዳዮች የሆንነው እኛ ኢትዮጵያውያን በመሆናችን፤ ሐገራችን አሁንም እየጠበቀች ያለችውን ፍትሕ እንድታገኝ በሰላማዊ ሰልፍ ለኢጣልያ መንግሥት ማስገንዘብ የሚደገፍ እንጂ የሚያሳስር መሆን የለበትም።
በመጨረሻም፤ ኢትዮጵያ ለተፈጸመባት እጅግ መራርና ከባድ ግፍ እስካሁን ድረስ ተገቢውን ፍትሕ ስላላገኘች፤ ድርጅታችን ለሚከተሉት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ ነው፤

(ሀ) የኢጣልያ መንግሥት፤ የጦር ወንጀለኛውን የግራዚያንን መታሰቢያ እንዲያስወግድ፤
(ለ) በቫቲካንና በኢጣልያ መንግሥቶች ይዞታ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንብረቶች እንዲመለሱ፤
(ሐ) የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል፤
(መ) ቫቲካን፤ ከፋሺሽት ኢጣልያ ጋር ተባብራ በተፈጸመው ወንጀል፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
(ሠ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀሉን እንዲመዘግብ ነው።

ሐገራችን ላይ ለተፈጸመው የጦር ግፍ በሰብአዊ መብት መከበር የሚያምን ሁሉ በሚያከናውነው የተባበረና የጠነከረ ጥረት ተገቢው ፍትሕ ይገኛል።
    Posted By.Dawit Demelash

Sunday, March 17, 2013

የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!


ሰማያዊ ፓርቲ
ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!
እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ የሚገኙት እና ስማቸው የተገኘ
1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ
3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር)
4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር)
5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ)
7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ)
8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር)
9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ)
10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ
11. ሰለሞን ወዳጅ
12. ወይንሸት ንጉሴ
13. እየሩሳሌም ተስፋው
14. ለገሰ ማሞ
15. ትዕግስት ተገኝ
16. አማኑኤል ጊዲና
17. አለማየሁ ዘለቀ
18. አገኘሁ አሰገድ
19. ሻሚል ከድር
20. አሸብር ኪያር
21. ጌታቸው ሽፈራው
22. ግሩም አበራ
23. አቤል ሙሉ
24. ዩሀንስ ጌታቸው
25. ስማቸው ተበጀ
26. ፍቃዱ ወንዳፍራው
27. ባህረን እሸቱ
28. ሄኖክ መሀመድ
29. እንቢበል ሰርጓለም
30. አለማየሁ በቀለ
31. ዩናስ
32. የመኪናው ሹፌር
33. ዮዲት አገዘ
34. ጥላዬ ታረቀኝ


     Posted By.Dawit Demelash

Saturday, March 16, 2013


መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ

መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ  ” በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል ፣ በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው  አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን የወያኔ ካድሬዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ ከፈረሱ እና እያፈረሱ ካሉ ቤቶች አብዛኞቹ የአማራ ተናጋሪዎች መኖሪያ መሆናቸውን መታዘቡን ” ገልጿል።በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተማዎች የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የባንክ ብድርን ጨምሮ መሬት እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ ከፍተኛ ግብር እየተጫነባቸው በመሆኑ ከንግድ ስርአቱ እንዲወጡ ተድርጓል ብሎአል መኢአድ በአሁኑ ጊዜ ከ200 በላይ ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በባህርዳር  ያለመጣለያ በጎዳና እየኖሩ መሆኑን መኢአድ በመግለጫው አመልክቷል።በባህርዳር ለጎዳናና ተዳዳሪነት ከተዳረጉት መካከል ብዙ ነፍሰጡሮችና ህጻናት የገኙበታል።አገዛዙ ከመጀመሪያው ጀምሮ የአማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ በብሄራዊ ጨቋኝነት በመፈረጁ በአርባ ጉጉ ፣ በበበደኖ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በጋምቤላ እንዲጨፈጨፍ ሲያድረጉ አገዛዙ ምን ያክል የአማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ለማጥፋት እንደፈለገ አመለካች ነበር፣ የሚለው መኢአድ፣  ከአንድ አመት በፊት በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በከፍተኛ ጭካኔ በአማርኛ ተናጋሪ አርሶአደር ፣ ሴቶች፣ ነፍሰ ጡር፣ ህጻናት እና ሽማግሌዎች ላይ የተጀመረው ጭካኔ የተሞላበት ስደት ተባብሶ ቀጥሎ በየጎዳናው የሚጣለው የኔቢጤ ከመሆን አልፎ ለአውሬና ለአሰቃቂ ኑሮ የተጋለጠው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ህብረተሰብ ቁጥር እየጨመረ በቤንሻንጉል ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር እና በአንዳንድ የአሮሚያ ክልል እየቀጠለ ነው ብሎአል፡፡መኢአድ ” ማንኛውም ሰው በቋንቋው ፣ በጎሳው፣ በእምነቱ፣ በቀለሙ እና በማንኛውም ልዩነት ምግብ ሲያጣ መጠለያ ሲነፈገው ጨቅላ ህጻናት በየጎዳናው ሲሞቱ፣ ነፍሰጡሮች በየበረንዳው ሲወድቁ፣ ህሊናን የሚያደማ መሆኑን ገልጾ፣ የህንን ጨቋኝ ስርአት በአለም ህዝብ ፊት በዘር ማጥፋት ወንጀል ልንከሰው ይገባል ብሎአል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ  ከ5 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን እንዲፈናቀሉ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የተባሉ የ67 አመት አዛውንት ” ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” ሲሉ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የሚባሉት እኚሁ እናት የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት ባለቤታቸውም እንደ እሳቸው ሁሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን  ከዕንባቸው ጋር እየታገሉ መግለጻቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። “በሐረር ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ኖሬ፤ ሀብትና ንብረት አፍርቼ እኖር ነበር አሁን ግን በአካባቢው እንዳልኖር ተደርጌያለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ከ30 ዓመት በላይ የኖርኩበትን ቤቴን የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው ፓሊስ አዛዥ አስጠርተው ቤትሽን ለወ/ሮ አኒሳ መሐመድ ሸጠሽ ግቢውን እንድታስረክቢያት አሉኝ፡፡” ብለዋል። እኔ ቤቴን የመሸጥ ሐሳብ የለኝም፡፡ ቤቴን ሸጪ የት እወድቃለሁ? አልሸጥም አልኳቸው እንቢ ካልሽ ከአገራችን እናባርራሻለን በገንዘብ አልሸጥም ካልሽ በባዶሽ ተባረሽ ወደ አገርሽ ትሄጃለሽ አሉኝ፡፡ እኔ ሌላ አገር የለኝም የምሄድበትም ቦታ የለኝም መንግስት ባለበት አገር ቤትሽን ተቀምተሽ ውጪ የሚለኝ የለም ብዬአቸው ተመለስኩኝ” በማለት የችግሩ መነሻ አስረድተዋል።ጎስቋላዋ የ67 ዓመት እናት በማያያዝም “በማግስቱ እኔ ቡና አፍልቼ፣ ባለቤቴም ጫማውን አውልቆ ፍራሽ ላይ አረፍ እንዳልን፤ አንድ ፓሊስ በሩን በሰደፍ እና በእርግጫ መቶት  በረገደው፡፡ ምንድነው? ብለን ስንወጣ ከ30 በላይ ፓሊሶች ቤታችንን ከበውታል፡፡ ይህች ናት፡፡ ነይ ውጭ! ብሎ ለሁለት ሶስት ሆነው ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምን አደረኩ ብዬ ስለምናቸው አንቺ ለህግ አልገዛ ያልሽ አመጸኛ ነሽ! ወንጀለኛ ነሽ እያሉ መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምንም የሰራሁት ወንጀል የለም ብዬ ጮኩኝ፡ ፡ ጎረቤት ተሰበሰበ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ማንም ምላሽ አልሰጠም” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ሟች ልጃቸውን በሀዘን ተውጠው እያስታወሱ ይቀጥላሉ “ልጄ ባል አግብታ የምትኖረው ሌላ ቦታ ነው፡፡ ቀን ቀን ምግብ እየሰራች ትሸጣለች ፓሊሶች እናትሽን ከበው እየደበደቡ ናቸው ብሎ ጎረቤት ሲደውልላት ሮጣ መጣች፡፡ ደርሳ ምን አድርጋ ነው ብላ ብትጠይቅ ቤቱን አስረክቢ ስትባል እንቢ ብላ ነው አሏት፡ ፡ የተወለድንበትና ያደግንበትን ቤት ከህግ ውጭ እንዴት እንነጠቃለን ብላ ስትጮህ ጥላው ሄዱ” በማለት በለቅሶ ያስረዳሉ፡ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ  “ያንለቱኑ ማታ ልጄ ምግብ የምትሸጥበት ቦታ ሁለት ሰዎች ተመጋቢ መስለው ከገቡ በኋላ ፣ ረመዳን የተባለ ፓሊስና እንዳለ ግርማ የተባለ ወጣት፣ ቤቱን አስረክቡ ስትባሉ አናስረክብም የምትሉት ለምንድነው ብለው ረመዳን ልብሷና ሰውነቷ ላይ ጋዝ ሲደፋባት እንዳለ ግርማ የተባለው ላይተር ለኩሶ አቃጥለዋታል፡፡  ሳትሞት ሆስፒታል ደርሳ ነበር፡፡ በማግስቱ አዲስ አበባ አምጥቼ ላሳክም መኪና ተከራይቼ ይዤ ስወጣ ፓሊስ እዚህ አትታከም እንጂ ከሐረር አትወጣም ብሎ ከለከለኝ፡፡ እኔም ገንዘብ ካለኝ እንኳን አዲስ አበባ አሜርካን ወስጄ ባሳክም ለምን እከለከላለሁ ብዬ ብጮህ ባለቅስ ማንም ሊደርስልኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ህክምና አጥታ ሞተች፡፡” ብለዋል፡፡አዛውንቷ ከልጃቸው ሞት በኋላ የደረሰባቸውን በምሬት ሲገልጹ “እኔንም ከቤቴ አስወጥተው ቦታውን ሺጭላት ላሏት ሴት ሰጧት፡ ፡ አሁን ቦታዬ ላይ ፎቅ እየተገነባ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ ግን ጎዳና ተጣልን፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ አዋጥቶ የሰጠኝን 3ሺ ብር አንድ ፓሊስና አንድ ደላላ መጥተው ነጠቁኝ፡፡ ሐረር ውስጥ አደሬ ወይም ኦሮሞ ካልሆንክ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፡፡ አማራ ነው ከተባለ ሁሉም ባለስልጣን በደረሰበት ግፍና ስቃይ ይስቅበታል፡፡ በደርግ ጊዜ የሐረር ፓሊስ አዛዥ ትግሬ ነበር፤ የማረሚያ ቤት አዛዥም ትግሬ ነው፡፡ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ትግሬ ነው፡፡ ለምን ትግሬ ሆነ ያለ አንድም ሰው የለም፡፡ ዛሬ በሀረር በየትኛውም መስሪያ ቤት አማራ ባለስልጣን የለም፡፡ ባለቤቴ ኦሮሞ ነው፡፡ ልጆቼም ኦሮሞ ናቸው፡፡ እኔ አማራ በመሆኔ ብቻ ይህ ሁሉ ጉዳት ተፈጸመብን፡፡” የሚሉ ወይዘሮዋ፣ የተፈፀመባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዘራቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡አክለውም “አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቃ ተቋም አመለከትኩኝ፡፡ ፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም እንዴት እንዲህ ይፈጸማል ብለው ይዘውኝ ሐረር ተመለሱ፡፡ የቤቴ ካሳ እንዲከፈለኝ ተወሰነልኝ፡፡ የክልሉ ባለስልጣናትም እሺ ይፈጸምሎታል ብለው ቃል ገቡልኝ፡፡ እንባ ጠባቂዎቹ ወደ አዲስ አበባ ተመልሱ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ግን ምንም መፍትሄ አልሰጡኝም፡፡ በድጋሚ አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ባመለክት እነሱም ውሳኔያቸውን እንደ አጀማመራቸው ሊያስፈጽሙልኝ አልቻሉም፡ ፡ ጉዳዬንም ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ ” በማለት የበደላቸውን ስፋት ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡“ዛሬ እኔ አዲስ አበባ ላይ ባለቤቴ ደግሞ ሐረር ላይ ጎዳና ላይ ነን፡፡ መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም” ሲሉ ተስፋ መቁረጥና ምሬት ተሞልተው በለቅሶ የመንግስት ያለህ … የህዝብ ያለህ በማለት ጥያቸውን ማቅረባቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
        Posted By.Dawit Demelash

የህወሀት መሪዎች በድርጅቱ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ ለመምከር መቀሌ ገቡ



March 16, 2013 


መለስ ዜናዊ ሞት ከተሰማበት ግዜ ጀምሮ ምሶሶዉ እንደተደረመሰበት ቤት እራሱን ችሎ መቆም ያቃተዉ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እንዴት ወደፊት መጓዝ እንዳለበትና መጪዉን የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ በተመለከተ ከአባላቱ ጋር ለመምከር በቅርቡ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤዉን እንደሚጀምር አስታወቀ።  በዚህ ከመጋቢት 8 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት መቀሌ ዉስጥ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀዉ የግንባሩ 11ኛ ጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ነባሮቹ የህወሀት መሪዎች መቀሌ በመግባት ላይ መሆናቸዉን የዘገበዉ የግንቦት ሰባት ድምጽ ዘጋቢ ገልጿል፣ ፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆነዉን ስዩም መስፍንን ጨምሮ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖምና ሌሎችም ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት መቀሌ ውስጥ መታየታቸውን የጠቀሰው ዘጋቢያችን  የመቀሌ ከተማ “ምን ይመጣ ይሆን” በሚል ፍርሀት መዋጧንና ነዋሪዉ ፊት ላይ ፍርሀት እንደሚነበብ ገልጿል።
የተከፋፈሉት የህወሀት መሪዎች በተከታታይ ስብሰባ ተቀምጠዉ ለ11ኛ ጉባኤያቸዉ የሚሆን አጀንዳ መቅረጽ ተስኗቸዉ ብዙ ከሰነበቱ በኋላ ከሰሞኑ ያለ አጀንዳ ከመሰብሰብ ያዳናቸዉን የግብር ይዉጣ አጀንዳ እንዳዘጋጁ ለማወቅ ተችሏል። መቀሌና ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ የህወሀት መከፋፈል በግልጽ እተነገረ ሲሆን ግንባሩ በዚህ እሁድ በሚጀመረዉ 11ኛ ጉባኤዉ ላይ ተአምር ሰርቶ አንድነቱን ካላረጋገጠ ደደቢት ዉስጥ የተጠነሰሰዉ ህወሀት መጨረሻዉ መቀሌ ዉስጥ ሊጀመር ይችላል ብለዉ የሚያምኑ ለህወሀት ቅርበት ያላቸዉ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደገመቱ ዘጋቢያንች ከመቀሌ የላከልን ዜና ያስረዳል።
በአሁኑ ወቅት አንጋፋዋ የመቀሌ ከተማ በአንድ በኩል በህወሀት አርማና በወያኔ ሰንደቃላማዎች ያሸበረቀች ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በየመንገዱ ላይ ጠመንጃ አንግበዉ የሚርመሰመሱት ወታደሮችና መንገዱን ያጣበቡት ወታደራዊ  ፒክ አፕ መኪናዎች ከተማዋን አጨናንቀዋታል። ጭራሽ ይህም አልበቃ ብሏቸዉ የወያኔ ካድሬዎች ከቤት ወደ ቤት እየተዘዋወሩ ህዝቡ የጉባኤዉን ማብቃት አስመልክቶ ድጋፉን ለህወሀት እንዲገልጽ በመወትወት ላይ መሆናቸዉን ዘጋበያችን አክሎ የላከልን ዜና ያስረዳል።  

            Posted By.Dawit Demelash