MINILIK SALSAWI (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ተጠፍጥፈው በወያኔ የተሰሩት የኢሕኣዴግ አባል ድርጅቶት እስከዛሬ እንዳልተዋሃዱ የሚታወቅ ነው:: እንዚህ ድርጅቶች ባለፉት 20 አመታት ውስጥ ያልተዋሃዱበት እና በአንድ ፓርቲ እና ግለሰብ ስር እየተሽከረከሩ የኖሩበት ሁኔታ በበረሃው የመሃላ ፖለቲካ አለምብሰላቸው ወደ ሕወሓት ስረወመንግስት ውሳኔ ሰጪነት ሳያሸጋግራቸው የፖለቲካ ባሮች እንደሆኑ አሉ::ርእዮት አለሙ እጅግ ወደ ኋላ የቀረ እና የአስተሳሰብ ጥልቀቶች አለመኖር ፓርታዊ ዲሞክራሲን ማእከል አለማድረጋቸው የውህደት ምህዳሩ እንዲደፈን እና ብሔር ተኮር የውህደት አደረጃጀት ወደ ሃገራዊ ፓርቲነት እንዳይለወጡ ለውህደቱ ዚግዛግ እደምታ አስከትሎበታል::ይህ ደሞ ሕወሓት የበላይነቱን እዳያጣ እና ስረወመንግስት እንዳይደረመስ ከመፍራት በመጣ የተቀነባበረ የፖለቲካ ሴራ ነው::
በባህር ዳር ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ያለው የኢሕኣዴግ ጉባኤ እጅግ በተጠንቀቅ እየተጠበቀ ሲሆን ፓርቲዎች ላለፉት አመታት እየተደረገባቸው ያለውን የፖለቲካ ጭቆና በተመለከተ ያፈነዱታል ተብሎ ተሰግቷል:: ለዚህን በአሁን ሰአት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል:: የግንባሩ አባል ድርጅቶች በሕወሃት ላይ ያላቸውን ጥላቻ ያንጸባርቁበታል ድርጅታዊ መብታቸን በፋት ይጠይቁበታል የተባለለት ይህ ጉባየ ሌሎች ችግሮችንም እንደሚወልድ እየተነገረለት ነው::እነዚሁ አባል ድርጅቶች “የህወሃት የበላይነት በእኩልነት” የሚል አዲስ አስተሳሰባቸውን ይዘው ስለሚቀላቀሉ ፍራቻውን ለማስወገድ ተሳታፊ አባላት ሲመረጡ ጥንቃቄ እንዲወሰድ ስራዎች ተሰርተዋል::በግንባሩ ላይ የለውጥ ተጸኖ ያሳድራሉ የተባሉ ተሳታፊዎች ወደ ባህር ዳር እንዳይዘልቁ በመደረጉ ችግሮች እንዳመረቀዙ ነው ያሉት::
ራሳቸውን ስልጣን ላይ ለማቆየት የተለያዩ መርሆዎችን የሚከተሉት ወያኔዎች በለውጥ ጎዳና የሄዳሉ ማለት ዘበት ነው::መርሆዎቻቸው የህብረተሰቡን መብቶች እና የሃገሪቱን የምጣኔሃብት እድገቶች ከማኮላሸት ዉጪ ምንም ፋይዳ የላቸውም::በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተመረዙ የፖለቲካ እና የምጣኔሃብት አጀንዳዎች ያሉት ኢህኣዴግ የዴሞክራሲ ተፈጥሮ ሰላለለው ስልጣኑ በእጁ ስላለ ባለስልጣኖቹ የህዝብን መብትና ንብረት ለጥቅማቸው አውለውታል:: እጅግ በሚደንቅ ሁኔታ ነጋዴ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለስልጣኖች Bank of Malaysia በከፈቱት አካውንት ከፍተኛ የዶላሮች ክምችት እንዳላቸው መረጃዎች ጠቆሙ:: በሃገር ውስጥ ያሉ የምእራባውያን ዲፕሎማቶች እይታዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት ራሳቸው በፈጠሩት በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ስም የተለያዩ አካውንቶች ውስጥ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እንዳስቀመጡ በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ የረድኤት ድርጅት ዲፕሎማቶቹ ያደረሱት መረጃ አመላክቷል::እንዲሁም በኳታር;በሲንጋፖር;በታይዋን;በቱርክ.. የተለያዩ የባንክ አካውንቶች ያሏቸው ሲሆን በምእራቡ አለም እምብዛም ባንኮችን አይጠቀሙም::
የመድበለ ፓርቲን በመርህ ደረጃ ብቻ የሚቀበለው ወያኔ ለመተግበር ስለሚከብደው ካድሬዎቹ በራሳቸው ድንጋጠ ውስጥ የከተታቸው ሲሆን ታማኝነቱን አጉድሎታል:;በምላሱ ብቻ የሚናገራቸው የዲሞክራሲ መርሆዎች ከካድሬዎቹ የፖለቲካ ማንነት ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል::
ባለፉት 20 አመታቶች ውስጥ ኢትዮጵያውያን እምነት እንዳጡበት ደጋግመው ያሳዩ ወያኔ አሁንም አስተማማኝ የተባለ መንገድን ለመጥረግ ዝግጁ ባለመሆኑ እና ጀሌዎቹም ባንድ ወጥ ውሳኔ አሰጣት ያልሰለጠኑ የፖለቲካ ታማኞች በመሆናቸው በቀታይነት ከወያኔ ምንም እንደማይጠበቅ የወቁ ብዙሃን ህዝቦች ይህን ስረወመንግስት ለመናድ በስፋት እየዘመቱ ይገኛል:;
በፍትህ ስርኣቱ ታማኝነቱ ተጠሪነቱ ለመንግስት መሆኑ አሁንም ዋና እና አነጋጋሪ ይርሆነ ጉዳይ ሲሆን ወያኔ ካለፉት መንግስታት ምንም አይነት የፍርድ ቤቶችን አሰራር በተመለከት ትምህርት አላመቅሰሙ ሊያስጠይቀው የሚገባ ጉዳይ ነው የደርግን መንግስት እንኳን ብንወስድ ቀይ ሽብርን የፈጸመው ከፍርድ ብት ውጪ እንደነበር እና ከዛም በሁዋላ በነበሩ ጊዜያት ታስረው የነበሩ ማናቸውም ሰዎች ከደርግ ጣልቃ ገብነት ውጭ ፍርድ ቤቶች የራሳቸውን ውሳኔ ይሰጡ እንደነበር የሚያውቁ ይመሰክራሉ::በአሁኑ ሰአት ግን እያንዳንዱ ህብረተሰብ በፍትህ ተቋማት ላይ ትልልልልቅ ጥያቄዎች እያነሳ ነው::
የወያኔ መንግስት በበረሃ ታግሎ የመጡት እና የድል አጥቢያ አርበኞት የእርስ በእርስ አለመተማመን ድርጅቱ እየፈረካከሱበት እንደሆነ እና ህዝቡ ዘንድ ያለውም ጥላቻ መስፋቱ ድንጋጠው እንዲበረታ ሲያደርጉት ከመሪው መለስ ሞት በኋላ መራባውያን በጥርጣሬ እያኡት መሆኑ ደሞ ስጋት ፈጥሮበታል:: ከመለስ ሞት በኋላ ነጻነታችንን እናገኛለን ብለው የነበሩት የግንባሩ አባል ድርጅቶች የህ/ማርያም ወደ ስልጣን መምጣት ስልጣናቸውን ለየክልላቸው ካለተጽእኖ እንደሚጠቀሙ እና ተሰሚነታችንም ከሕወሓት እኩ ይሆናል ብለው ቢገምቱን የመንግስቱ ስልጣኖች ሰፍተው እና አድገው በሕወሃት አመራሮች መያዛቸው ተስፋቸውን በማጨለሙ “ከሕወሓት የበላይነት ወደ እኩልነት የሚል እደምታ እንዲፈጠር ሆኗል:;
የኢሕኣዴግ አባላት እየተናቆሩ ያሉበት ያንድም ፓርቲ የማስወገድ ጥያቄ አሁንም ለማስቆም የወያኔ ጀሌዎች በካድረው ውስጥ ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ቢሆንም ሊሳካላቸው አልቻለም:: የአንዱ ከፍታ እና የአንዱ ዝቅታ አሁንም ጥያቄው እንዳልተፈታ ነው::
Posted By.Dawit Demelash

No comments:
Post a Comment