Saturday, March 16, 2013

የህወሀት መሪዎች በድርጅቱ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ ለመምከር መቀሌ ገቡ



March 16, 2013 


መለስ ዜናዊ ሞት ከተሰማበት ግዜ ጀምሮ ምሶሶዉ እንደተደረመሰበት ቤት እራሱን ችሎ መቆም ያቃተዉ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እንዴት ወደፊት መጓዝ እንዳለበትና መጪዉን የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ በተመለከተ ከአባላቱ ጋር ለመምከር በቅርቡ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤዉን እንደሚጀምር አስታወቀ።  በዚህ ከመጋቢት 8 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት መቀሌ ዉስጥ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀዉ የግንባሩ 11ኛ ጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ነባሮቹ የህወሀት መሪዎች መቀሌ በመግባት ላይ መሆናቸዉን የዘገበዉ የግንቦት ሰባት ድምጽ ዘጋቢ ገልጿል፣ ፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆነዉን ስዩም መስፍንን ጨምሮ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖምና ሌሎችም ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት መቀሌ ውስጥ መታየታቸውን የጠቀሰው ዘጋቢያችን  የመቀሌ ከተማ “ምን ይመጣ ይሆን” በሚል ፍርሀት መዋጧንና ነዋሪዉ ፊት ላይ ፍርሀት እንደሚነበብ ገልጿል።
የተከፋፈሉት የህወሀት መሪዎች በተከታታይ ስብሰባ ተቀምጠዉ ለ11ኛ ጉባኤያቸዉ የሚሆን አጀንዳ መቅረጽ ተስኗቸዉ ብዙ ከሰነበቱ በኋላ ከሰሞኑ ያለ አጀንዳ ከመሰብሰብ ያዳናቸዉን የግብር ይዉጣ አጀንዳ እንዳዘጋጁ ለማወቅ ተችሏል። መቀሌና ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ የህወሀት መከፋፈል በግልጽ እተነገረ ሲሆን ግንባሩ በዚህ እሁድ በሚጀመረዉ 11ኛ ጉባኤዉ ላይ ተአምር ሰርቶ አንድነቱን ካላረጋገጠ ደደቢት ዉስጥ የተጠነሰሰዉ ህወሀት መጨረሻዉ መቀሌ ዉስጥ ሊጀመር ይችላል ብለዉ የሚያምኑ ለህወሀት ቅርበት ያላቸዉ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደገመቱ ዘጋቢያንች ከመቀሌ የላከልን ዜና ያስረዳል።
በአሁኑ ወቅት አንጋፋዋ የመቀሌ ከተማ በአንድ በኩል በህወሀት አርማና በወያኔ ሰንደቃላማዎች ያሸበረቀች ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በየመንገዱ ላይ ጠመንጃ አንግበዉ የሚርመሰመሱት ወታደሮችና መንገዱን ያጣበቡት ወታደራዊ  ፒክ አፕ መኪናዎች ከተማዋን አጨናንቀዋታል። ጭራሽ ይህም አልበቃ ብሏቸዉ የወያኔ ካድሬዎች ከቤት ወደ ቤት እየተዘዋወሩ ህዝቡ የጉባኤዉን ማብቃት አስመልክቶ ድጋፉን ለህወሀት እንዲገልጽ በመወትወት ላይ መሆናቸዉን ዘጋበያችን አክሎ የላከልን ዜና ያስረዳል።  

            Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment