በሲዊዲን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ
በስቶኮልም ሲዊድን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን የሰልፍ አስተባባሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም የተደረገው የተዋውሞ ሰልፍ አላማ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን በደል ለመቃወም መሆኑን የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ከ 200 በላይ በስቶኮልምና በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መገኘታቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
ሰልፉን ያስተባበሩት በስዊዲን የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎች ጋር በመተባበር ሲሆን ሰልፉን የክርስትና እምነት ተከታዮችም በርከት ብለው በመታደም አጋርነታቸውን ገልፀውበታል፡፡
በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተደረገው በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ “ድምጻችን ይሰማ በስቶኮልም ከተማ”፣ “ሀገር በህግ እንጂ በሀሰት ፊልም አይመራም”፣ “ኢትዮጵያ የሁላችንም ሀገር ናት”፣ “ኮሚቴዎቻችን ህጋዊ ናቸው፤ እነሱን አሸባሪ ማለት ሁሉንም የኢትዮጵያ ሙስሊም አሸባሪ ማለት ነው” የሚሉና የተለያዩ መፈክሮችም ተስተጋብተዋል፡፡
Posted By.Dawit Demelash

No comments:
Post a Comment