ወር በገባ ዘወትር በ 3 የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን የሚዘክረው የሻማ ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድነት ፕርቲ ዋና ፅህፈት ቤት ውጭ ተከበረ፡፡ ስነስርዓቱ “አንድ ታጋይ ቢታሰር ሺ ታጋይ ይተካል! “በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
ዝግጅቱ የተካሄደው መጋቢት 3 ቀን 2005ዓ.ም. አዲስ አበባ ቄራ አካባቢ በመገኘት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የመኢአድ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ፣ የታሳሪ ቤተሰቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የአንድነት ፓርቲ አባላትና የተለያዩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ በተደረገው የሻማ ማብራት ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህ የሚደረገው የሻማ ስነስርዓት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ከመጠየቅ በተጨማሪ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአመለካከቱ ብቻ መታሰር እንደሌለበትና ይህንንም ኡ …ኡ.. እያ..ኢያ ደበርሳ (በኦሮሚኛ) ጩኹና ጩኸታችንን አስተጋቡ (በአማርኛ) በማለት ሁላችንም በጋራ ለመብቶቻችን መጨሁ አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ እንግዳ ሆነው የተጋበዙት የመኢአድ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ ወንድማገኝ ፣ የአንድነት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ሻለቃ አርጋው ካብታሙ እና የባለዕራይ ወጣቶች መኀበር ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ አያሌው ንግግር አድርገዋል፡፡
Posted By.Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment