ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝብንና አገርን የሚጠቅም ስራ መስራት እንደማይቻል የጀርመን ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ተናገሩ
የኢትዮጵያ መንግስት ከጾታ እኩልነትና ከሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጋር የምንሰራዉን ስራ ለመግታት እራሱ ከጻፈዉ ህገመንግስት ጋር የሚጻረር ህግ አዉጥቷል ያሉት ሚስተር ፓትሪክ በርግ አገዛዙ ነገሮችን የሚያየዉ ህዝብን ይጠቃማል ወይስ ይጎዳል ብሎ ሳይሆን ከራሱ የስልጣን ዘመን ጋር እያስተያየ ስለሆነ ከዚህ አይነት አገዛዝ ጋር ምንም አይነት ህዝብንና አገርን የሚጠቅም ስራ መስራት አይቻልም ብለዋል።
ድርጀቱን ወክሎ ከሚስትር ፓትሪክ በርግ ጋር የተወያየዉ የብሉምበርጉ ሚስትር ዊልያም ዳቪሰን ደግሞ የሲቪክ ሶሳይቲና ቻርቲ ህግ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ውርስ መሆኑን ተናግሮ ህጉ የወጣዉ ከመንግስት የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ተቃዋሚዎችና ምግባረ ሰናይ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ነዉ በማለት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን በመጥቀስ ተናግሯል።
በሌላ በኩል ደግሞ የሂውማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል በቀለ ፣ መንግስት ያወጣው የሲቪክ ሶሳይቲና ቻሪቲ ህግ ዋና ግቡ በአገር ውስጥ ካለው ፖለቲካና ሲቪክ ሶሳይቲ ስራ ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የሆነዉ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ህጉ በሙስና የተዘፈቁ የሲቪክ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ተብሎ የተረቀቀ መሆኑን በመግለጽ፣ የወያኔን አቋም አንጸባርቋል።
Posted By.Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment