በሰሜን ጎንደር መተማና አካባቢው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በራሪ ወረቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ሲሆን ፣ የወያኔ ካድሬዎችም ድርጊቱን ለማስቆም የተጠናከረ አሰሳ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በመላ ሀገሪቱ እየታየ ያለው የሕዝብ መነሳሳት ስሜትና ተጋድሎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከለውጥ ፈላጊው ሕዝብ ጎን የቆመ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያቶች በጠላት ላይ በሚያደርሰው ጥቃት የሀገርና የወገን ደራሽነቱን ያስመሰከረ ሲሆን፣ ከወታደራዊ ትግሉ ጎን ለጎን የአካባቢውን ህብረተሰብ የማስተማር፣ የመቀስቀስ፣ የማደራጀትና የማስታጠቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገለፀ።
በሰሜን ጎንደር መተማና አካባቢው በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛች ግንባር ደጋፊዎች አማካኝነት የድርጅቱ ወቅታዊ የሀገር አድን ጥሪ በራሪ ወረቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ በመገኘቱ ስጋት የገባው አሸባሪው የወያኔ ገዥ ቡድን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ወከባና እንግልት እያደረሰ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን የመረጃ ምንጭ ያስረዳል
Posted By.Dawit Demelash
|
No comments:
Post a Comment