Wednesday, April 30, 2014

ቅስቀሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል -ፖሊስ እውቅና የተሰጠውን የሰላማዊ ሰልፍ የበራሪ ወረቀት ቅስቀሳ ለማስተጓጎል እየሞከረ ነው::

ሜክሲኮ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሊያሰራጩ የተንቀሳቀሱ አባላትን ፖሊስ 5 ፖሊስ ጣቢያ አገተ፡፡ 1- ዳንኤል ፈይሳ 2- አበበ ቑምላቸው 3- አብነት ረጋሳ 4- ሳሙኤል ይትባረክ 5- አያክሉህም ጀንበሩ 6- ዳግማዊ ተሰማ 7- ዳዊት አለሙ







http://www.zehabesha.com/amharic/archives/29663



University students protest the new Addis Abeba Master Plan



(ESAT News) Several university students in Ambo, Jimma, Nekemt and others are protesting the new Addis Abeba City Master Plan, which the City believes will reduce the City’s land shortage problems.

Students in Wellega University have been injured due to actions taken by securities.
Gebru Gebremariam, former MP and current Deputy Chairman of the Oromo Federalist Congress said to ESAT that although it was so not clear whether the protests were organised or not, there are ongoing protests.

Gebru said that it was necessary to give proper response to the questions of the people rather than raising issues and claiming that my way is the only way. He also warned that care should be taken so that the problems do not lead to ethnic conflict.


Source: ESAT

http://www.zehabesha.com/university-students-protest-the-new-addis-abeba-master-plan/

Tuesday, April 29, 2014

ፖሊስ የጣይቱ ልጆችን ለማሸማቀቅ እየጣረ ነው


April 29, 2014

ሚያዝያ 19/2006 . ለተደረገው ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ፖሊስ ‹‹የእውቅና ደብዳቤው አልደረሰኝም፣ ህገ ወጦች ናችሁ!›› ብሎ ያሰራቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት (የጣይቱ ልጆች) ላይ ፖሊስ የተለያዩ የማሸማቀቂያ ስልቶችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ በዛሬው ቀን ፖሊስ ታሳዎቹን በተለይም ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንዲፍራውን ‹‹እስር ቤቱን በመረበሽ›› በሚል ሌላ ክስ ከግቢ አስወጥተው ቃል ተቀብለዋቸዋል፡፡ በወቅቱም ማስፈራራትና ዛቻ እንደደረሰባቸው ታሳሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

የጣይቱ ልጆች በታላቁ ሩጫ ላይ በፖሊስ በተያዙበት ወቅት ፖሊስ የተለያዩ በደሎችን ለመፈጸም ሲጥር መብታቸውን ለማስከበር ባደረጉት ጥረት ፖሊሶች ሌሊት ከግቢ አስወጥተው የድብደባና ሌሎች ማስፈራሪዎችን እንዳደረጉባቸው ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ምግብ እንዳይገባላቸው፣ ቤተሰብ እዳይጠይቃቸውና ሌሎችንም መብታቸውን የሚጋፉ በደሎች እየተፈጸሙባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
 
Young semayawi party female activists

http://ecadforum.com/Amharic/archives/12050/

ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ – ኢህአዴግ አሁንም በሶማሊያ ያስፈራራ ይሆን?

 

ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችን “አገር በማተራመስ” ወንጀል ከሰሰ
kerry 1
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጉዞ በርካታ ጉዳዮች የሚከናወኑበት እንደሆነ ተጠቆመ። የዘወትር የጎልጉል ምንጭ አንዳሉት የኬሪ አዲስ አበባ ጉዞ አስቀድመው የተሰሩ ስራዎች ውጤት ነው። ጥቁሩ ሰው “ውሻ ምንም ሳይመለከት አይጮህም” ሲሉ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ብቃት ያላቸው አማራጮች መሆናቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ኢህአዴግ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እንደለመደው “ከሶማሊያ ጦሬን አወጣለሁ” በማለት መደራደሪያ ከማቅረብ ውጪ ሌላ አቅም እንደሌለው ተገለጸ። ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች “አገር በማተራመስ” ወንጀል ክስ መሰረተባቸው።
የድረገጽና የማህበራዊ ገጽ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚ አባላት ባይዋጥላቸውም አሜሪካና ኢህአዴግ የነበራቸው ግንኙነት እየሻከረ መሔዱን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የዋሽንግቶን ዲፕሎማት ምንጩን በመጥቀስ እንደዘገበው አሜሪካ ኢህአዴግን “የምስራቅ አፍሪካ ስጋት” አድርጋም ፈርጃለች። የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተለውና በስቴት ዲፓርትመንት ውስጥ የተቋቋመው የቀውስ መከላከልና ዕርቅ ቢሮ ሃላፊ ከጥር ወር ወዲህ ባሉት ጥቂት ወራት ውስጥ አራት ጊዜ አዲስ አበባ ተጉዘዋል።
ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ፍትሃዊነት የጎደለው አገዛዝ ኢትዮጵያን ወደ ቀውስ እንዳመራትና ይኸው ቀውስ እልባት ካልተበጀለት የምስራቅ አፍሪካን የሚያዳርስ እንደሚሆን በአሜሪካ በኩል አቋም መያዙ ኢህአዴግን እንዳስበረገገው ተንታኞች እየገለጹ ነው። የምስራቅ አፍሪካ “የሰላም አባት ነኝ የሚለው ኢህአዴግ በውስጣዊ የፖለቲካ ቀውስ ስለሚገኝ የመወላለቅ ችግር ሳይገጠመው በፊት አሜሪካ አስቀድማ ስራዋን መስራት መጀመሯ ከራሷ ጥቅም አንጻር ነው” ሲሉ ዲፕሎማቱ እንደቀድሞው ሁሉ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል። የኬሪ ጉዞም የዚሁ አካል እንደሆነ አስታውዋል። “ኢህአዴግ” አሉ ዲፕሎማቱ “የቀለም አብዮት እያለ እንደሚደነፋው ሳይሆን በመጪው ምርጫ በሩን ከፍቶ ለመወዳደር ከተስማማ ብቻ የለመደው ርጥባን ይሰጠዋል የሚል ግምት አለኝ” ብለዋል።
በ97 ምርጫ ወቅት እንዳደረገው በሶማሊያ ያለውን አለመረጋጋት እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም ጦሩን የማስወጣት ርምጃ ቢወስድስ? በሚል ለተጠየቁት “ኢህአዴግ የመጫወቻ ካርዶቹ ያለቁበት ይመስለኛል” በማለት የግሌ ያሉትን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ኢህአዴግ በምርጫ 97 ተደራደር ሲባል ጦሩን ሰብስቦ ለመውጣት በዝግጅት ላይ እንደሆነ መግለጹን የተለያዩ የውጪ አገር ሚዲያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም።
obang-o-metho-hearingየአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ “ውሻ ከጮኸ የሆነ ነገር አለ ማለት ነው” ሲሉ ለጎልጉል አስተያየት ሰጥተዋል። ኦባንግ አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህንን ጩኸት ሰምተው ህዝብን በማስቀደም ራሳቸውን አማራጭ አድርገው እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል። አማራጭ የለም የሚለውን ፍርሃቻ በመስበር ወቅቱን ለህዝብና ለአገር ጥቅም ለማዋል እንዲተጉ አሳስበዋል። የሚመሩት ድርጅት በቅርቡ በዚህ ዙሪያ የሚለው ነገር ስላለ ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ ከመግባት ተቆጥበዋል።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በመጥቀስ የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው ኬሪ፤ ሃይለማርያም ደሳለኝን፣ ቴድሮስ አድሃኖምንና የሚመለከታቸውን ባለስልጣናት በሰብአዊ መብት አያያዝና በዲሞክራሲ ትግበራ ዙሪያ እንደሚያነጋግሩ ማረጋገጫ መሰጠቱን ጠቁሟል። በዚሁ ዜና ላይ ቃላቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ኬሪ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጋር ይነጋገራሉ የሚል ስጋት እንዳለባቸው የሚያሳብቅ መልስ ሰጥተዋል። ኬሪ የዞን9 ድረገጽና ማህበራዊ ድር ጦማሪዎች እስርን አስመልክቶ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ጆን ኬሪ ስለ ዞን9 አባላት እስር ሊያነሱ እንደሚችሉ ተጠይቀው “እንደምናከብረው መሪ ጥያቄውን ካቀረቡ አስፈላጊውን መልስ እንሰጣለን” ካሉ በኋላ “የዞን9 ጦማሪዎች በጋዜጠኛነታቸው አልታሰሩም” በማለት ከገጀራና ከስርቆት ወንጀል ጋር በማዛመድ ለማቃለል ሞክረዋል።
getachew
ጌታቸው ረዳ
አገዛዙ ዝም ማለቱን አስመልክቶ “የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረገ ሴል ቢኖር መግለጫ እናወጣለን” ሲሉ የመለሱት አቶ ጌታቸው፣ ጆን ኬሪ የእስረኞቹን ጉዳይ እንዲያነሱ ያሳሰበውን ሂውማን ራይትስ ዎችን “ልማዱ ነው” ሲሉ ዘልፈዋል።
የዞን9 አባላትን ታፍኖ መወሰድና በአገር ማተራመስ ወንጀል መከሰሳቸውን የሰሙ “ኢህአዴግ ማንንም ለአገር ተቆርቋሪ ሆኖ የመወንጀል ሞራላዊ ብቃት የለውም” በማለት ነው አስተያየታቸውን የሚጀምሩት። ኢህአዴግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አሁን አስከደረሰበት ደረጃ ድረስ ዜጎችን በአገር ክህደት የመፈረጅ ብቃት ከቶውንም እንደሌለው ራሱም ጭምር የሚያወቀው እውነት እንደሆነ የደረሱን አስተያየቶች ያመላክታሉ።
ያለፈው እሁድ አራዳ ምድብ አንደኛ ችሎት የቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማሪዎች በሶስት የተለያዩ መዝገቦች መከሰሳቸው የጀርመን ሬዲዮ ይፋ አድርጓል። ከታሰሩ በኋላ ከቤተሰብና ከተመልካች ተሰውረው ምርመራ ሲደረግባቸው የነበሩት የዞን9 ጦማሪዎች አስመልከቶ ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የራሳቸው በሆነው የዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ ክስ ከመመስረቱ በፊት ስለተከሰሱበት ጉዳይ የፖሊስ ምንጭ ጠቅሰው መናገራቸውን ቪኦኤ ተናግሯል።
ወ/ሮ ሚሚን ጠቅሶ የዞን9 ጦማሪዎች አርቲክል 19 ከሚባለው ተቋም ጋር ግንኙነት ያላቸውና የተለያዩ አገራት ሄደው የሰለጠኑ መሆናቸውን፣ በአገሪቱ ትርምስ ለመፍጠር በሻዕቢያና በግብጽ በገንዘብ እንደሚረዱ ቪኦኤ በዘገበ ማግስት ነው ፖሊስ በተመሳሳይ የክስ መዝገብ የተጨማሪ ቀጠሮ ቀን የጠየቀባቸው። የዞን 9 ጦማሪዎች ኢህአዴግ ላይ ጠንካራ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ ናቸው።
“አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን አባላት ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ በበነጋው ደግሞ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስም በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘዋል፡፡ታሳሪዎቹን ለመያዝ የመጡት አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን መስማታቸውን በዚሁ አጭር መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።
zone9“ዞን 9” የጦማርያን ስብስብ አባላት ሚያዚያ 15፣2006 ባወጣነው መግለጫ ላለፉት ሰባት ወራት የዞኑ አባላት ከፍተኛ የሆነ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር በጠቅላላው የተጠቆመ ሲሆን ክትትሉ የተወሰኑ የቡድኑን አባላትና የቅርብ ወዳጆችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የዞኑን ተመልሶ ወደ ስራ መግባት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም የዞን 9 አባላትና ወዳጆች በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንዳልነበር ለማረጋገጥ እንወዳለ” በማለት በራሳቸው የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ዜና አሰራጭተው ነበር።
በተመሳሳይ ዜና ቻይናን “ቃል የገባሽውን ብር አምጪ” ብሎ የሙጥኝ የያዘው ኢህአዴግ “ቀለም ይፈራል” ሲሉም በቅርብ የሚከታተሉ እየተቹት ነው። “ሆድ በባሰው ቁጥር የቀለም አብዮት ” በማለት ቅስቀሳ የሚያዘወትረው ኢህአዴግ አሁን ያስፈራው የትኛው ቀለም እንደሆነ በይፋ ባይገልጽም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑትን ኢንጂነር ይልቃል “ተስፋ የተጣለባቸው ወጣት መሪዎች” በሚል ተመርጠው ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር አሜሪካ ለስልጠናና ለልምድ ልውውጥ መጋበዛቸው፣ ወደ ስፍራው እንዳያመሩ መደረጉ፣ እንዲሁም አሁን በድፍረት የሚንቀሳቀሱና የሚያስተባብሩ መሆናቸው አንዱ የስጋት ምንጭ ሊሆን አንደሚችል ግምት አለ።
“የቀለም አብዮት ሰለባዎች” በሚል ርዕስ ኢህአዴግ ዩክሬንን አስታኮ ያሰራጨው ቪዲዮ አሜሪካንን በሽብር ስራ የማሰልጠን ክህሎት ያላት፣ ሽብርተኞች አገርን አንዲያተራምሱ በመደገፍ የሚታወቁ ተቋማት ባለቤት የሆነች አገር ብሎ መፈረጁ አይዘነጋም። ኢህአዴግ ተንታኝ አድርጎ ያቀረባቸው ጎረምሶች አሜሪካንና የምዕራብ አገሮችን ሲዘልፉ የሚያሳየው ፊልም መጨረሻው “ከፊል የዩክሬን ህዝብ ራስን በራስ በመወሰን መብቱ ተጠቅሞ የቀድሞ አካሉን ሩሲያን ተቀላቀለ” በሚል መሆኑና ጉዳዩ ከአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ተዛምዶ መቋጨቱ የኢህአዴግን በተለይም የህወሃትን ስጋት እንደሚያጎላው የሚያሳይ እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠበት ነው። በሕገመንግሥቱ አገር እንድትበታተን በአንቀጽ 39 በግልጽ አስቀምጦ እስካሁን ኢትዮጵያን በ“ነጻ አውጪ ግምባር” ስም የሚመራውና “የነጻ አውጪ ግምባሩን” መሪ ወደ ተባበሩት መንግሥታት በመላክ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል ዓለምን የለመነው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “የቀለም አብዮት ሰለባዎች” በማለት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ ከሶቪየት ህብረት የተገነጠለችውና የዩክሬን አካል የነበረችው ክሬሚያ ወደ እናት አገሯ ሩሲያ መመለሷን አብሮ ማሰራጨቱ ዘጋቢ ፊልሙን ዋጋቢስ የሚያደርገው መሆኑን አለማስተዋሉ በራሱ ሌላ ዘጋቢ ፊልም የሚያሰራ ነው፡፡
 
 

Monday, April 28, 2014

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

(አዲስ ጉዳይ) ፖሊስ ለምርመራ 10 ቀናት ጠይቋል ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 . በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች ዕሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 . አራዳ ፍርድ ቤት 1 ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በማዕከላዊ እስር ቤት የቆዩት ተጠርጣሪዎች ሰኞ ለፍርድ እንደሚቀርቡ የተጠበቀ ቢሆንም ባልተለመደ ሁኔታ ዕሁድ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን የክሱም ሃሳብ በአጭሩሀገሪቱን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሃሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማምተው የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋልየሚል ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ተመሳሳይ ክስ የቀረበባቸው ቢሆንም 3 የተለያዩ መዝገቦች ተከፋፍለው ነው ፍርድ ቤት ቀረቡት፡፡ የአዲስጉዳይ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆነው ዘላለም ክብረት እና የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጠኛና በአሁኑ ወቅት በአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ላይ የሚሰራው ተስፋለም ወልደየስ በመዝገብ ቁጥር 118722 የተጠቃለሉ ሲሆን፤ አጥናፉ ብርሃነ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና ኤዶም ካሣ በመዝገብ ቁጥር 118721 እንዲሁም በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው።


በመዝገብ ቁጥር 118721 እና መዝገብ ቁጥር 118722 የተካተቱት ተጠርጣሪዎች ለሚያዝያ 29 ቀን 2006 ተቀጥረዋል። ጉዳያቸው በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተተው ተጠርጣሪዎች ደግሞ ለሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓመተምህረት ተቀጥረዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/29599

Friday, April 25, 2014


Six members of Zone Nine, group of bloggers and  activists, have been  arnested today late in the afternoon at 5:20 pm by Ethiopian security. Team members Befeqadu Hailu, Atnaf Berahane, Mahlet Fantahun, Zelalem Kiberet, Natnael Feleke and Abel Wabela are all under custody on arrest warrant.
The arrest comes immediately after the bloggers and activists notified their return to their usual activism on April 23, 2014 after their inactivity for the past seven months. On their return note the group indicated that they have sustained a considerable amount of surveillance and harassment. They have indicated that one of their reasons for their disappearance from activism is the harassment they have been receiving from government security agents.

De Birhan has also learnt that journalist Tesfalem Waldyes has also been detained this afternoon.

We believe members and friends of Zone Nine have nothing to do with illegal activities and we request the government to release them immediately.


ዛሬ አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 1120 ገደማ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን አባላት የሆኑት ጓደኞቻችን በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘዋል፡፡ እነርሱም ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ ናቸው፡፡ ጦማርያኑን ጓደኞቻችን ለማሰር የመጡት አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን ሰምተናልአ መደበኛ የሆነውዞን 9” የጦማርያን ስብስብ አባላት ሚያዚያ 152006 በዋጣነው መግለጫ ላለፉት ሰባት ወራት የዞኑ አባላት ከፍተኛ የሆነ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር በጠቅላላው የተጠቆመ ሲሆን ክትትሉ የተወሰኑ የቡድኑን አባላትና የቅርብ ወዳጆችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የዞኑን ተመልሶ ወደ ስራ መግባት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም የዞን 9 አባላትና ወዳጆች በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እነዳልነበር ለማረጋገጥ እንወዳለ፡፡ በመሆኑም የታሰሩ የዞኑ አባላትና ወዳጆች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡

http://debirhan.com/?p=4491