Wednesday, April 23, 2014

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ የጠራውን ሰልፍ እኛ በምንለው መሠረት ካላደረጋችሁ ፎርም አትሞሉም አለ (ደብዳቤውን ይዘናል)

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ / ቤት በዛሬው ቀን ለሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ፎርም መሙላት አለባችሁ በሚል ጥሪ አድርጎ የነበረ ቢሆን ወደ ቢሮው ካቀኑ በኋላ ‹‹ሰልፉን የምታደርጉት እኛ በምንለው መሰረት ካልሆነ ፎርሙን አትሞሉም›› እንዳላቸው ታውቋል፡፡ አመራሮቹም ደብዳቤ በጻፋችሁልን መሰረት ፎርሙን ካልሞላን ከቢሮ አንወጣም ብለዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ቅስቀሳውና ሌሎች ለሰላማዊ ሰልፉ የሚደረጉት ዝግጅቶች አሁንም ቀጥለዋል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/29392

No comments:

Post a Comment