Monday, April 14, 2014

የኢህአዴግ “አሸባሪነት”በ2007 ምርጫ ማንን ያስር ይሆን?

ሳሙኤል ተወልደ በርሔ/ሃርስታድ ኖርዌይ/

ሰው በላው የኢህአዴግአሸባሪነት2007 ምርጫ ምን እየቆመረ ይሆን?…ኢህአዴግ  ስልጣኑን ከተቃውሞም ሆነ ከነፃው ፕሬስ ወቀሳ የሚያረጋጋበት በርካታ -ፖለቲካዊ (-ዴሞክራሲያዊ) አካሔዶች አሉት፡፡ ኢህአዴግ እንደቀደምቶቹ የኢትዮጵያ መንግስታት ሁሉ የተቃውሙትን ፖለቲከኞች አስሯል፤ በዩኒቨርስቲ ውስጥ የአካዳሚ ነፃነታቸውን የጠየቁ ተማሪዎችን በፖሊስ አስደብድቧል፤ ከፍ ሲልም በእስር አሰቃይቷል፡፡ ብዙዎችንም በፖለቲካ አመለካከታቸው (በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ) ከገዛ ሀገራቸው እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ ንቁ  የፖለቲካ ተሳትፎ በሚያደርግ አባወራ ምክንያት የቤተሰቡ አባላት ከፍተኛ ወከባ እና እንግልት እንዲደርስባቸው አስደርጓል፡፡

1997 . ምርጫ ውጤት ፍፁም ወደተቃዋሚዎች ማጋደሉን የተመለከተው እና ስልጣኑ አደጋ ላይ መውደቁን የተገነዘበው ኢህአዴግ 97 . በኋላ እስከአሁን ድረስ ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ አስጨናቂ ማድረጉ የአደባባይ ሐቅ ነው፡፡ ከአስጨናቂ እና ከኢ-ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ርምጃው መካከል በዋነኝነት ሊጠቀስ የሚችለው ደግሞአሸባሪነትየሚለው ታፔላው ነው፡፡

በዚህ ሰው በላ ሐሳዊ ፍረጃውም ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን፣ ሞጋች የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞችንባጠቃላይ ስልጣኔን በዓይነ ቁራኛ ይመለከቱብኛል ብሎ ቀይ መስመር ያሰመረባቸውን ሰዎች አስሮ አስቀምጧቸዋል፡፡

በዚህ ስጋቱ የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ 2007 . በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ ብሎ የሚገምታቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም የነፃው ፕሬስ  ሞጋች ጋዜጠኞችን አሸባሪነትሰበብ እየቀፈደደ ወህኒ ሊያወርዳቸው እንደሚችል የማይጠረጥር የኢህአዴግን አስከፊ የፖለቲካ ስነ-ባህሪ የማያውቅ ብቻ ነው፡፡

ይህን ያልኩት ያለ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡ 1997 . የምሁራን ስብስብ በነበረው ቅንጅት የደረሰበት ወደር አልባ ሽንፈት ዳግም እንዲደገምበት ስለማይፈልግ ለስልጣኑ የሚያሰጉ ፓርቲዎችን (አመራሮቻቸውን) አነፍንፎ ከመያዝ ወደ ኋላ አይልም፡፡
በዚህም የተነሳ 2007ቱን ብሔራዊ ምርጫ ተቃዋሚዎች እንደፈለጉ እንዲሆኑበት እና የነፃው  ፕሬስ አባላት በነፃነት እንዲዘግቡት ሁኔታዎችን ያመቻቻል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ እናም 97  . ምርጫ ለወህኒ ቤት እንደተገበሩት ተቃዋሚዎች እና ጋዜጠኞች 2007ቱም ምርጫ እንደ አድባር የሚገበሩ ተቃዋሚዎች እና ጋዜጠኞች አይጠፉም፡፡ ጥያቄው ይገበራሉ ወይስ አይገበሩም? የሚለው ሳይሆን፤ እነማን ይገበራሉ? የሚለው ነው፡፡

ደርግ በዘመነ ስልጣኑ የተቃውሞ ድምፅ ሲያሰሙት የነበሩ ሰዎችንአድኃሪ፣ አወናባጅ…” ወዘተ እያለ ይፈርጅ ነበር፡፡ ፈርጆ ሲያበቃምአድኃሪዎችምኖች፣ ምናምኖች ያላቸውን ሰዎች  ከማሰርና ከመደብደብ አልፎ እስከ መግደል የደረሰ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ደርግ እንዲያ ሲፈርጅ፣ ሲገድል፣ ሲያስር፣ ሲደበድብ የነበረው ለህልውናው ስለሚሰጋ ነበር፡፡

እየፈረጀ ባያስር፣ እያሰረ ባይገድልየተቃውሞ ድምፅ የሚያሰሙ ወገኖች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ስልጣኑ (ህልውናው) አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስለሚያምን የስልጣን ትንኮሳ ለሚያደርጉበት ሰዎች እንቅልፍ የለውም ነበር፡፡ ጃንሆይም ተቃውሞ ያሰሙባቸው የነበሩ  የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችንፀረ ዘውድ፣ ፀረ ንጉስ…” እያሉ በመፈረጅ ለህልውናቸው ማቆያ  ወይም ለስልጣን ማረጋጊያ የሚያግዙ ርምጃዎችን ይተገብሩባቸው ነበር፡፡

እነሆ ኢህአዴግምከማን አንሼበሚል ስሜት የሰላ ሂስ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን፣ ለስልጣኔ  (ለወንበሬ) ያሰጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን እያደነ አሸባሪነትስም ወህኒ ያወርዳቸው  ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በጋዜጠኞቹ በእነ እስክንድር ነጋ እስር (“የአሸባሪነት ታፔላ”)  ነፃውን ፕሬስ ለማስበርገግ፣ በፖለቲከኞቹ በእነ አንዷለም አራጌ ተመሳሳይ ታፔላ የተቃውሞውን መንደር ለማስደንበር መላ ዘይዶ የተነሳው ገዢው ፓርቲአሸባሪየሚለውን ሰበብ የህልውናው ማስጠበቂያዘበኛሳያደርገው የቀረ አይመስለኝም፡፡

ጋዜጠኞች አሸባሪነትስም ወህኒ በወረዱ ቁጥር መንግስት የሰላ ሂስ ከሚሰነዝሩ የነፃው  ፕሬስ አባላት ሂስነፃእየወጣ ይሄዳል፡፡ እንዲሁ ከፍተኛ የህዝብ ቅቡልነት የተቀዳጁ  የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችአሸባሪበሚል ሰረገላ ወህኒ ሲወርዱ ገዥው ፓርቲ የስልጣን ማገሩን ይበልጥ እየተከለው እና እያጠበቀው ይመጣል፡፡ ታዲያ አሸባሪነትበላይ  የመንግስትን ህልውና (ስልጣን) እያስጠበቀ ያለ ዘብ ይኖር ይሆን?

ኢህአዴግአሸባሪነት ለብቻው የሚረዳበት (የሚተረጉምበት) የተለየ መዝገበ ቃላት እንዳለው የምናውቀው የነ አሜሪካን አቋም በአንክሮ የገመገምን ዕለት ነው፡፡ እንደሚታወቀው አሜሪካና  ኢትዮጵያየጸረ ሽብርአጋር ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስትአሸባሪእያለ የሚያስራቸውን ጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሜሪካአዎ! አሸባሪ ናቸውብላ አታምንም፡፡
ይባስ ብላበሽብርተኝነትስም የታሰሩ ጋዜጠኞችን እና ፖለቲከኞችን በአስቸኳይ ይፈታ ዘንድ የኢትዮጵያን መንግስት ያሳሰበችበት ጊዜ በርካታ ነው፡፡ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትም የኢትዮጵያ መንግስትሽብርተኛእያለ ወህኒ የወረወራቸውን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች  “ጀግናእያሉ ሲሸልሟቸው ነው የምናስተውለው፡፡

ከዚህ እውነታ የምንገነዘበው ኢህአዴግ ራሱ በፈለሰፈው እና የተቀረው አለም በማይስማማበትሽብርተኝነትስም እየነገደ መሆኑን ነው፡፡ አዎ! ሽብርን እና አሸባሪዎችን የማይጠየፍ ጤነኛ  ሰው የለም፡፡ ነገር ግን ኢህአዴግአሸባሪየሚለውን ቃል የሚተረጉምበት መዝገበ ቃላቱ  ከሌላው አለም የተለየ በመሆኑ ሰርክ እንደተወገዘበት ነው የሚገኘው፡፡

አንድ የማውቃቸው ባለትዳሮች ነበሩ። ምንም እንኳን ዛሬ ተነጣጥለው ለየብቻ መኖር ቢጀምሩም፤ ሚስትየው ባሏ መጠጥ እንዲያቆም ያልተሳለችው ስለት እና ያላንኳኳችው የቤተክርስቲያን በር የለም። ከዚህም ሌላ ጠዋት ከቤት ሊወጣ (ወደ ስራ ሊሄድ ሲል) እግሩን ከመላስ በማይተናነስ መልኩ ማታ ጠጥቶና ሰክሮ እንዳይመጣ ትወተውተዋለች፣ ትለምነዋለች፣ ታስጠነቅቀዋለች።
ውትወታዋም ሆነ ልመናዋ እንዳልሰመረ የምትረዳው ማታ ወደ ቤት ሲመጣ ሰክሮ እየተንገዳገደ  መሆኑን ስትመለከት ነው።

ጠዋት ሲወጣ አስጠንቅቃው ማታ ሲገባ የሚሰክረው ለምንና ምን በድላው እንደሆነ ስትጠይቀው `ሰይጣን አሳስቶኝ ነው` ይላታል በመጠጥ የተላወሰው ምላሱ  እየተደናቀፈበት። እሱ እየሰከረ እሷ እየመከረችና እየለመነች ለአንድ አመት ያህል አብረው ቢኖሩም, መፋታታቸው ግን አልቀረም ነበር። አብረው በኖሩባቸው ወቅቶች ጠጥቶ ሲመጣ `ለምን?` ማለቷን አትተውም ነበር። `ሰይጣን አሳስቶኝ ነው` የሚለው ቃል የዘወትር መልሱና ሰበቡ መሆኑን የተገነዘበችው ሚስት `ምን አለበት ለአንድ ቀን እንኳን ሰበብህን ለወጥ ብታደርገው? ሁልጊዜ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው እያልክስ ለምን ታሞኘኛለህ?` ብላ በተናገረች ማግስት እቃዋን ይዛ ላትመለስ ተለየችው።

እውነት ነው! አመቱን ሙሉ ወይም ለአመታት በአንድ በማይለወጥና በማይሻር ሰበብ  አድራጎታችንን (ስህተታችንን) እየሸፋፈንን ለመቀጠል የምናደርገው ሙከራ ሰበባችንን  በሚያደምጠው ሰው ላይ የማይሰረይ መሰላቸት ይፈጥራል። ሁልጊዜ በአንድ ሰበብ ለመጓዝ መሞከር ፋራነታችንን እና አራዳ አለመሆናችንን ያሳብቅብናል።

በማይለወጥ ሰበባቸው (ምክንያታቸው) ልንጠቅሳቸው ከምችላቸው አካላት ደግሞ ገዥያችን ኢህአዴግ አንዱ ነው። ኢህአዴግ መንግስት እንደመሆኑ የአገሪቱን ፀጥታና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ (አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በርከት ለሚሉ አንዳንድ ጊዜዎች) ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ሙስሊሙን ወክለው የሚንቀሳቀሱ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ሲከስስ ወይም ሲያስር እንደ ምክንያት (ሰበብ) የሚያስቀምጣቸው መልሶች  እጅግ ተመሳሳይ እና ማሻሻያ የማይደረግባቸው ናቸው። ጋዜጠኛን ሲያስር ‹‹ህገ-መንስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል (በሽብር) ለመናድ ሲቀሳቀስ…›› የምትል የተለመደችውን ምክንያት ያስቀምጣል። ይህ ምክንያት ጋዜጠኛውን ለመክሰሻ አገልግሎት ብቻ የሚውል አይደለም። ተቃዋሚዎችን ሲያስርም ‹‹ሽብርተኛ›› የምትለውን ቃል ለመክሰሻ ፍጆታው ያውላታል። በአሁን ሰአት በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙን ተወካዮች ሲያስር እንደ ምክንያት የተጠቀመው ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን ለመክሰስ የደረደራቸውን ሰበቦቹን ነው።

ከላይ የባለትዳሮቹን የህይወት ተሞክሮ ያነሳሁት ያለ ምክንያት አይደለም። ከኢህአዴግ ምክንያት ድርደራ ጋር ተቀራራቢ (ተመሳሳይ) ባህሪ ስላለው ነው እንጂ። ሚስት ‹‹ሰይጣን አሳስቶኝ ነው›› በሚለው የባሏ ቋሚ ተሰላፊ ሰበብ ትዳሯን እስከመናድ ያደረሰ መሰላቸት  አሳድሮባታል።

1997 . የምርጫ ውጤቱ ወደ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካጋደለና ሁኔታዎች ወደአላስፈላጊ አቅጣጫ ከዞሩ በኋላ በርካታ ተቃወሚዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች ወህኒ ወርደዋል። የዛን ጊዜ የታሰሩበት ምክንያት ‹‹ህገ-መንግስቱን እንደ ሾላ በድንጋይ ለማውረድ…›› የሚል ነበር። 1997 . ጥሎን ከነጎደ ዛሬ ወደ ስምንት አመት ሆኖታል። በነዚህ ስምንት አመታቶች ውስጥ ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው፣ ኑሮው፣ የሰው አስተሳሰብበውድቀትና በእድገት ምህዋር ውስጥ ወይ ወደ ላይ ወጥቷል፤ አሊያም ወደታች ወርዷል። በአጠቃላይ ሁኔታው ተለውጧል፤ ተለዋውጧል።ህገ-መንግስቱንና ህገ-መግስታዊ ስርዓቱን በሀይል (በሽብር) ለመናድ ሲንቀሳቀሱ…›› በመንግስታችን ቋንቋ፤ የቁመት፣ የወርድ፣ የመጠን ለውጥ ሳይደረግባት ይኸው እስከዛሬ እንዳለች አለች። ኢህአዴግ ወደፊት እስከሚኖርበት ጊዜ ድረስም አብራው ትኖራለች፤ ሰንደቁና አርማው ናትና አትጠፋም። ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚዎች፣ ‹‹እምቢየው›› መብቴን የሚሉ ዜጎች ከኢትዮጵያ ምድር  ሲጠፉ ብቻ ነው ያቺ የኢህአዴግ ምክንያት ‹‹በክብር›› ወደ ማህደሯ የምትመለሰው። እስከዚያው ድረስ ግን፤ እንደ ርዕዮተ አለም የተያዘችው ምክንያት ሳትከለስ፣ ሳትበረዝም ሆነ ተሐድሶ ሳይደረግባት በዶግማ (Doctrine) መልክ ትቀጥላለች።

የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ‹‹መንግስት በሽብርተኝነት ሊያስረን እንደሆነ ከታማኝ ምንጮቻችን ሰማን›› ብለው አገር ጥለው ከተሰደዱ በኋላ፤ እንዳሉትም በሌሉበት በሽብርተኝነት ተከስሰውና ‹‹ሽብርተኛ›› ተብለው ተፈርዶባቸዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርእዮት አለሙ ተከስሰው የተፈረደባቸው ‹‹ሽብርተኛ›› በምትለዋና ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረቦች በተለጠፈችው ቦሎ ነው። አንድ ጋዜጠኛ ሲታሰር የክሱ ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ የግድ የሚመለከተው አካል መግለጫ እስኪሰጥ መጠበቅ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። አሁን አሁን እከሌ የሚባል ጋዜጠኛ ታሰረ የሚል ወሬ ሲሰማ፤ ያው ‹‹በሽብርተኝነት›› እንደሚከሰስ አስቀድሞ ማረጋገጥ እየተለመደ መጥቷል። ይህ እንዲሆን በር የከፈተው መንግስታችን በተለይም 1997 ምርጫ በኋላ እየተከተለው የመጣው ተሐድሶ አልባ ምክንያቱ (ሰበቡ) ነው።
ለአዲስ ነገር ጋዜጠኞች ክስ የተጠቀመውን ምክንያት ለእስክንድር ነጋ፣ ለእስክንድር ነጋ  የተጠቀመውን ለርዕዮት አለሙለውብሸት ታዬነገ  ደግሞ አንድ ጋዜጠኛ ሲታሰር፤ ለእሱም ፍጆታ ያውለዋል።

በአንድ ተመሳሳይ ምክንያት የተለያዩ ጋዜጠኞችን ማሰር አይሰለችም? የሰው ልጅ አንዴ፣ ሁለቴና ሶስቴ በሰይጣንሊሳሳትይችል ይሆናል። ግን እንዴት ዘለአለአም በሰይጣን እየተሳሳተ ይኖራልእያንዳንዱ ጋዜጠኛስ እንዴት ‹‹ሽብርተኛ›› ሊሆን ይችላል?
በደርግ ጊዜ ነው አሉ፤ ‹‹አንድ ሰው አይደለም በጤናው ሰክሮ እንኳን የመንግስቱ ኃይለማርያምን አስተዳደር መውቀስም ሆነ መተቸት አይችልም ነበር ይባላል።ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋልየሚለው አባባል በደርግ ጊዜ አይሰራም ነበር።ሲሉ አንድ አባት አጫውተውኛል። ደርግ ከተገረሰሰ ከሃያ ሁለት አመታት በኋላ ማለትም ዛሬ፤ ያውምዴሞክራሲና ነፃነት ያለገደብ መስፈኑበሚነገርበት በዚህ ጊዜ ሳይሰክሩ መንግስትን መተቸት ከባድ እየሆነ መጥቷል። ከባዱን መከራ እጋፈጠዋለሁ ያለ ጋዜጠኛም ‹‹ያቺ ነገር›› ትመዘዝለታለች።

እንግዲህ በደርግና በኢህአዴግ መካከል ያለውን ልዩነት እንመርምር። በደርግ ጊዜ ተሰክሮም ሆነ ሳይሰከር ትችት እሰነዝራለሁ ማለት ከባድ ነበር። በኢህአዴግ ጊዜ ዲሞክራሲውያለ ገደብ”  በመንሰራፋቱ፣ በገደብ ሰክረው ያለገደብ የመንግስትን ስህተት መተቸት ይቻላል። ታዲያ  በመጠጥ ስካር እንጂ በኑሮው ንረት፣ በመልካም አስተዳደር ችግር፣ በመኖሪያ ቤት እጥረት ስካር መንግስትን ማማረር፣ ከማማረርም አልፎ ለተቃውሞ መውጣትህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች…” ለሚል የክስ ፋይል አሳልፎ ይሰጣል። መቼም አሜሪካና አውሮፓ የሽብርተኞች ደጋፊና አፍቃሪ ስለሆኑ አይደለም-የኢትዮጵያ መንግስትአሸባሪያላቸውን እነ እስክንድርን እየሸለሙ ያሉት፡፡ እናም ኢህአዴግ ሆይ! የተበላች ዕቁብ የመሰለችውን ምክንያትህን (አሸባሪነትን) ቀየር ብታደርጋትስ?!…


 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/29135




No comments:

Post a Comment