Monday, April 28, 2014

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

(አዲስ ጉዳይ) ፖሊስ ለምርመራ 10 ቀናት ጠይቋል ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 . በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች ዕሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 . አራዳ ፍርድ ቤት 1 ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በማዕከላዊ እስር ቤት የቆዩት ተጠርጣሪዎች ሰኞ ለፍርድ እንደሚቀርቡ የተጠበቀ ቢሆንም ባልተለመደ ሁኔታ ዕሁድ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን የክሱም ሃሳብ በአጭሩሀገሪቱን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሃሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማምተው የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋልየሚል ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ተመሳሳይ ክስ የቀረበባቸው ቢሆንም 3 የተለያዩ መዝገቦች ተከፋፍለው ነው ፍርድ ቤት ቀረቡት፡፡ የአዲስጉዳይ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆነው ዘላለም ክብረት እና የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጠኛና በአሁኑ ወቅት በአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ላይ የሚሰራው ተስፋለም ወልደየስ በመዝገብ ቁጥር 118722 የተጠቃለሉ ሲሆን፤ አጥናፉ ብርሃነ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና ኤዶም ካሣ በመዝገብ ቁጥር 118721 እንዲሁም በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው።


በመዝገብ ቁጥር 118721 እና መዝገብ ቁጥር 118722 የተካተቱት ተጠርጣሪዎች ለሚያዝያ 29 ቀን 2006 ተቀጥረዋል። ጉዳያቸው በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተተው ተጠርጣሪዎች ደግሞ ለሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓመተምህረት ተቀጥረዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/29599

No comments:

Post a Comment