Wednesday, April 9, 2014

ሰበር ዜና – የአዲስ አበባ መስተዳድር የእውቅና ደብዳቤ ጻፈ ፓርቲው አልተስማማም::

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 . ሊያደርገው ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የመስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍና ማሳወቂያ ክፍል ዘግይቶ በጻፈው ደብዳቤ የሰልፉ ቀን በሌላ ፕሮግራም መያዙን በመጥቀስ የቀን ለውጥ እንዲደረግ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡

ፓርቲው የቀረበውን አስተያየት በመቀበል ሰልፉ ለሚያዚያ 5 ቀን 2006 . እንዲደረግ መወሰኑን በመግለጽ ለመስተዳድሩ አሳውቋል፡፡ሆኖም መስተዳድሩ ዕለቱ በታላቁ ሩጫ መያዙን በመጥቀስ ለፖሊስ ጥበቃ ለመስጠት የሚያስቸግረው በመሆኑ ሰልፉ ለሚያዚያ 4 ቀን 2006 . እንዲደረግ የእውቅና ደብዳቤ ጽፏል፡፡ፓርቲው በመስተዳድሩ የተሰጠውን እውቅና አለመቀበሉን ለማሳወቅ ከፍተኛ አመራሮቹን ወደ ከንቲባው /ቤት ልኳል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም አመራሮቹና የመስተዳድሩ ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ እየተነጋገሩ ነው፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/28987

No comments:

Post a Comment