Friday, May 9, 2014

በግንቦት ወር የተከሰቱ 11 ታሪካዊ ሁነቶች ያውቁ ነበር ?


ከአቤኔዘር ይስሃቅ
1. ግንቦት 1, 1947 . ሀገራቸውን ከድተው ለጣሊያን በባንዳነት ሲያገለግሉ የነበሩት የአስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ የነበረው የቀድሞው አምባ-ገነኑ፣ ከፋፋዩና ጎጠኛው መሪ ለገሰ/መለስ/ ዜናዊ የተወለደበት ቀን።

2. ግንቦት 8, 1981 . የሀገሪቱ ጄኔራሎች በመንግስቱ ሀይለማሪያም ላይ የመፍንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉበት ቀን።

3. ግንቦት 8, 1982 . በመንግስቱ ኃይለማሪያም ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት ጄኔራሎች የተረሽኑበት ቀን።

4. ግንቦት 13, 1983 . አምባ-ገነኑ፣ ሰው በላውና ጨፍጫፊው መንግስቱ ኃይለማሪያም ሀገሪቱን ጥሎ ወደ ዚምባቡዌ የፈረጠጠበት ቀን።

5. ግንቦት 16, 1983 . ሻዕቢያ የኢትዮዽያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የነበረችውን አሥመራን የተቆጣጠረበት ቀን።

6. ግንቦት 20, 1983 . አምባ-ገነኑ ኢህአዴግ የቀድሞውን አምባ-ገነን ደርግን የተካበት ቀን።

7. ግንቦት 4, 1990 . ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የወረረበት ቀን።

8. ግንቦት 7, 1997 . የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በነቂስ ወጥቶ በምርጫ የራሱን መሪዎች የመረጠበት ቀን። /በኋላ ኢህአዴግ ቢያጭበርብረንም/

9. ግንቦት 7, 1997 . ማታ ላይ መለስ የራሱን ሕገ-መንግስት ጥሶ ከግንቦት 8, 1997 . ጀምሮ ምንም አይነት ከቤት ውጪ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መከልከሉን ያወጀበት ቀን። 8 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከመለስ ሞት በኋላ በመለስ የታወጀው ሕገ-ወጥ ክልከላ እንዲሻር ማድረጉ ይታወቃል።

10. ግንቦት 8, 1997 . በሀገሪቱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የምርጫ ቆጠራው ሳይጠናቀቅና ምርጫ ቦርድም ምንም አይነት መግለጫ ከመስጠቱ በፊት ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ በቀር በሁሉም የሀገሪቱ ክልል ምርጫውን ማሸነፉን በጉልበት ያወጀበት ቀን።

11. ግንቦት 10, 2004 . አበበ ገላው በአሜሪካ የመለስን ቀልብ የገፈፈበትና መለስም በአደባባይ ሲደነግጥ የታየበት ቀን። ከድንጋጤው ሳያገግም ከዚያ በፊት የነበረበት ህመም ተባብሶበት 2 ወር በኋላ በዚያው ሞተ። የተረሳ ካለ ጨምሩበት።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30111

No comments:

Post a Comment