Monday, May 26, 2014

ወያኔ በ«ዐማራ ክልል» ለኤች. አይ. ቪ. ኤድስ በሽታ መከላከያ ብሎየሚያሠራጨው መድኃኒት በሽታውን የማይከላከል መሆኑ ተገለጠ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

እሑድ ግንቦት ቀን ፪ሺህ፮ ..(Sunday May 18, 2014)

በሲያትል ከተማ (ዋሽንግተን ግዛት) በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማዕከል፣ ከሕዝብ የመተዋወቂያ ሕዝባዊ ስብሰባ አዘጋጅቶ ነበር። በዚያ ስብሰባ ወቅት ከተሰብሰባዊዎቹ አንዱ የሆኑና በሙያቸው ሐኪም የሆኑ ለተሰብሳቢው እንደገለጹት፣ በዐማራው ክልል ለኤችኢቪ በሽታ መከላከያ እየተባለ የሚታደለው መድኃኒት ከበሽታው ጋር ምንዓይነት ግንኙነት የሌለው፣ አልፎ አልፎም ጊዜው ያለፈበት መሆኑን በጥናት የደረሱበት መሆኑን ገልጠዋል። ይህ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በዐማራው ነገድ ላይ በሽታውን ሆን ብሎ በማስፋፋት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ እንደሆነ የሚያመለክት መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል።

ባለሙያው ከዚህ በማያያዝም የኤች. አይ. . ኤድስን ወረርሽኝ ለመከላከል በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የገንዘብ ዕርዳታ፣ የቁሣቁስ እና የባለሙያ እገዛ እንደሚያደርግ አውስተው፣ ሆኖም ከተደረጉት ጥናቶች እንደተገነዘቡት ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው ገንዘብ እና ዕርዳታ ለተገቢው ግልጋሎት ያለመዋሉን እንዳረጋገጡ ገልፀዋል። ስለሆነም በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ፣ በተለይም ዐማራው፣ ይህ ከፍተኛ የሆነ የአሜሪካ ታክስ ከፋይ ገንዘብ፣ ተገቢ ላልሆነ እና ሕዝብን ለሚያጠፋ ተግባር እየዋለ መሆኑን ለሕዝብ ተወካዮቻቸው እና ለሴናተሮቻቸው ባሉት የመገኛና ዘዴዎች ሁሉ በመጠቀም ማሳወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ከሁሉም በላይ ለቫይረሱ መከላከያ ተብሎ የሚሠራጨው መድኋኒት  ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚበልጥ ስለሆነ የአሜሪካ መንግሥት ለዚህ ተግባር የሚልከው ዕርዳታ ለተፈላጊው ግልጋሎት ያልዋለ መሆኑን አውቆ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ የዐማራው ነገድ አባላት ድምፃቸውን በተቀነባበረ መንገድ እይዲያሰሙ ሁኔታዎች  በአስቸኳይ  እንዲመቻቹ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በዚህ ዙሪያ በርትቶ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል። በዚህ ረገድ ሰብአዊነት  የሚሰማው ሰው ሁሉ፣ በተለይም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት የዐማራ ነገድ ተወላጆች፣ የተባበረ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ባለሙያው በእልህና በቁጭት ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም ባለው መረጃ በመመርኮዝ «የኤች. አይ. . ኤድስን በሽታ ለመከላከል» በሚል ስም በሕዝብ ላይ ሆን ብለው እና አቅደው የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ የትግሬ-ወያኔ ባለሥልጣኖች ለፍርድ እንዲቀርቡ  ኢትዮጵያውያን ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ በአፅንዖት ተማፅነዋል።

በዕለቱ በሲያትል የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አዳራሽ የታደሙት የስብሰባው ተካፋዮች በሰሙት ዜና ከመገረም አልፈው፣ በዚህ በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም ሕዝብ ከደረሰበት ዕድገት እና የሥልጣኔ ደረጃ ላይ ሆኖ ለሚያስብ ሰው፣ «ይህ ድርጊት ዛሬ ይፈጸማል» ብሎ ለማመን አስቸጋሪ እንደሆነባቸው አስተያየታቸውን አስደምጠዋል። ቢሆንም፣ በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ያልተፈጸመ አሰቃቂ የወንጀል ዓይነት ስለሌለ፣ በጥናት የቀረበውን መረጃ ከማስተባበል ይልቅ ተዓማኒነቱ እንደሚያመዝን ገልፀዋል። ስለዚህ ሁኔታውን በፍጥነት የዓለም ሕዝብ እንዲያውቀው፣ በተለይም «ጉዳዩ ይመለከተናል» የሚሉ ወገኖች በአፋጣኝ የመፍትሔ ዕርምጃ እንዲወስዱ ተሰብሳቢዎቹ ተማፅነዋል።

በዕለቱ የስብሰባው አስረጅ ሆነው የቀረቡት የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ተክሌ የሻውም፣ የሰሙት መረጃ የትግሬ-ወያኔ በዐማራ ነገድ ተወላጆች ላይ ሰንቆት ከመጣው ሥር የሠደደ ጥላቻ አንፃር ብዙም ድብ-ዕዳ እንዳልሆነባቸው ጠቁመዋል። እንዲያውም የትግሬ-ወያኔ፥ ዐማራን፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖትን እና የአማርኛ ቋንቋን ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት ከአቀደው ዕቅድ፣ አልፎም በተግባርም በመፈጸም ላይ ካለው አጠቃላይ የጥፋት ዘመቻ አንጻር ብዙም የሚያስገርም ያለመሆኑን አውስተዋል። በመሆኑም ይህንን ድርጊት ለሚፈፅመው ናዚያዊ አገዛዝ በታቀደ ሁኔታ ከፍተኛ ዕርዳት ለሚሰጡ መንግሥታት እና ዓለምአቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ሁኔታውን ለማሣወቅ ሞረሽ ወገኔ አቅሙ የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። አቶ ተክሌ አክለውም የዚህ ዓይነት መረጃ ያላቸው ሰዎች እና በተለይም የሕክምና ባለሙያዎች፣ ከሞረሽ ወገኔ ጋር በመተባበር ድርጊቱን ማስቆም የሚቻልበትን ሥራ ሁሉ በጋራ እንዲሠሩ በተጎጅው ሕዝብ ስም ጥሪ አቅርበዋል። ይህ የዘር ማጥፋት ድርጊት ዐማራ ለሆነ ሰው ብቻ ሣይሆን፣ ማንኛውንም ሰብአዊነት ያለውን ፍጡር ሁሉ የሚያስቆጭ እና የሚያናድድ በመሆኑ ድርጊቱን ለማስቆም የሚደረግን ማናቸውም ዓይነት እንቅስቃሴ ከመደገፍ ባሻገር፣ በግንባር ቀደምትነት መቆም አስፈላጊ መሆኑን አቶ ተክሌ አስገንዝበዋል።

በስብሰባው የታደሙት የሲያትል ነዋሪዎች ስለወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እና በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመ ስላለው አጠቃላይ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ዘመቻ ከስብሰባው አስረጂ ከተረዱ በኋላ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አቅርበው ከመድረኩ ተገቢ መልሶች ተሰጥተዋል። በአገኟቸው መልሶች የረኩት እና የድርጅቱን ዓላማ የተቀበሉት አብዛኛዎቹ ታዳሚዎች የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት አባል ለመሆን አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በማሟላት ድርጅቱን ተቀላቅለዋል፤ በሲያትል-ዋሽንግተን የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መሠረታዊ ማኅበርንም በይፋ መሥርተዋል።

ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በታማኝ ልጆቿ ጽናት እና ትግል ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30661

1 comment: