Friday, May 30, 2014

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዛሬ የተቃውሞ ድምጻቸውን በአዲስ አበባ ሲያሰሙ ዋሉ (ፎቶዎች ይዘናል)

(-ሐበሻ) ‹‹እኛም ኮሚቴው ነንፍትህ ለኮሚቴዎቻችን›› በሚል በፒያሳ ኑር መስጂድና በክልል መስጂዶች በዛሬው ዕለት የተቃውሞ መርሀ ግብሮች ተደረጉ። በተለይ በአዲስ አበባ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ባደረጉት ተቃውሞ የታሰሩት ኮሜቴዎቻቸው እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።

በአዲስ አበባ ደግሞ በፒያሳው ኑር መስጂድ (ሰፈር በኒን) አጋርነትን የማሳያ ታላቅ በተደረገው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ዋና አላማ የታሰረው ኮሚቴው ህዝበ ሙስሊሙ፣ ህዝበ ሙስሊሙም ኮሚቴው መሆኑን ዳግም ማሳየት እንደሆነ ድምጻችን ይሰማ ማስታወቁ አይዘነጋም።

የአርብ ጸሎታቸውን እንዳጠናቀቁ እጅ እጅ በመያያዝ 5 ደቂቃ ተቃውሟቸውን የገለጹት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች 5 ደቂቃ ያህልም እጃቸውን በማቆላለፍ የታስረናል ምልክት አሳይተዋል። እንደዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከሆነም ፈጣሪ እልህ እና ድፍረት ከፍትህ ጋር እንዲሰጣቸው በመጸለይ ተቃውሟቸውን በሰላም አጠናቀው ወደየቤታቸው ሄደዋል።

ፎቶዎችን ይመልከቱ








http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30808

No comments:

Post a Comment