Saturday, April 11, 2015

በሰሜን ጎንደር የጦር መሳሪያ ሽያጭ መጧጧፉ ተሰማ


በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የጦር መሳሪያ ሽያጭ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጧጡፎ በመሸጥ ላይ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

በአለፋ ፣ ጣቁሳ፣ መተማ፣ አርማጭሆ፣ ቋራና በሌሎችም በርካታ ወረዳዎች አንድ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ45 ሺ እስከ 60 ሺ ብር በመሸጥ ላይ ነው። የጦር መሳሪያዎችን በብዛት የሚገዙት አርሶ አደሮች ናቸው።

በርካታ ቁጥር ያለው የኢህአዴግ ወታደር በጠረፍ ከተሞች ውስጥ ከሰፈረ በሁዋላ የጦር መሳሪያ ሽያጩ መድራቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በቅርቡ በአርማጭሆ የታየው አለመረጋጋት ነዋሪዎች የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን እንዲገዙ ሳያስገድዳቸው እንደማይቀር አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ።

የኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተከታታይ የጦርነት ልምምድ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

መንግስት ሰሞኑን የክልሉ ነዋሪዎች የጦር መሳሪያዎቻቸውን አስመዝገበው ህጋዊ ፈቃድ እንዲይዙ መመሪያ አውጥቶ አንዳንድ ነዋሪዎች መሳሪያዎቻቸውን ሲያስመዘግቡ ታይቷል።

በሻውራ ከተማ ከሰፈሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል አንድ ጌጡ የተባለ ፖሊስ የኦነግ አባል ነህ ተብሎ በመጠርጠሩ ታስሮ ወደ አዲስ አበባ ተወስዷል።

ምንጭ  – ኢሳት ዜና

http://satenaw.com/amharic/archives/6168

No comments:

Post a Comment