Thursday, April 9, 2015

ኢትዮጵያዊቷ አይሁድ በእስራኤል የሰፈነውን ዘረኝነት እዋጋለሁ አሉ

በእስራኤል ፓርላማ ሲገቡ የመጀመሪዋ ሴት ትውልደ ኢትዮጵዊት አይሁድ የሆኑት የሽአዲስ ታመኑ ሽታ ዘረኝነትን እንደሚዋጉ ተናገሩ፡፡
ሴትየዋ ባገባደድነው ወር በእስራኤል ተካሂዶ በነበረው የፓርላማ ምርጫ በጥቂት ድምጾች ተሸንፈው ከፓርላማ እንደራሴነት ውጪ ቢሆኑም እንኳን ዘረኝነትን በየትም ቦታ ሆነው ለመዋጋት ነው ቃል የገቡት፡፡

የምሰራው ብዙ ስራ አለኝ ያሉት ወይዘሮዋ “የኔና የወገኖቼ የፊት ገጽ በዘረኝነት ወላፈን በሚገረፍበት ሀገር ውስጥ መኖር አልችልም” በማለት ነበር በፓርላማም ሆነ ከፓርላማ ውጪ ይህን አስከፊ ችግር ለመዋጋት እንደቆረጡ የተናገሩት፡፡

በእስራኤል ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አይሁዶች ከሀገሪቱ ህዝብ 1.5 በመቶ ብቻ የሚሸፍኑ ቢሆኑም በወታደራዊ አገልግሎትም ሆነ በበርካታ መንገዶች የዘር መድሎና መገለል እንደሚደርስባቸው ይነገራል፡፡ የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለኤችአይቪ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦች የደም ልገሳ አልቀበልም በሚል ትውልደ ኢትዮጵያውኑን አይሁዶች የደም ልገሳ ከልክሏል፡፡

ራሳቸው ወ/ሮ የሽአዲስ ታመኑ ሽታንም በቅርብ ጊዜያት የፓርላማ አባላት ደም ሲለግሱ እሳቸው እንዳይለግሱ ተከልክለው የነበረበት ሁኔታ ትልቅ ውዝግብ አስነስቶም ነበር፡፡

በሌላም በኩል በቅርብ ጊዜ የወጡ ዜናዎች የእስራኤል መንግስት ለትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ቁጥራቸውን ለመቀነስ በሚል የወሊድ መከላከያ ያለፈቃዳቸው ሲያስውጣቸው እንደከረመ ይፋ አድርገዋል፡፡


ይህንና ሌሎች አይን ያወጡ የዘር መድሎና ጥላቻ የመዋጋጥ ጥረቱ ታዲያ ለሴትየዋ ይሳካ ይሆንን? ጊዜ የሚመልሰው ነው የሚሆነው፡፡
http://satenaw.com/amharic/archives/6134

No comments:

Post a Comment