Wednesday, April 8, 2015

የአንዳርጋቸውን የትግል መንገድ ሚሊዮኖች ይከተላሉ። – ሳሙኤል አሊ (ከኖርዌይ)

ወደ በረሃ ወርዶ የሰራውን ስራ በፎቶዎቹ  እያየው ነው እነዚህን ፎቶዎችን ሳይ አይኔ በእንባ ይሞላሉ ልቤ በእልህ ይቀጣጠላል የተዘበራረቀ ስሜት ወደ ውስጤ ሲገባ ይታወቀኛል የደስታ ስሜት፣ የእልህ ስሜት፣ የቆራጥነት ስሜት፣ የጽናት ስሜት፣ የእውነተኝነት ስሜት ብቻ ምን ልበላቹህ ተደበላልቀው ውስጤን ይወጥሩታል እናም ፎቶዎቹን ሳያቸው የሚያወሩኝ ያህል ደስታን ይሰጡኛል 

አንድ ቀን ታድያ አንድ የጎረቤት አገር ሰው ሁል ጌዜ በተደጋጋሚ ጌዜ  የዚህን ሰውዬ ፎቶዎች  ተመስጠህ ታየዋለህ ለምንድነው አለኝ 

የኔም መልስ አይ ደስ ስለሚለኝ ነው አልኩት። እርሱም መልሶ ጥያቄወችን ይጠይቀኝ ጀመር አባትህ ነው? ዘመድህ ነው? ገበሬ ነው? ወዛደር ነው? ወታደር ነው? ምንድ ነው? ንገረኝ ደጋግመህ  ስታየው አባትህ ከሆነ  ብዬ ነው አልያም ዘመድህ  ደግሞ ይሄኘው   ፎቶ ገበሬ ደግሜ  ያኛው  ወዛደር ይሄኛው ደግሞ ወታደር ይመስላል ማን ነው ንገረኝ አለኝ እኔም ስመልስለት ልክ ብለሃል  እንደአባቴ የማየው አባት ያውም የኔ ብቻ ሳይሆን ነጻነት ለተጠሙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አባት ነው።  ከገበሬም ገበሬ ነው ስለገበሬው ነጻነት የሚታገል የገበሬው ወዳጅ ነው። ከወዛደርም ወዛደር ነው ድንጋይ እየተሸከመ እንጨት እየፈለጠ ወዛደሩን ለማሳደግ የሚተጋ የፍቅር አባት ነው። ከወታደርም ወታደር ነው ወዳጅን ሳይሆን ጠላትን በህዝብ አናት ላይ ቁጭ ብሎ በብረት ረግጦ የነገሰና የሚገዛን አገር አፍራሽ ለመገርሰስ ወታደር ሆኖ ለአገሩ ነጻነት ዘብ የቆመ  ብርቅዬና ውድ የኢትዮጵያ ወታደር ነው  ብዬ ገለጽኩለት። ስሙም አንዳርጋቸው ጽጌ  ይባላል  ስምን መለአክ ያወጣዋል ይባላል እውነት ነው ስምና ተግባርን አዋህዶ  የያዘ  የዘመኑ የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጅ ነው።

አንድ አርጋቸው ማለት የተራራቀን ማቀራረብ፣ የተለያየን ማገናኘት፣ ያልጸናን ማጽናት፣ የሚለውን ትርጉም ሲሰጠን። ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ ማለት ነው። ሲተረጉም  የአንድነት አበባ እንደውም  የትም የማይበቅለው ኢትዮ ጵያዊ አበባ የእግዛአብሔር ጸጋ የሚያበቅለው አደይ አበባችን ነው።

ታድያ ይህንን የኢትዮጵያ የሰላም ባንዲራ፣ የነጻነት መዝሙር፣ የፍቅር ቅኔ፣ የእውነት ታጋይ፣ የሆነውን ድንቅዬ መከታችንን  ከአመት በፊት የመኖች ሚልዮን ዶላሮችን ተቀብለው ለአገር አጥፊው እና ለአረመኔው ወያኔ አሳልፋ የሰጠችው አንዳርጋቸው ሰለ ኢትዮጵያ ነጻነት የታገለ  ታጋያችንን የመን አሳጣችን። በአሁኑ ሰዓት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ይገኛሉ። ወያኔ ግን ይሄን የወገን  ጥሪ የሚሰማበት ጆሮ አልፈጠረበትም። የዜጋቸው ደህንነት ያሳሰባቸውና ያስጨነቃቸው አገሮች ነገሩ ሳይብስ በጊዜው ዜጎቻቸውን አስወጥተዋል። ከ45 በላይ ኢትዮጵያን ግን የሚደርስላቸው አጥተው በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ አርበኛውን አንዳርጋቸው አፍኖ ለማምጣት የመን ድረስ አምርቶ  የነበረው ቦይንግ ዛሬ የጥይት ናዳ እየወረደባቸው ላለው ዜጎቻችን መድረስ አልቻለም።  አንዳርጋቸውን ለማሳፈኛ ለየመን ያወጡት በሚልዮን የሚቆጠር  ዶላር የዜጎቻችንን ነፍስ ለማዳን ሳይችሉ ቀርተዋል።  ይልቅ ለነሱ የወገን ድረሱልኝ ጥሪ ከወደ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በፌስ ቡክ መስኮት የተናገሩት ቢኖር ስልክ ቁጥር ነው። እንዴት አሳፋሪ ነገር እየሰሩ እናዳለ የሁል ግዜ ተግባራቸውን በድጋሚ አሳይተውናል።  እኔን ያሳዘነኝ ነገር የራሷን የቤት ስራ ሳትሰራ፣ የራሷን የውስጥ መረጋጋት ሳታመጣ፣ ሰለራሳ ሕዝብ ሳትጨነቅ፣ የኢትዮጵያን እውነተኛ ታጋይ አሳልፋ  መስጠትዋ <<የራስዋ አሮባት የሰው ታማስላለች>>  የሚለውን አባባል ያስታውሰኛል ቢሆንም ግን  የመን ለሰራችው ስራ ልትጠየቅ ይገባል።


አንዳርጋቸው በኢትዮጵያን ልቦና ውስጥ የፈጠረው የአንድነት መንፈስ ወያኔን የማስወገድ  ሃላፊነትን ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን መንገድ ያሳየ  በመሆኑ  እኛ ልጆችህ ያሰብከውን ዲሞክራስያዊት አገር የማየት ህልምህን እውን ለማድረግ በአንድ አንዳርጋቸው ምትክ ሚልዮኖች ተተክተው ወደትግሉ ጎራ ገብተናል። ገዳያችንን ልናጠፋ፣  አንባገነኖችን ልንገረስስ፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ  ቆርጠን ተነስተናል። እናም የተደወለው ደውል  የክተት ነውና  ሁሉም በያለበት  ወያኔ የተባለውን ሰው በላ አውሬ  ከኢትዮጵያ  ምድር እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ እና ጨርሶ እንዳያንሰራራ አድርጎ የማስወገድ ደውል ነውና  ሁላችንም ለዚህ ክተት ጥሪ ተሳታፊ ሆነን ትግሉን እንቀላቀል።  የነጻነት ታጋይ የአንዳርጋቸው ጽጌ ልጆች እንዳለን ዛሬ የምናሳይበት ጊዜ  ነውና ገዳያችንን ገለን፣ አሳዳጃችንን አሳደን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በስደት ከተበታተንበት ተሰባስበን በደስታና በሰላም የምንኖርባት  ዲሞክራሳዊት አገር እንዲኖረን ክተቱን ተቀብለን ነጻነታችንን እናመጣለን።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40372

No comments:

Post a Comment