Saturday, April 25, 2015

ሕወሓት የሚያስተዳድረው መንግስት በአ.አ ጨርቆስ አካባቢ በርካታ ወጣቶችን አፍሶ ወዳልታወቀ ሥፍራ ወሰደ


አይሲኤል በኢትዮጵያውያኑ የፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ በመቃወም ሰልፍ የወጡት የአዲስ አበባ ሰዎች መካከል በተለይ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች ዛሬ በጠዋቱ ሲታፈሱ መዋላቸውን ለዘ-ሐበሻ ከአዲስ አበባ የደረሰው መረጃ ጠቆመ::

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የለውጥ መነሳሳት ስሜትን በሰሞኑ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ የተመለከተው ሕወሓት መራሹ መንግስት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛል ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ቀጣዩን የውሸት ምርጫ ካለምንም ኮሽታ ለማሳለፍ ሲል ወጣቶችን በማሸበር ላይ ይገኛል ብለዋል::


ሕወሓት የሚያስተዳድረው መንግስት ዛሬ በጨርቆስ አካባቢ ከአንድ መቶ የማያንሱ ወጣቶችን አፍሶ የወሰደ ሲሆን የት እንደደረሱ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40863

No comments:

Post a Comment