Wednesday, February 6, 2013

መከላከያ ሰራዊት በባድሜ አቅራቢያ ልምምድ አደረገ

ጥር ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-መንግስት እንዳስታወቀው አድዋ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ልምምድ ያደረገው የሰራዊቱን ወቅታዊ ብቃት ለመገምገም ነው። ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የተካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ግምገማ ይፋ አልሆነም። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተመሳሳይ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ ነው።
የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ወታደራዊ ሀይላቸው እየፈረጠመ መምጣት መንግስትን ስጋት ላይ እንደጣለው ታዛቢዎች ይገልጻሉ። በየግንባሩ የሚገኙ አዛዦች ከሻእብያና ከጸረ ሰላም ሀይሎች የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች በአንድ ጊዜ ለመመከት የሚያስችል ብቃት ማዳበር አለብን እያሉ ለሰራዊቱ አባላት በመናገር ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በዘር ፖለቲካው የተናሳ ውስጡ በክፍፍል የተሞላ መሆኑ ይነገራል። ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት አሁን በሚታው ክፍፍል ሰራዊቱ ከማንኛውም ሀይል የሚሰነዘርበትን ጥቃት ለርጅም ጊዜ ለመመከት አይችልም።
98 በመቶ የሚሆኑት የመከላከያ ሰራዊት ዋና ዋና አዛዦች የህወሀት አባላት መሆናቸው መዘገቡ ይታወሳል።

 Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment