መሪ አልባዉ የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በስንዴ ግዢ ጉዳይ ሲጨቃጨቅ መክረሙ ተሰማ
ከዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ መሪ የሌለበት የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተብየው መፈራራትና መከባበር የሚባል ነገር ርቆት አባላቱ “ፕሮፓጋንዳ ይሻለናል” ወይስ “ሀቁን ተጋፍጠን መፍትሔ እንፈልግ” በሚሉ ሁለት ቡድኖች ተከፍሎ በየቀኑ ሲጨቃጨቅ እንደሚዉል ለካቢኔዉ ቅርበት ያለቸዉ የታመኑ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩልን ዜና ገለጹ። የስንዴው ፖለቲካ በሚል አርዕስት ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰዉ ዜና መሰረት የወያኔ አገዛዝ አገሪቱ ዉስጥ በኤኮኖሚዉና በማህበራዊ ዘርፎች እየደረሰ ያለዉን ቀዉስ መቆጣጠር አቅቶት አሁን ስራዬ ተብሎ የተያያዘዉ የእህል ውድነት በህዝቡ ላይ በተለይ ወያኔ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ብሎ በሚፈራዉ በከተማዉ ህዝብ ላይ ያስከተለውን ቀውስ በአስቸኳይ “ለማረጋጋት” ምን ያህል ስንዴ ከውጭ እንግዛ በሚል ጭቅጭቅ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮቹ አክልዉ በላኩልን ዜና ገልጸዋል ።
በዚህ ሳምንት ከወያኔ ጓዳ በደረሰን ዜና መሰረት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሚል በያዝነዉ ወር 850 ሺህ ኩንታል ስንዴ አገር ውስጥ ገብቷል። የዚህ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ወጥቶበት የተገዛዉ ስንዴ ጉዳይ ቀድሞዉንም በቋፍ የነበረዉን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጭራሽ ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ዉስጥ እንዲዘፈቅ አደርጎታል። በአንድ በኩል ግዢዉ የሚፈጥረዉ የዉጭ ምንዛሬ ጉድለት የባሰዉኑ የዋጋ ግሽበቱን ያባብሰዋል የሚሉ የካቢኔዉ አባላት ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ “ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ስንዴ ከውጭ አምጥተን አከፋፍለናል ሆኖም ምንም አይነት ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት አልቻልንም ብለዉ የሚከራከሩ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
ቁጥራቸዉ ትንሽ ቢሆንም ከእነዚህ ሁለት ቡድኖች ለየት ያለ አስተሳሰብ ያለቸዉና የአገሪቱ ችግር የገባቸዉ አንዳንድ የካቢኔዉ አባላት ደግሞ ችግራችን ስንዴ መግዘት ወይም ማምረት ሳይሆን የገዛነዉን ወይም ያመረትነዉን ስንዴ ለተጠቃሚዉ ህዝብ በሚገባ ማከፋፈል አለመቻላችን ነዉ የሚሉም አልታጡም። ለምሳሌ የወያኔ አገዛዝ እራሱ በሰጣቸዉ መግለጫዎች “በ1.5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ይመረታል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከ3 ሚሊየን ቶን በላይ ስንዴ ኢትዮጵያን ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በስንዴ ምርት ቀዳሚ ያደርጋታል፤ ችግሩ ግን ይህ ብዛት ያለዉ ስንዴም ሆነ ከዉጭ አገር ተገዝቶ የሚመጣዉ ስንዴ ዬት እንደሚገባ አይታወቀም።
ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን በተገኘዉ መረጃ መሰረት ገበያ ለማረጋጋት በሚል ሰበብ ስንዴ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገዛ አየር በአየር ወደ ሌላ አገር እየተዛወረ በመሸጥ ላይ ሲሆን ግዢውን የሚፈቅዱት፣የሚያስፈጽሙት፤ የሚያጓጉዙትና ብሎም ወደ ደቡብ ሱዳንና አረብ አገሮች እያወጡ የሚሸጡት፣ በዘርና በስጋ ዝምድና የተሳሰሩ የህወሀት ሰዎች መሆናቸው በገልጽ ይታወቃል።
መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረባቸዉ ግዜ ማንም ሰዉ ደፍሮ የማያነሳቸዉ ይንንና ይህንን የመሳሰሉ ጉዳዮች ዛሬ የመወያያ አርዕስቶች እየሆኑ በመምጣታቸዉ ስልጣን ከእጃችን ሊወጣ ይችላል በሚል ፍራቻ ብዙ የወያኔ ባለስልጣኖች አገሪቱን ባዶዋን እያስቀሯት መሆኑን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ፤ በተለይ ከአገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት የሚኮበልለዉ የዉጭ ምንዛሬ ብዛት ያሰጋቸዉ አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ አዳራ ያሉን የገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የህወሀት አባላት ዝርፍያ በዚህ ከቀጠለ በቅርብ ግዜ ዉስጥ የኢትዮጵያ የዉጭ ምንዛ ካዝና ባዶ ይሆናል ብለዋል።
Posted By.Dawit Demelash
መሪ አልባዉ የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በስንዴ ግዢ ጉዳይ ሲጨቃጨቅ መክረሙ ተሰማ
ከዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ መሪ የሌለበት የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተብየው መፈራራትና መከባበር የሚባል ነገር ርቆት አባላቱ “ፕሮፓጋንዳ ይሻለናል” ወይስ “ሀቁን ተጋፍጠን መፍትሔ እንፈልግ” በሚሉ ሁለት ቡድኖች ተከፍሎ በየቀኑ ሲጨቃጨቅ እንደሚዉል ለካቢኔዉ ቅርበት ያለቸዉ የታመኑ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩልን ዜና ገለጹ። የስንዴው ፖለቲካ በሚል አርዕስት ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰዉ ዜና መሰረት የወያኔ አገዛዝ አገሪቱ ዉስጥ በኤኮኖሚዉና በማህበራዊ ዘርፎች እየደረሰ ያለዉን ቀዉስ መቆጣጠር አቅቶት አሁን ስራዬ ተብሎ የተያያዘዉ የእህል ውድነት በህዝቡ ላይ በተለይ ወያኔ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ብሎ በሚፈራዉ በከተማዉ ህዝብ ላይ ያስከተለውን ቀውስ በአስቸኳይ “ለማረጋጋት” ምን ያህል ስንዴ ከውጭ እንግዛ በሚል ጭቅጭቅ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮቹ አክልዉ በላኩልን ዜና ገልጸዋል ።በዚህ ሳምንት ከወያኔ ጓዳ በደረሰን ዜና መሰረት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሚል በያዝነዉ ወር 850 ሺህ ኩንታል ስንዴ አገር ውስጥ ገብቷል። የዚህ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ወጥቶበት የተገዛዉ ስንዴ ጉዳይ ቀድሞዉንም በቋፍ የነበረዉን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጭራሽ ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ዉስጥ እንዲዘፈቅ አደርጎታል። በአንድ በኩል ግዢዉ የሚፈጥረዉ የዉጭ ምንዛሬ ጉድለት የባሰዉኑ የዋጋ ግሽበቱን ያባብሰዋል የሚሉ የካቢኔዉ አባላት ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ “ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ስንዴ ከውጭ አምጥተን አከፋፍለናል ሆኖም ምንም አይነት ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት አልቻልንም ብለዉ የሚከራከሩ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
ቁጥራቸዉ ትንሽ ቢሆንም ከእነዚህ ሁለት ቡድኖች ለየት ያለ አስተሳሰብ ያለቸዉና የአገሪቱ ችግር የገባቸዉ አንዳንድ የካቢኔዉ አባላት ደግሞ ችግራችን ስንዴ መግዘት ወይም ማምረት ሳይሆን የገዛነዉን ወይም ያመረትነዉን ስንዴ ለተጠቃሚዉ ህዝብ በሚገባ ማከፋፈል አለመቻላችን ነዉ የሚሉም አልታጡም። ለምሳሌ የወያኔ አገዛዝ እራሱ በሰጣቸዉ መግለጫዎች “በ1.5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ይመረታል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከ3 ሚሊየን ቶን በላይ ስንዴ ኢትዮጵያን ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በስንዴ ምርት ቀዳሚ ያደርጋታል፤ ችግሩ ግን ይህ ብዛት ያለዉ ስንዴም ሆነ ከዉጭ አገር ተገዝቶ የሚመጣዉ ስንዴ ዬት እንደሚገባ አይታወቀም።
ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን በተገኘዉ መረጃ መሰረት ገበያ ለማረጋጋት በሚል ሰበብ ስንዴ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገዛ አየር በአየር ወደ ሌላ አገር እየተዛወረ በመሸጥ ላይ ሲሆን ግዢውን የሚፈቅዱት፣የሚያስፈጽሙት፤ የሚያጓጉዙትና ብሎም ወደ ደቡብ ሱዳንና አረብ አገሮች እያወጡ የሚሸጡት፣ በዘርና በስጋ ዝምድና የተሳሰሩ የህወሀት ሰዎች መሆናቸው በገልጽ ይታወቃል።
መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረባቸዉ ግዜ ማንም ሰዉ ደፍሮ የማያነሳቸዉ ይንንና ይህንን የመሳሰሉ ጉዳዮች ዛሬ የመወያያ አርዕስቶች እየሆኑ በመምጣታቸዉ ስልጣን ከእጃችን ሊወጣ ይችላል በሚል ፍራቻ ብዙ የወያኔ ባለስልጣኖች አገሪቱን ባዶዋን እያስቀሯት መሆኑን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ፤ በተለይ ከአገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት የሚኮበልለዉ የዉጭ ምንዛሬ ብዛት ያሰጋቸዉ አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ አዳራ ያሉን የገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የህወሀት አባላት ዝርፍያ በዚህ ከቀጠለ በቅርብ ግዜ ዉስጥ የኢትዮጵያ የዉጭ ምንዛ ካዝና ባዶ ይሆናል ብለዋል።
Posted By.Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment