Friday, February 1, 2013


በሰደተኞች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል እንዲቆም ለግብጽ ፕረዚዳንት ደብዳቤ ተላከ

በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራና የሌሎችም ጎረቤት ሀገሮች ስደተኞች ግብጽ በሚገኘው የሲናይ በረሃ የሚደርስባቸው ወንጀል እንዲቆም የኤርትራው ህዝባዊ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ ለግብጹ ፕረዚዳንት ደብዳቤ ላከ።
2/1/13 — በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራና የሌሎችም ጎረቤት ሀገሮች ስደተኞች ግብጽ በሚገኘው የሲናይ በረሃ በድብቅ ሰዎችን በማሸጋገር ተግባር ላይ በተሰማሩ ሰዎች ብዙ ስቃይ እንደሚደርስባቸው ለህልፈትም እንደሚዳረጉ ይታወቃል። እንዲህ አይነቱ የወንጀል ተግባር እንዲቆም የኤርትራ ህዝባዊ  ዲሞክራስያዊ ፓርቲ የተባለው የኤርትራውያን ተቃዋሚ ድርጅት ለግብጹ ፕረዚዳንት መሐመድ ሞርሲ ደብዳቤ ልኳል። ይህን መሰረት በማድረግም  የፓርቲውን ሊቀመንበር አቶ መንግስተ-አብ አስመሮምን አነጋግረናልደብዳቤውን የላክነው ጥር 29 ቀን ነው። ምክንያቱም ባለፈው ማክሰኞ የግብጹ ፕረዚዳንት ጀርመንን ይጎበኛሉ በሚል ጠብቀን ነበር። ነገር ግን እሳቸው ባለፈው ረቡዕ ነው ጀርመንን የጎበኙት። ደብዳቤው ግን ለተለያዩ የግብጽ ባለስልጣኖችና በተለያዩ የአለም ማእዝናት ላሉት የግብጽ ኤምባሲዎች ተልኳል። በነሱ በኩል ደግሞ ለፕረዚዳንት ሙርሲ እንዲደርስልን ጠይቀናል ሲሉ አቶ መንግስተ-አብ አብራርተዋል።በሰተኞቹ ላይ ስለሚደርሰው  ስቃይና ወጀልም ዘርዝረዋል። "መጀመርያ ከኤርትራ፣ ከሱድን ወይም ከኢትዮጵያ ተጠልፈው በሲናይ በረሀ እስከሚደርሱበት ጊዜ ድረስ ከአንድ ህገ-ወጥ አሸጋጋሪ ወደ ሌላ እየተሸጋገሩ ነው የሚሄዱት። ለጠለፋቸው ሰው መከፈል ያለበት ገንዘብ እስከ $50,000 ዶላር ድረስ ይሆናል። ያንን 50,000 ዶላሩን ከቤተሰቦቻቸው ለማግኘት ሲሉ ጠላፊዎቹ በስደተኞቹ ላይ ከፍተኛ በደል ይፈጽማሉ።ይደበድብዋቸዋል፣ ፕላስቲክ እያቀለጡ በአካላቸው ላይ ያፈሳሉ፣ እጃቸውናእግርቸው በእግረ-ሙቅ ታሰሮ ረዥም ጉዞ ኦይሄዳሉ። ሲጃራ ይተርኩሱባቸዋል፣ በሴቶች ብልት ላይም ይተረኩሳሉ። በሴቶች ላይ የወሲብ ጥቃት ይፈጽማሉ። ያልተፈለገ እርግዝናና መውለድ ይከተላል። ለመክፈል ካልቻሉም አይኖቻቸውን፣ ኩላሊቶቻቸውን ወይም ሌላ ዋጋ የሚያስገኝ አካላቸውን እያወጡ ይሸጣሉ። በዚህ መልክ ገድለው ይጥልዋቸዋል ወይም ይቀብሯቸዋል።






































































POSTED BY DAWIT DEMELASH

No comments:

Post a Comment