በዘንድሮዉ ምርጫ ወያኔ የረጂም ግዜ አጃቢዎቹም ሊከዱት አንደሚችሉ በመነገር ላይ ነዉ ተባለ
እነዚህ ህዝባዊ ድጋፍና ተቀባይነት የሌላቸዉ ፓርቲዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዕጩዎችን ማቅረብ የግድ በሆነበት በዚህ የአካባቢ ምርጫ የአገሪቱን ሀብት እንደራሱ ንብረት ከሚቆጣጠረዉ ወያኔ ጋር መወዳደር ቀርቶ ለምርጫዉ ከሚያስፈልጋቸዉ የዕጩዎች ቁጥር ዉስጥ ከመቶ አምስቱን እንኳን ማቅረብ አለመቻላቸዉ ታዉቋል። ፓርቲዎቹም ይህንን በሚገባ ስለሚረዱ ምርጫ ቦርድ የገንዘብ እርዳታ
እንዲያደርግላቸዉ ለገዢዉ ፓርቲ ለኢህአዴግ አቤቱታ ቢያቀርቡም ኢህኣዴግ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ጥያቄያቸዉን ሳይሰማ ቀርቷል።
በዚህ የተነሳ አንዳንዶቹ ፓርቲዎች በምርጫዉ ተሳትፈናል ለማለት ብቻ አንዳንድ ቦታ ላይ በጣት የሚቆጠሩ ዕጩዎች ቢያቅርቡም በከፍተኛ የገንዘብ ችግር የተነሳ በምርጫዉ ለመሳተፍ የሚችሉ ባለመሆናቸው የዘንድሮዉን ምርጫ የሚያዘጋጀዉ፤ የሚወዳደረዉና ከራሱ ጋር ተወዳድሮ የሚያሸንፈዉም ወያኔ ብቻ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ይንቀሳቀሳሉ ከሚባሉት ከ65 በላይ ፓርቲዎች ውስጥ ሃያ ስምንቱ ከምርጫ በፊት ውይይት ይቅደም ብለዉ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ እራሳቸዉን ከምርጫው ማግለላቸው የሚታወቅ ሲሆን ዉሸት የማይሰለቸዉና በኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የተሞላው ምርጫ ቦርድ ግን 15 ፓርቲዎች በተወዳዳሪነት ተመዘግብዋል እያለ ህዝብን በማጣለል ላይ መሆን ታዉቋል።
Posted By.Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment