Thursday, August 22, 2013

ድብደባ የተፈፀመባቸው ከ 16 የሚበልጡ የአንድነት አመራርና አባል ህክምና ላይ ይገኛሉ ግን ለምን ?

ትናንትናው እለት ሁለት የአንድነት ፓርቲ የእስቀሳ ቡድን አባላት ፍቼ ከተማውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተተፈፀመባቸው መግለጻችን ይታወሳል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ሶስት ከተሞች “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ለቅስቀሳ ወደ ፍቼ ካቀኑት የፓርቲው አመራሮችና አባላት መካከል ትላንት ነሃሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ በከተማው የፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ሃይለየሱስ በየነ በሚመሩ ሲቪል ለባሾች ከፍተኛ ድብደባና ዝርፊያ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ድባደባውን የፈፀሙት ከ16 የሚበልጡ ግለሰቦች ሲሆኑ የተደበደቡት ሁለት የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የሆነው አቶ ነብዩ ባዘዘው እና አቶ መሳይ ተኬ ዛሬ ጠዋት የህክምና እርዳታ አግኝተዋል፡፡ የደረሰባቸውን ጉዳት የተመለከቱት ዶክተሮች የተሸለ ህክምና እንዲያገኙ ሪፈር ፅፈውላቸዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ በፍቼ የተፈፀመውን መንግስታዊ ውንብድና አውግዞ የተጠናከረ ቡድን ልኳል፡፡

No comments:

Post a Comment