Tuesday, August 13, 2013

ታላቅ ሃገራዊ መልዕክት ለሁሉም በማዳረስ ሃሰትን ለማንገስ የሚደረገውን ሩጫ ያጋልጡ !!!

ታላቅ ሃገራዊ መልዕክት ለክርስቲያን ወገኖቻችን


እኛ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በሃገራችን ኢትዬጲያ ለረጅም ዘመናት ከክርስትና እምነት ተከታዬች እና ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር ተከባብረን እና ተደጋግፈን ስንኖር መቆየታችን ይታወሳል፡፡

ይህም የመቻቻል እና የመደጋገፍ ባህላችን ዛሬም መልኩን ሳይቀይር አለምን በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ሆኖም ይህንን ተቻችሎ እና ተከባብሮ በሰላም የመኖር ባህላችንን ለማደፍረስ የኢህአዴግ መንግስት በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ በመግባት ከሊባኖስ አህባሽ የተሰኘ ከእስልምና አስተምህሮ ያፈነገጠ ባዕድ እምነት በማስመጣት በሙስሊም ወገኖቻችሁ ላይ በግዳጅ እምነታችንን ለማስቀየር እየሞከረ ይገኛል።
እኛ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በሃገራችን ኢትዬጲያ ለረጅም ዘመናት ከክርስትና እምነት ተከታዬች እና ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር ተከባብረን እና ተደጋግፈን ስንኖር መቆየታችን ይታወሳል፡፡
For Ethiopian muslims and chrstians
እኛም ሙስሊሞች መንግስት በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ አትግባብን ከጥንት ጀምሮ በሃገራችን የነበረውን አስልምና መንግስት ባስመጣው አህባሽ በተሰኘ አዲስ ሃይማኖት አንቀይርም በማለታችን አክራሪዎች፣አሸባሪዎች ናችሁ በማለት በመንግስት እየተደበደብን እየተገደልን እና እየታሰርን እንገኛለን፡፡
መንግስት በሃማኖታችን ላይ ጣልቃ አይግባብን በማለት በሰላማዊ መንገድ መቃወም ከጀመርን ድፍን ሁለት አመት ሊሞላን ጥቂት ጊዜያት ብቻ ይቀሩታል፡፡ በሁለት አመት የሰላማዊ ትግላችን ሂደት ውስጥ ከጅማሮ አንስቶ አስካሁን ድረስ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ለመንግስት አቅርበን ምላሽ እስኪሰጠን እየጠበቅን ብንገኝም መንግስት እንደመንግስት በሚሊዬን የሚቆጠረውን የሃገሪቷን ሙስሊሞች ድምፅ ከመስማት ይልቅ ጥያቄዎቻችንን በማድበስበስ እና ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የጠየቅናቸውን 3 ቀላል ጥያቄዎችንን በማጣመም በሃሰት ፐሮፖጋንዳ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፤


ለግንዛቤ ይረዳችሁ ዘንድ ሦስቱ መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን የሚከተሉት ነበሩ
1ኛ:- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራሮች በህዝብ ያልተመረጡ በመሆናቸው በመስጂድ ውስጥ በሚደረግ ምርጫ በህዝብ በሚመጡ አመራሮች ይተኩ።
2ኛ:- አወሊያ ብቸኛው የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም በመሆኑ ከህዝብ በሚመረጥ ቦርድ ይተዳደር።
3ኛ:- በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ በአስገዳጅነት እየተካሔደ ያለው የአህባሽ እምነት ጠመቃ ይቁም፣ እንደማንኛውም እምነት ግን በራሱ ተቋማት እምነቱን የመስበክ እና የማስፋፋት መብት አለው። መንግስት ከላይ ለተጠየቁት ጥያቄዎች አስፈላጊውን ትብብር ያድርግልንየሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ|፡፡
እንግዲህ ከላይ እንዳነበባችሁት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸው እጅግ በጣም ቀላል ጥያቄዎች ከላይ ያስቀመጥናቸውን ይመስላሉ።ዛሬ ግን መንግስት እነዚህን ተራ እና ቀላል ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ የስልጣን ቆይታን ለማራዘም ሙስሊሞችን እና ክርስቲያኖችን ለማጫረስ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት እንመስርት እያሉ ነው በማለት መርዙን እየረጨ ይገኛል፡፡
ከላይ እንዳነበባችሁት ሶስቱን ጥያቄዎቻችንን ለመንግስት እንዲያደርሱልን ከመላው ሃገሪቱ በፊርማ ተደግፎ የመረጥናቸውን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እስር ቤት በማስገባት በኢትዬጲያ መንግስት የተለመደችዋን አሸባሪ የሚለውን ክስ በመለጠፍ ወደ ወህኒ ወርውሮብናል፡፡
ይህም ሳይበቃ ከቀናት በፊት የረመዳን ፆም ፍቺ በኢድ አልፈጥር በአላችን ላይም ጸሎታችንን አድርሰን በመመለስ ላይ በነበርንበት ወቅት ከላይ የጠቀስናቸውን ሶስቱን ቀላል ጥያቄዎች እና ወደ ወህኒ በመንግስት በሃሰት ተወንጅለው የተወረወሩብንን ኮሚቴዎቻችንን እንዲፈቱል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የሃገራችንን ሰንደቅ አላማ በመያዝ ጥያቄዎቻችንን አቅርበን በሰላም ወደየቤታችን በአላችንን ለማክበር በመመለስ ላይ በነበርንበት ወቅት የመንግስት ወታደሮች መንገድ በመዝጋት ሴት ወንድ ህፃን አረጋዊያን ሳይሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ደበደቡን፡፡ በድብደባውም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ወገናችሁ ጉዳት ደረሰበት፡፡ነፍሰጡር ሴትን ጨመሮ ሌሎች 5 ሙስሊሞች ፖሊስ በፈጸመው አረመኒያዊ ድብደባ ሂወታቸውን አጥተዋል፡፤በሺዎች |የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ወደ አስር ቤት ተግዘዋል፡፡
ይህም ኢሰብአዊ ድብደባ በአዲስ አበባ፣በደሴ ፣በወልቂጤ እና በአዳማ በሚኖሩ ሙስሊም ወገኖቻችሁ ላይ ተፍፅሟል፡፤ ይህንን እውነታ ከጎረቤታችሁ፣ከስራ ባልደረባችሁ ከሆኑ ሙስሊሞች ማረጋገጥ ትችላላችሁ፡፡
መንግስት ግን በውሸት በሚያሰራጭበት ጣቢያው ጥቂት አክራሪዎች ኢስላማዊ መንግስት ካልተመሰረት በማለት ሁከት ቀስቅሰው በቁጥጥር ስር አውያቸዋለው በማለት በደስታችን በኢድ በአላችን ቀን የፈፀመብንን ኢ ሰብአዊ ድርጊት በመካድ የህፃናት እና የሴት እህቶቻችንን እንዲሁም የአሮጊት እናቶቻችንን እና ሽማግሌ አባቶቻችንን እንባ፣ለቅሶ እና ደም የጥቂቶች ሲል አሾፈብን፡፤
በኢድ በአላችን ቀን መንግስት የፈፀመብን አሰቃቂ ድብደባ መሸከም ያልቻሉ እናቶች ህፃናት፣ሴቶች እና አባቶች ተክለ ሃይሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን በመግባት ሂወታቸውን በማትረፍ ቤተክርስቲያኗ ለታሪክ የማይረሳ አጋርነቷን አሳይታለች፡፤ድብደባው በሚፈፀምበት በነበረው በሁሉም የአዲስ አበባ አቅጣጫዎች የሚገኙ ክርስቲያኖች ቤታቸውን በመክፈት የተጎዱትን ሙስሊሞች እንክብካቤ በማድረግ እና ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ለረጅም አመታት በአንድነት እና በፍቅር የመኖር ተምሳሌትነታቸውን እና አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፤
ውድ ወገኖቻችን ሆይ እኛ ኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላለፉት ሁለት አመታት በሰላማዊ መንገድ የጠየቅነው ፍፁም ሃይማኖታዊ ጥያቄ እንጂ መንግስት ከናነተ ጋር እኛን ለማጋጨት እንዳሰበው የሸሪአ መንግስት ይመስረትልን በሚል አይደለም፡፡
እኛ ሙስሊሞች አይደለም የሸሪአ መንግስት ይታወጅልን ብለን ልንጠይቅ ይቅርና በኢትዬጲያ የሚገኙ መስጂዶችን እንኳን ሙስሊሙ ያስተዳርራቸው፣የሙስሊሙ መሪ ተቋም የሆነው መጅሊስ ህዝብ በመስጂድ ውስጥ በሚመርጣቸው የሃይማኖት አባቶች ይተኩልን ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ ምላሽ ተነፍጎን እተደበደብን እየተገደልን እና እየታሰርን እንገኛለን፡፤
በመሆኑም ሁሉም የኢትዬጲያ ህዝብ መንግስት ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅሙ ሲል ሙስሊሙን ከክርስቲያን ወገኑጋር ለማጋጨት በተለያዩ ሚዲያዎቹ አክራሪዎች፣ጥቂቶች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱባችሁ ነው በማለት በሚያደርገው ሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳ እንዳትሸወዱ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
በኢ.ቲ.ቪ የሚቀርቡት ጥምጣም የጠመጠሙ ሙስሊም መሳዬች በሙሉ የአዲሱ አህበሽ እምነት ተከታዬች ሲሆኑ በተጨማሪም የመንግስት ካድሬዎች እና በገንዘብ የተሸነገሉ ግለሰቦች በመሆናቸው ሙስሊሙን እንደማይወክሉ በዚህ አጋጣሚ እንገልፅላቹሃለን፡፡
በመንግስት እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አጠገባችሁ የሚገኙትን ሙስሊሞች በመጠየቅ ተጨማሪ እውነታዎችን መረዳት የምትችሉ መሆኑን እንገልፅላቹሃለን፡፡
ሰላም፣ ፍቅር እና ብልፅግና ለኢትዬጲያ ይሁን!!!
ይህን መልዕክት ላልደረሳቸው በማዳረስ የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ!!!!
  Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment