የሐገሬ ጉዳይ ያገባኛል፤ ይመለከተኛል ብላችሁ በሲቪክ፤ በፖለቲካ፤ በብሄር፤ በህብረ ብሄር የተደራጃችሁና እንዲሁም በግላችሁም የምትንቀሳቀሱ ታዋቂ ግልሰቦች በሙሉ፡ እሳት በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ድርጅቶችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ለፊት ለፊት ውይይት እ. አ. አቆጣጠር ኦገስት 17 2013 በቨርጂኒያ ሸራተን ሆቴል ጥሪ ማድረጉን በአለም ዙሪያ ተበትነን የምንገኝ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ ታዳሚዎችና አስተዳዳሪዎች ጥሪውን በታላቅ ስሜት የምንደግፍና እሳት ሚዲያ ይህንን መድረክ በማዘጋጀቱ ያለንን ከፍተኛ አድናቆት እንገልጻለን።
ኢትዮጵያ ሃገራችን በታሪኳ በህዝብ የተመረጠ መሪ ሳይኖራት ነገስታትና አምባ ገነኖች ሲፈራረቁባት ኖራለች፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንኑ በደነደነ ትከሻው ሲሸከም ኖሯል።
ባለፉት 22 አመታት ሃገራችንን የገጠማት አገዛዝ ግን በአለም ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ የሰየመ፤ ለተቀረው ህዝብ ታላቅ ጥላቻና ንቀት ያለው ቡድን ህዝቡን በማሰቃየት ላይ ይገኛል። የመብት ጥያቄ የሚያነሱትን፤ የግፍ አገዛዙን የሚቃወሙትን የተለያየ ስያሜ እየሰጠ ከማሰር፤ ሰቆቃ ከመፈጸምም በላይ ዘር እስከ ማጥፋት የሚደርስ ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል።
ዝርዝሩ ከናንተ የተሰወረ በይሆንም ለዋቤ ያህል፡ የወያኔ ስርዓት
1. በተፈጥሮ ሃብታችን እኛም ተጋሪ እንሁን ያሉትን የአኝዋክ ተወላጆች ፈጅቷል፡ ከሞት የተረፉትን ከቤታቸው፤ ከንብረታቸው፤ ከተወለዱበት መንደር አፈናቅሎ የአውሬ ሲሳይ አርጓቸዋል። መሬታቸውን ለባእዳን ሸጦታል፡ ስንቶቹ ሃገር ጥለው እንደተሰደዱ ስንቶቹ በህይውት እንደተረፉ እንኳ በውል አይታወቅም
2. በትረ ስልጣን ከመያዙም በፊት ሆነ ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ በመነሳት በጎንደርና በሰሜን ወሎ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አፈናቅሎና ገሎ መሬታቸውን ቀምቶ የትግራይ ታጣቂዎችን አስፈሮበታል፡ ያም አልበቃ ብሎ ዘር እንዳይተካ የማምከኛ መርፌ እየወጋ የአማራን ዘር በማጥፋት ላይ ይገኛል፡
3. የሶማሌ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ከአለም እይታ ጋርዶ ፈጅቷቸዋል አየፈጀም ነው፡ በመሆኑም ምን ያህሉ በህይወት እንዳሉ ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።
4. የኦሮሚፋ ተናጋሪ ህዝባችንን የተለያየ ስም እየሰጠ በየአደባባዩ አየፈጃቸው፤ እና በገፍ እስር ቤት እያጎራቸው ነው፡ የኦሮሞ ህዝብ ብዛት ያለው በመሆኑ ሊጨርሳቸው አልቻልም እንጂ የወያኔ እቅድ ለመጨረስ ነበር። ከዚህ እኩይ ተግባሩ፡ ይታቀባል ተብሎ አይጠበቅም።
5. አማርኛና ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን አጋጭቶ እንዲተላለቁ ታላቅ ሴራ ቢያሴርም በሁለቱ ህዝቦች በሳልነት ያቀደውን ያህል እንዲሳካ እድል አልሰጡትም።
6. የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የሃይማኖት መሪዎቻችንን ራሳችን እንምረጥ፤ መንግስት ራሱ ያወጣውን ህገ መንግስት ጥሶ በእምነታችን ጣልቃ አይግባ በማለት ላለፉት 18 ወራት ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲያቀርቡ ቢቆዩም ጋጠ ወጡ የወያኔ ቡድን ግን አኔ የመረጥኩላችሁን ሃይማኖትም ሆነ የሃይማኖት መሪዎች ተቀበሉ በሚል መጠነ ሰፊ ጥቃት እየሰነዘረባቸው ነው። ይህም ሳያንሰው ከክርስትና እምነት ተከታይ ወገነኖቻቸው ጋር ለማቃቃርና ለማፋጀት ከፍተኛ በጀት መድቦ ፍፁም ሃላፊነት የጎደለው ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛል።
የወያኔ ወንጀል ለቀናት ቢዘረዘር አያልቅም፡ ለተነሳንበት መልዕክት ግን በቂ ነው ብለን እናምናለን፡
ወያኔ ይህን ሁሉ ወንጀል ሲፈጽም በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፈናል፡ ሰብአዊ መብት በዛች ሃገር እንዲከበር እንታገላለን፤ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን እንፈልጋለን ከሚሉ ድርጅቶች ግን ሚዛን የደፋ እንቅስቃሴ ሲደረግ አልታየም። ለምን ለሚለው ጥያቄ አንድ መቶ አንድ ምክንያቶች ሊሰጡ ይችላሉ። ግን እነዚህ የሚሰጡት ምክንያቶች ወያኔ ህዝቡ ላይ ከሚያደርሰው ግፍ የበለጡ ነበሩን? ናቸውን? ይህንን ለያንዳንዳችሁ ህሊና እንተወዋለን።
ሀ) የጋምቤላ እልቂት ብቻ በቂ መነሻ በሆነ ነበር፡ http://www.youtube.com/watch?v=BMAbsbAWyks&feature=player_embedded#at=14
ለ) ኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ሰቆቃ ብቻ ልዩነትን ፈቶ በጋራ ለመታገል በቂ በሆነ ነበርhttp://www.youtube.com/watch?v=UeR3AmFOzOc
ሐ) በእንደዚህ አይነት ደስታና ተስፋ የተጀመረው የ1997 ምርጫ https://www.youtube.com/watch?v=VMgdDe3ACtI ይህን በመሰለ አሰቃቂና አስደንጋጭ ሁኔታhttps://www.youtube.com/watch?v=oIOHPaqC6OI መጠናቀቁ ምንም አይነት የግል ፍላጎትና አላማን ወደጎን ሊያሰተውና ሊያስተባብር በተገባ ነበር፡
መ) በቅርቡ ለ3 አመት ያለምንም ፍርድ ታስረው ለመፈታት ፊርማ በማሰባሰባቸው ብቻ ቂሊንጦ
http://www.youtube.com/watch?v=Rq8ml5h8TwY ተወስደው የተደበደቡትና ለሞት የተዳረጉት የኦሮሞ ወገኖቻችን የሰቆቃ ጥሪ ብቻ ሊያናድደንና በቃ ሊያስብለን በተገባ ነበር
http://www.youtube.com/watch?v=Rq8ml5h8TwY ተወስደው የተደበደቡትና ለሞት የተዳረጉት የኦሮሞ ወገኖቻችን የሰቆቃ ጥሪ ብቻ ሊያናድደንና በቃ ሊያስብለን በተገባ ነበር
ሰ) ሰሞኑን በእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጅምላ ጭፍጨፋhttp://ecadforum.com/ethiopianvideo/2013/08/08/ethiopian-muslims-protest-august-07-2013/ ብቻ ወደ አንድ ሊያመጣ ይገባ ነበር፡
ረ) በወያኔ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተጠቂ መሆናቸውን እንኳ በውል ያላወቁ ልጅ ወልዶ ራሳቸውን ለመተካት በየጸበሉ የሚነከራተቱ ወገኖች እንባ http://www.youtube.com/watch?v=0tJ0VmilVmQ ብቻ በአንድ ጎራ ሊያሰልፈን ይገባ ነበር፡
ይህ ሁሉ አልፏል፤ ካለፈው መማር እንጂ መማረር የትም አያደርስምና ከዚህ በሗላ ግን ያለፈው ስህተት እንዳይደገም ብርቱ ጥንቃቄ እንዲደረግ አደራችን የጠበቀ ነው።
የሐገሬ ጉዳይ፤ የወገኔ ጉዳይ ያገባኛል፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የእንሰሳ መብት በሚከበርበት ወቅት ባንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ ሰቆቃ መፈጸም የለበትም፤ ከትግራይ የተውጣጡ የወንጀለኛ ቡድኖች ባሪያ ሆነን መኖር አንችልም አይገባንምም ብላችሁ በተናጠልም ይሁን በቡድን በማህበረ ሰብ (ሲቪክ)ም ይሁን በፖለቲካ፤ በብሄርም ይሁን በህብረ ብሄር ድርጅት ስም የምትንቀሳቀሱ ሁሉ በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝታችሁ ሃሳባችሁን በግልጽ ተነጋግራችሁ፤ ጊዜያዊ መፍትሄ (short term solution) ዘላቂ የመፍትሄ ሃሳብ (Roadmap) መክራችሁና ዘክራችሁ አገርን ከመፍረስ ህዝብን ከጥፋት ትታደጉት ዘንድ የዜግነት ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ (ECADF)
Posted By,Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment