Saturday, November 30, 2013

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ

30 November, 2013
በአወዛጋቢው የ1997 ዓ.ም ምርጫ የታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት አና ጐሜዝን ጨምሮ “ለአፍሪካ ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክና የአውሮፓ ህብረት” የጋራ ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ሰሞኑን ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር  ተወያዩ፡፡ፓርቲያቸውን ወክለው በውይይቱ እንደተካፈሉ የተናገሩት የኢዴፓ ማዕከላሚ ኮሚቴ አባል አቶ ልደቱ አያሌው፤ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት የኢትዮጵያ  የዲሞክራሲና የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ምን አዲስ ነገር አለ? የወደፊቱ አቅጣጫ ምን ይሆናል? በማለት ጥያቄ እንደሰነዘሩ ገልፀዋል፡፡ የፓለቲካ ምህዳሩ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊጠናከሩ የሚችሉበት እድል ከጊዜ ወደ ጊዜ መጥበቡን ተናግሬያለሁ የሚሉት አቶ ልደቱ፣ የሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሂደት እንደሚያሳስበንና የአውሮፓ ህብረት እርዳታ የፓለቲካ መጠቀሚያ እንዳይሆን ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለባቸው አስረድቻለሁ ብለዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ለአገራችን እርዳታ መስጠቱን እንደማንቃወም፣ የእኛን ችግር እነሱ እንዲፈቱ እንደማንጠብቅ ገልፀንላቸዋል ያሉት አቶ ልደቱ፤  ከዲሞክራሲያዊና ከሰብዓዊ መብት አያያዝ አኳያ ማድረግ የሚገባችሁን ወደኋላ ትታችኋል፤ እርዳታ ሰጪ እንደመሆናችሁ ማድረግ ያለባችሁን ነገር ዘንግታችኋል የሚል አስተያየትሰጥቻለሁ ብለዋል፡፡ 

የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አስራት ጣሴ በበኩላቸው፣ የፓለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን፣ የሠላማዊ ትግል ተስፋ መዳፈኑንና ህገ መንግስቱ እየተከበረ አለመሆኑን እንዳስረዱ ጠቅሰው፤ በነፃው ፕሬስ ህግ፣ ተሻሽሎ በወጣው የፓርቲ  ህግ፣ በፀረ ሽብርተኛ አዋጁ ዙሪያ እንደተወያዩበት ተናግረዋል። በ2002 ዓ.ም. ምርጫ በዝርፊያና በንጥቂያ ኢህአዴግ 99.6 በመቶ ድምፅ አግኝቶ ማለፉን በመጥቀስ፤ 2007ዓ.ም. የሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ አጣብቂኝ እንደሆነብን ለአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት አስረድቻለሁ ብለዋል - አቶ አስራት፡ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህዝቡን ሰብስበን ማነጋገር፣ ሠላማዊ ሰልፍ  ማድርግ እንዳልቻልንም፣ የመንግስትን ጫና በማሳየት ገለፃ አድርጌያለሁ በማለት አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት አባላት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም ጋር ቀደም ብለው ውይይት ማድረጋቸውን የተናገሩት አና ጎሜዝ፣ አገሪቱ በኢኮኖሚ ማደጓለ እንደሚገልፅና ልማቱ ግን  ህዝቡን ከድህነት ያላወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በ2007 ዓ.ም. ለሚደረገው አገራዊ ምርጫም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አና ጐሜዝ ገልፀው፤ ታዛቢዎችን ከመላክ በተጨማሪ በየሁኔታው እና በየወቅቱ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በውይይቱ ላይ ተካፋይ እንደነበሩ ታውቋል፡፡

Posted By.Dawit Demelash

Thursday, November 28, 2013

የዕለቱ ዜና ዘገባ ( ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ ) 27.11.2013


ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ http://www.finote.org/Finot27_11_2013.mp3

    Posted By.Dawit Demelash


የወያኔ በዲሞክራሲ ቁማር እስከመቼ?

በአሸናፊ ንጋቱ
በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት የዛሬ 22 ዓመት አንግቦት የነበረውን የዲሞክራሲ መፈክር በማየት ዲሞክራሲ የጠማው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ጮቤ በመርገጥ ነበር የተቀበለው፡፡ ነገር ግን ይህ መፈክር ድራማ መሆኑ እየዋል እያደረ ነበር እየተጋለጠ የመጣው። ጮቤ እየረገጠ፤ ትግሉን ተቀላቅሎ መስዋት የከፈለውን ህዝብ የቁልቁል ወደ ባሰ የመከራ ማጥ ከቶታል።

ወያኔ እራሱ ህግ አውጥቶ እራሱ የማፍረስና በህጉ ያለመገዛት አባዜ የተጠናዎተው አንባገነን ስርአት መሆኑ በሃያ ሁለት አመታት የስልጣን ጉዞው አስመስክሯል፡፡ በትክክል እንደ ህገ-መንግስቱ ቢሆን ኖሮ ህገ-መንግስት የህጎች ሁለ የበላይ ህግ ነው፡፡ነግር ግን ወያኔ ያለምንም ከልካይ እንዳሻው ያለ ህዝብ ተሳትፎ ለስልጣናቸው እርዝማኔ ይመች ዘንድ ሲዘርዙትና ሲደልዙት ይስተዋላል፡፡ ሲፈልግ ስልጣን መብት ሲሰጥህ/ሽ ሳይፈልግ ደግሞ ሲከለክልህ/ሽ በስመ ዲሞክራሲ እየነገደ የሚኖር የማፍያ ስርአት ነው፡፡ የአምባገነን መንግስታት መለዬ በሆነው ሃይልን እየተጠቀመ በመግደል፤ በእስር፣ በመሳርያ እና በዱላ እያስጨነቀ የህዝቡን ስነ ልቦና በማድከም የስልጣን ቆይታውን ማርዘምም የስርአቱ ዋና አላማ፡፡ እንዲህ አይነቱ አምባገነንና በዲሞክራሲ ስም ህዝባችን ላይ ቁማር የሚጫዎት ስርአት ለኢትዮጵያውያችን አያስፈልግም፡፡ ስለዚህ ይህንን በጨካኝኔ የተሞላ ስርአት ከሃገራችንና ከህዝባችን ጫንቃ የምናስወግድበት ሰአት አሁንና አሁን ብቻ ነው።
በዲሞክራሲ ቸነፈር መመታታችን ሳያንሰን አገር አልባ ለመሆን በተቃረብንበት እና ማንነታችን ጥያቄ ውስጥ በገባበት በዚህ ጊዜ ዲሞክራሲን መናፈቃችን ብቻ ተፈጥሮአዊ አያደርገንም፡፡ በተፈጥሮ ያገኘነውን ነፃነት በተግባር ስናስጠብቅ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሁሌ ፍዳና መከራ የሆነው በሃገራችን ላይ በጣም ገኖ ከእኔ በላይ ላሳር በማለት በሃይል በጉልበት በስልጣን ላይ በተቀመጠው የወያኔ ስርአት ነው፡፡ የወያኔ ስርአት ስልጣን ከያዘ ቀን ቀንን እየተካ፤ ሳምንት ሳምንታትን እየተካ፤ ወር ወራትን እየተካ፤ አመት አመታትን እየተካ ይኸው እነሆ 22 አመታችንን አስቆጠርን፡፡ በዚህ 22 ዓመት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ለዲሞክራሲ፤ ፍትና ነፃነት የዘመሩ ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው የድራማው ሰለባ ሆነዋል፡፡ አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም፡፡ አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤ ጐለምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆዳደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል ይበቃል ልንለው የግድ ነው፡፡
በዲሞክራሲ እጦት ሃገራችንን ማስጨነቁ አልበቃው ያለው ይህ ክፉ ስርአት በአሁኑ ጊዜ የህዝባችንን ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎት ይገኛል፡፡ ህዝባችን በኑሮ ውጣ ውረድ ህይወቱ ሰላም አጥቷል። ወያኔ ስርአቱን የሚቃወሙትን ብሎም የዲሞክራሲ ጥያቄን ያነሱ ንፁሃን ዜጐችን መግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት መለዬው ነው። ወያኔ ይህን ስትራቴጂ የሚጠቀመው ለሃገራቸው መልካም የሚመኙትን እና ለሃገር ይሰራሉ ተብለው የሚገመቱትን ሃገር ወዳድ ዜጐች ማጥፋት ከመፈለጉ የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ሁሌም ለሃገራቸው ደህንነት ለህዝባቸው ኑሮ የሚጨነቁ ስለሆኑ ስርአቱን የመደገፍ ፍላጎት ስለማይኖራቸውና እየፈፀመ ያለውን አረመኔ ተግባር ለህዝብ ሊያጋልጡብኝ ይችላሉ ብሎ ስለሚፈራም ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ የሚቀጠለው እንዴት ነው? ውድ ኢትጵያውያን በአሁኑ ጊዜ ህዝባችን ስቃይ ላይ ነው፡፡ ልንደርስለትና ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ነፃነታችን ማፋጠን ይገባናል፡፡
በስተመጨረሻም መጠየቅ የምፈልገው በዲሞክራሲ እየነገደ ያለው ይህ የወያኔ ስርአት በሃገራችን ገነባሁት፤ እያበበም ነው የሚለው የዲሞክራሲ ስርአት የቱ ይሆን?
በየትኛው ዲሞክራሲ፡ ነፃነትና ፍትህ ያለበት ሃገር ላይ ነው አንድ መንግስት ለ22 አመታት ሲገዛ ያየነው? ዲሞክራሲ፡ ነፃነት እና ፍትህ አሰፍናለሁ ብሎ ቃል የገባላትን እናት ሃገር ዛሬ ግን ድንበሯን በመሸራረፍ እየሸጧት፣ እየለወጧት ብሎም ህዝባችንን በኑሮ እሳት ረመጥ እያቃጠሉት፤ ነፃነቱ ቀርቶ የሃገራችንን ህዝቧን እየከፋፈሉ የብሄር ብሄረሰብ መብትን አስከብራለሁ እያሉ እርስ በእርስ ህዝቡን ማጋጨትና ማጨፋጨፉ ይሆን የሃገራችን ዲሞክራሲ መገለጫው?
ነው ወይስ ዲሞክራሲ ለወያኔ ህዝቡን መከፋፈል፣ እንደልብ እንዳይናገር ማፈን፣ መሬትን ያለባለቤቱ ፈቃድ እየነጠቁ መሸጥ፣ ሙስናን ተዋጋሁ እያሉ በሙስና ተጨማልቆ መገኘት፡፡ ይሄ ነው የወያኔ ዲሞክራሲና እና ፍትህ? የቆሰለችውን ኢትዮጵያ አድንሻለሁ ብሎ ለባሰ ህመም መዳረግስ ለምን!? እውነት ግን በተቃራኒው በቁስሉ ላይ እየሸነቆሩ ማድማት ነበር እንዴ አላማቸው? የተራባችሁትን ሰላም እና ዲሞክራሲ እሰጣችኋለሁ ብሎ ቃል የገቡለትን ህዝብ እልል ብሎ ሲቀበል፣ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው የመከራ ጦስ መክተት ነበር እንዴ የወያኔ አላማ!? ስራቸውና ተንኮላቸው የገባው/ት ለምን ብሎ ሲጠይቅ/ ስትጠይቅ ወደ ወህኒ እና ወደ ሞት መጣል መሆን አለበት እንዴ የዚያ የምስኪን ህዝብ ለሰራው ውለታ መልሱ? ታዲያ የወያኔ ዲሞክራሲያዊ ግዛት ይኼ ነው?
ዛሬ ህዝባችን የተወለደበትን ምድርና ቀየ በሃይል በማስለቀቅ መሬቱን በኢንቨስትመንት ስም እየተሸነሸነ እየተሸጠ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ታዲያ ይሄ ጭቁን ህዝብ ምድሩን ለቆ ወዴት ይሂድ የትስ ይድረስ? ነው ወይስ ስርአቱ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ነው ቆርጦ የተነሳው? ወገኔ ሆይ ሃገር አለን ብለን የምንኮራው መቼ ይሆን? እስኪ መልሱልኝ፤ የቀን ከሌት ጥያቄየና በራሴ መልስም ለማግኘት ባለመቻሌ አንድ ብትሉኝና ለአምሮየና ለመንፈሰይ ሰላምን ባገኝ ነው ለዘመናት የሚመላለስብኝን ጥያቄዎች መሰንዘሬ፡፡ በእኔ በኩል ይህንን አፋኝና አምባገነን ስርአት ያለምንም ልዩነት በአንድ ልብ በቃ ልንለውና፤ በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል ባይ ነኝ።
ድል ለጭቁኑ ኢትዮጵያ ህዝብ!!!

   Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, November 27, 2013

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሲጮኹ ዋሉ፤ ዲኑ ተማሪዎቹን “በዩኒቨርሲቲው በቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁ” አሉ

የዩኒቨርሲቲው ዲን / ባየልኝ ዳምጤበቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁአሉ

(
-ሐበሻ) በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት ተማሪ የሆኑ ተማሪዎች ከውጤት አሰጣጥ ጋር ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ሲጮኹ መዋላቸውን የዘ-ሐበሻ የባህርዳር ዘጋቢዎች ከስፍራው ዘግበዋል። እንደ ዘጋቢዎቻችን ገለጻ 3 ዓመት ተማሪዎቹ ጩኸታቸውን ሲያሰሙ ከዋሉ በኋላ የዩኒቨሲቲው ዲን / ባየልኝ ዳምጤ ሰብስበው ያነጋግሯቸው ቢሆንም፤ / ችግሩን ከማብረድ ይልቅ እሳት ለኩሰውበት ሄደዋል ሲሉ ተማሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ነግረውታል።

ዩኒቨርሲቲው አዲስ ባወጣው መመሪያ መሠረት በተማሪዎች ማርክ አሰጣጥ ላይ ከዚህ ቀደም 85 የነበረው ወደ 95 ያድጋል ባለው መሠረት ተማሪዎቹ ልክ እንደ 1 እና 2 ዓመት ተማሪዎች ማርክ ሊያዝልን ይገባል በሚል የዛሬው የባህርዳር ዩኒቨሲቱ ሁከት መፈጠሩን የገለጹት ዘጋቢዎቻችን፤ ይህን ተከትሎም በሃገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ፖለቲካ የሚመለከቱ መፈክሮችን ተማሪዎቹ ሲያሰሙና ሲጮኹ ከዋሉ በኋላ / ባየልኝ ዳምጠው ጠርተው አንጋግረዋቸዋል። ተማሪው / ባየልኝ ወደ ጠሩት ስብሰባ ሲገባ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰማ ሲጮህ ነበር ያሉት ዘጋቢዎቻችን ዲኑ ስብሰባውን ሲመሩ የነበረው እንደተማረ ሰው አልነበረም የሚሉ አስተያየቶች 3 ዓመት ተማሪዎቹ ተሰምቷል።
/ ባየልኝ ተማሪውን ሰብስበውበቤታችሁ በነበራችሁበት ጊዜ በቀን 2 ጊዜ የምትበሉ ተማሪዎች እዚህ ዩኒቨሲቲ ውስጥ በቀን 3 ጊዜ እየበላችሁ ጠገባችሁ፤ ይሄ ጥጋብ ነው ስለማርክ አሰጣጥ ጥያቄ ያስነሳችሁየሚል አንባገነናዊ ንግግር በመናገራቸው ተማሪው ቁጣውን እንዳሰማ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎችእኛ በችግረኛ ሃገር ላይ ሆነንና የትምህርት ጥራት በሌለበት መልኩ ያደጉ ሃገራት የትምህርት ፖሊሲ መሞከሪያ አንሆንምበሚል 3 ዓመት ተማሪዎቹ ቁጣቸውን ገልጸዋል ብለዋል። ይህን ተከትሎም ጉዳዩ እኛንም ይመለከተናል በሚል የባርዳር ዩኒቨርሲቲ 1 እና 2 ዓመት ተማሪዎች 3 ዓመት ተማሪዎቹን ጥያቄ መቀላቀላቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

-ሐበሻ ወደ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ዲን ቢሮ ደውላ የነበረ ቢሆንም / ባየልኝ ዳምጤን ማግኘት አልቻለችም። በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

  Posted By,Dawit Demelash

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10019