Monday, November 18, 2013

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ማስወገድ !!


ኢትዮጵያውያን
የወያኔ ባናዳዎች ባፈሙዝ ሀይል ስልጣን ላይ ከወጡበት እለት አንስቶ በርካቶች ለስደት፤ለእስራት፤ለሞት እና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡የሰሃራን በረሃ አቋርጠው ለማለፍ ሲሞክሩ የበረሃ እራት ሁነዋል፡፡ሌሎች ደግሞ ኩላሊታቸው ሳይቀር እየተዘረፉ ለከፋ አካላዊ እና አእምፘዊ ጉዳት ተዳርገዋል፡፡በባህር ሲያቋርጡ የተሳፈሩበት ጀልባ በሞገድ እየተመታ በብዙ የሚቆጠሩት ለዓሳ እራት ሁነዋል፡፡በታንዛኒያ እና በኡጋንዳ ሲያልፉ በኮንቴነር ታፍነው የሞቱትን ቤት ያቁጠራቸው፡፡ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን የመን ውስጥ ተጠልፎ በውስጡ የነበሩት የአየር መንገዱ ሰራተኞች እና ተሳፋሪዎች ባሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፏል፡፡
ይህ ሁሉ ህይወት እንደቅጠል ሲረግፍ የወያኔ ባለስልጣኞች አንድም ቀን ብለው የተጎዱ ቤተሰቦችን አጽናንተው አሰከሬናቸው በክብር እንዲያርፍ አላደረጉም፡፡በሰው ሰራሽ አደጋ ለሞቱትም ጥፋተኞችን ለፍርድ ለመቅረብ ተንቀሳቅሰው አያውቁም፡፡ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድም ዳግም ስህተቶች እንዳይፈጸሙ ስምምነቶችን ተፈራርመው ያውቁም፡፡በየሀገራቱ የሰገሰጉዋቸው ዲፕሎማት ተብየዎችም ቤተሰባቸውን እንዴት አንደላቀው እንደሚያኖሩ ፤ከነማን ጋር የንግድ ሽርክና እንደሚፈራረሙ እንጂ በስደት ለሚንገላታው ዜጋቸው መብት ተከራክረው የሀገሪቱን ጥቅም ለማስጠቀም አንዳች ስራ ሰርተው አያውቁም፡፡
ዲፒሎማቶች ከሙያ ብቃት ጀምሮ ህዝባዊ ወገንተኝነትም ስለሚጎድላቸው የፓርቲውን ህልውና ለማስጠበቅ ካልሆነ በስተቀር ለህዝብ የሚጠቅም ስራ ይሰራሉ ብሎ መገመት ያዳግታል፡፡የወያኔ ዲፕሎማቶች በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ እንዲከፋፈሉ ከላይ በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ብዙ የመከፋፈል ስራዎችን ሲሰሩ እነደቆዩ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ዛሬ 40/60 የኮንደሚኒየም እና በዓባይ ግድብ ግንባታ ሰበብ በውጪ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ዶላር ለመሰብሰብ ደፋ ቀና የሚሉት ዲፕሎማቶች ለይስሙላ ያክል እንኳን አንድም ቃል መተንፈስ አልቻሉም፡፡
በወያኔዎች ዘንድ ብሔራዊ የሀዘን ቀን የሚታወጀው እና ህዝቡ በግዳጅ እየወጣ የመንግስት አገልግሎች መስጫ ድርጅቶች ሳይቀሩ ለሁለት ሳምንተ ያልክ ተዘግተው ስራቸው ሀዘን ብቻ እንዲሆን መመሪያ የሚተላለፈው የስልጣን እና የጥቅም አጋራቸው ሲሞት እንጂ ሌላው ተራ ዜጋ እማ ሞቱን እንኩዋን የሚዘግበለት የሀገሩ የመገኛኛ ብዙሀን የለውም፡፡ ግብር የሚከፍልበት ቴሌቭዥን እንዲህ ያሉ ዜናዎችን ለህዝቡ እንዳያቀርብ እነሽመልስ ከማል አፉን ጥርቅም አድርገው ይዘውታል፡፡የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሜዲያዎች የዘገቡትን እውነት በወያኔ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የሀገሪቱ ቴሌቭዥን የቁጥር ጨዋታ ያዟል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተብየው / ቴወድሮስ አድሀኖም ችግሩ ተጋኖ ቀረበ ነው ሲሉ ተዘባበተውብናል፡፡
ሀገሪቱን እመራለሁ ብሎ የተቀመጠ ሀይል እንዴት እንዲህ ሀገራዊ ውርደት ሊያከናነብ ቻለ? መልሱ ቀላል ነው፡፡ መጀመሪያም ወያኔዎች ከሆዳቸው ባለፈ ሀገር እና ህዝብ ብሎ ነገር አይገባቸውም፡፡አሰራ ሰባት ዓመት ተዋጋንለት የሚሉትም የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት እንጂ ለህዝብ የሚጠቅም አንዳች ሀገራዊ አጀንዳ ኑፘቸው አደለም፡፡የወያኔዎች ዋነኛ መገለጫቸው እና ግባቸው ሀገራዊ ውርደት ማሰፈን ነው፡፡ ይሕን ደግሞ ባለፉት አመታት ሁላችንም በደንብ የምናውቀው ነው፡፡ለግራዚያኔ ሀውልት ማቆምን የተቃወሙ ህዝቦችን አስረዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን በትነዋል፡፡የሀገሪቱን ቅርስ እና ታሪክ በማወደም ታረክ- አልቫ አድርገዋል፡፡የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም በተደጋጋሚ ለባእዳን አሳልፎው ሰጥተዋል፡፡አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ ለም መሬታችንን በርካሽ ዋጋ ሲቸበችቡት ቆይተዋል፡፡ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎው ሰጥተዋል፡፡በሰላም ማሰከበር ስም ወታደሮች በሶማሊያ መንገድ አስክሬናቸው እንዲበተን አድረገዋል፡፡ዜጎች እምነታቸውን በነፃነት እንዳያመልኩ አድርገዋል፡፡ሌላው እና መሰረታዊው ነገር ራሱ ወያኔ ዜጎችን አደህይቶ፤አደንቁሮ፤አዋርዶ መግዛት የአስተዳደር ስትራቴጅው ዋነኛ ማጠንጠኛው ነው፡፡
በሰሞኑ ያየነውም በአረብ ሀገራት የያኔን አንባገነን ስርዓት ሸሽተው የተሰደዱ ዜጎች በሳዉዲ ወሮበላ ፖሊሶች እንደ በግ ሲታረዱ ሰማያዊ ፓርቲ ሕዝቡን በማስተባበር ሐገራዊ ውርደት እንዲያቆም፤በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ ፤አሰገድዶ መድፈር እና እንግልት እንዲቆም በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ የወገን ተቆርቋሪ ዜጎችን በፌዴራል ፖሊስ ማስቀጥቀጥ፤የፓርቲውን አመራሮች ማሰር የወያኔ ብሄራዊ ውርደት ለፍተኛው ማሳያ ነው፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የሰራው መንግስት ሊሰራው የሚገባውን የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ነው፡፡
ምን እናድርግ?
የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ምንጭ ወያኔ ነው!ስለዚህ መፍትሄውም የችግሩን ምንጪ ከመሰረቱ ማድረቅ ነው፡፡ወያኔን ለማሰወገድ ደግሞ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ሀዘናችንን አቁመን በልበ ሙሉነት ለዚህ ሀገራዊ ውርደት የዳረገንን አንባገነናዊ ስርዓት ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ዛሬ በሳውዲ ማጎሪያ ክምፕ ያለኸውም ሀገርህ ብትገባም ሊያስኖርህ የሚችል መንግስት አደለም ሀገሪቱን የሚመራት፡፡ያው ከመውጣትክ በፊት የምታውቀው በአንድ ዘር የበላይነት የተገነባው አብዛኛው ጾም የሚያድርበት ተቂቶች በብዙሀኑ ደም የሚንደላቀቁበት ነው፡፡ገብተህ ድምጽህን የምታሰማበት ምንም መንገድ የለህም፡፡ምናልባትም የሚጠብቅህ ሰበብ ተፈልጎ ቃሊቲ መወርወር ሊሆንም ይችላል፡፡ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የነፃነት ታጋዮችን በመቀላቀል ነፃነታችንን፤የተዋረደው ክብራችንን ፤በአለም አደባባይ የጎደፈው ስማችንን በጋራ ማደስ ይኖርብናል፡፡እግዚያብሄር አምላክ የሞቱት እህት እና ወንዶሞቻችን ነፍስ በገነት ያሳርፍልን፡፡የጠላቶቻችንን ልብ ያራራልን፡፡

ሞት ረግጠው ለሚገዙን አንባገንን መሪዎች !ድል የነፃነትን ብርሀን ለመፈንጠቅ በየበረሀው ለምትንከራተቱ የቁርጥ ቀን ልጆች!

   Posted By.Dawit Demelash

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9610

No comments:

Post a Comment