Saturday, November 16, 2013

ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ ! ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታስረዋል

ethio saudi addis1


አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሺየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።
መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ አስፋዉ ሚካኤል፤ መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።
ethio saudi addis2ዘገባዉ አክሎም ፖሊስ አንዳንድ ጋዜጠኞች ያነሱትን ፎቶግራፍ መደምሰሱንም አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይን አስተያየት ማግኘት እንዳልተቻለም ተገልጿል። ለተለያየ ሥራ ሳዑድ አረቢያ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ እንዲያወጡ የተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ካለቀ ወዲህ እዚያ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት እየደረሰባቸዉ እንደሚገኝ እየገለፁ ነዉ።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር። ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሩ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ላይ የሚያደርሠዉን በደል፥ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ እያወገዙት ነዉ። ትናንት እዚህ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ፍራንክፈርት ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን፥ ማንገላታት፥ ማሠር፥ መደብደብ መግደሉን እንዲያቆም፥ የኢትዮጵያ መንግሥትም የዜጎቹን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዉ ነበር።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።
ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ። ሠልፈኞቹ ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት ገና ከመሠብሰባቸዉ ፖሊስ ደብድቦ አብዛኞቹን በተነ፥ የተቀሩትን አሠረ። ዮሐንስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።
ዩናይትድ ስቴትስ ርዕሠ-ከተማ ዋሽግተን-ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚወስደዉን እርምጃ በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ትናንት የተጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍና ዉግዘት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችም ይቀጥላል።ethio saudi addis
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎችን ከሐገሩ ማባረሩን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ እንደነገረን በኢትዮጵያዉያንና በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መካካል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ዛሬም ጋብ ብሏል።ከዚሕ ቀደም ኮንትራታቸዉ ተቋርጦ፥ ቀጣሪዎቻቸዉ ጠፍተዉ፥ ወይም ታመዉ ጂዳ ኢትዮጵያ ቆንስላ ዉስጥ ለወራት ተጠልለዉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ማቆያ ጣቢያ ገብተዋል። ነብዩን ከአንድ ሠዓት በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። የመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ምን አዲስ ነገር — የሚል ነበር። (ምንጭ፡ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ – ለአሰራር በሚያመች መልኩ ርዕሱን ቀይረነዋል)
ከዚህ በታች የሚገኙትን አስፈንጣሪዎች በመጫን ዝርዝሩን ይመልከቱ
በሌላ በኩል ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ የሚከተለውን ብሏል፡፡
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን በድል እና ስቃይ ለመቃወም አዲስ አበባ በተጠራው ሠላማዊ ሠልፍ የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሶች አሰቃቂ ድብደባና እሰር መፈፀማቸው ቀደም ተብሎ መገለፁ የሚታወቅ ነው፡፡
ቀደም ብሎ ስማቸው የተዘረዘሩት እስረኞች በአሁኑ ሰዓት ሁለት ቦታ የተከፈሉ ሲሆን ከዚህ በታች ያሉት ፒያሳ ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ሲሆን
1ኛ. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀ/መ
2ኛ. አቶ ስለሺ ፈይሳ የፓርቲው ም/ት ሊቀ/መ
3ኛ. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አላፊ
4ኛ. አቶ ዮናታን ተስፋዬ የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ አላፊ
5ኛ. ወጣት አቤል ኤፍሬም አባል
6ኛ. ሰለሞን ወዳጄ አባል
7ኛ እመቤት ግርማ አባል
8ኛ. ዳዊት ፀጋዬ ደራሲና ጻሃፊ (በግል)
9ኛ. እየሩስ ተስፋ አባል
የተቀሩት እዛው መስቀል ፍላወር አካባቢየሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ
1ኛ. አቶ ወረታው ዋሴ የፓርቲው የፋይናስ ጉዳይ አላፊ
2ኛ. አቶ ጌታነህ ባልቻ የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ አላፊ
3ኛ. አቶ አብታሙ ደመቀ የብሔራዊ ም/ቤት አባል
4ኛ. አቶ ዮናስ ከድር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
5ኛ. ዮሴፍ ተሻገር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
6ኛ. ፋሲካ ቦንገር አባል
7ኛ. መርከብ ሀይሌ አባል
8ኛ. አስራት አብርሃም ደራሲና ጻአፊ (በግል)
9ኛ. ንግስት ወንድይፍራው አባል

  Posted By. Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment