ህዳር 3 ቀን 2006 ዓ.ም.
ወደ ታሪክ መለስ ብለን ኢትዮጵያ ለሳውዲ አረብያ ይህን አደረገች ረዳች ማለቱ ጉንጭ አልፋ ንግግር ከሆነ ጊዘ አልፏል--
የዘንድሮዎቹ ኋላ ቀር፣ ዘረኛና በራሳቸው ስብስቴ ዘመን ተቀርቅረው ያሉ ጨቋኝ ገዢዎች በኢትዮጵያውያን ላይ በሰሞኑም እየፈጸሙ
ያሉት ኢሰብዓዊ ግፍና ግድያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥብቅ የሚያስወግዛቸው መሆኑ ግልጽ ሆኗል፤ በንዴትና ብስጭትም ወገኖቻችን
ሲሰቃዩና መከራ ሲቀበሉ ማየትም ተገደናል። ኦሕአፓ ይህን ግፈኛ የሳውዲ አገዛዝ እያወገዘ ዜጎች ሁሉ የሚያደርጉትንና እያደረጉ
ያሉትንም ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ደግፎ ይህ ተቃውሞ ሁሉን ዜጋ ያቀፈ እንዲሆንም ጥሪ ያደርጋል።
የዚህን መራራና አሳዛኝ ክስተት መንስዔ የምንስተው አይደለም። ዜጎቻችንን ያውም በለጋ ዕድሜ ለስደትና ለዘመናዊ ባርነት የሸጠውና
እየሸጠ ያለው ወያኔ ነው። ይህን ድርጊት ደግሞ የሳውዲ ጥቅም አስጠባቂ ሆኖ ኢትዮጵያን የሚበዘብዘው ግማሽ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባዩ
ቱጃርም የሚጠየቅበት ነው። የሳውዲ ገዢዎች “አባሯቸው” ሲል የተስማማው የወያኔ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አድህኖም መሆኑንም
እየገለጹ ናቸው። ኢትዮጵያውያን በደልና ስቃይ በሚደርስባቸው ሁሉ ወያኔ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ለመሆኑ ዜጎችን ምስክር ጥሩ
የሚላቸው የለም። ወጣት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት ተሸጠው ሲሰቃዩና ሲገደሉ ወይም በቀቢጸ ተስፋና እርዳታ እጦት ራሳቸውን
እንዲገድሉ ሲደረጉ ወያኔ ያደረገላችው ምንም የለም። ሌሎች የእስያ ሀገሮች ወደ ዘረኛዋ ሳውዲ ሠራተኛ አንልክም በማለት ውሳኔ
ሲያስተላልፉ ወያኔ ተሽቀዳድሞ በዓመት 45ሺ ለመላክ መስማማቱንም በይፋ አሳውቆ እንደነበር የምናስታውሰው ነው። በሳውዲም
ሆነ በካታር፣ ሌባኖን፣ …ወዘተ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ ዘረኝነትና ጭፍን ብዝበዛ ደርሶባቸዋል፤ እየደረሰባቸውም ነው። ሙስሊም
ኢትዮጵያውያንም የግፉ ተቀባይ መሆናቸው ግልጽ ቢሆንም አያሌ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን በመሆናቸውና ለመጸለይ
በመሰብሰባቸው ብቻ ወደ እስር ተወርውረው ተደብደበዋል፤ ተደፍረዋል፤ አሁንም ታግተው አሉ። የሳውዲ ገዢዎችና ጭፍሮቻቸው
ድርጊት ለሙስሊሞች ሁሉ ቅዱስ ቦታዎች የተባሉትን ሜካና መዲና ጠባቂ ነን በማለት እንወስደዋለን ከሚሉት ሃላፊነትና
ከሃይማኖታቸውም ጋር የሚጣጣም አይደለም። የሳውዲ ኋላ ቀር ገዢዎች ከዚህ ቀደምም በርካታ ኢትዮጵያውያንን ገድለዋል፤
ቢያንስ አንዲት ዜጋችንን በአደባባይ ሰቅለዋል፤ ብዙዎችን ገርፈዋል። ሳውዲ አረብያ በአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ (በማሊ፣
ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ቱኒዝያ፣ ባሕሬይን፣ ግብጽ፣ ኢራቅ፣ …ወዘተ) በጸረ-ዴሞክራሲ ጸረ-ሕዝብ ድርጊት ላይ የተሰማራች ናት።
በኢትዮጵያ የምታደርገውም ጣልቃ ገብነት ምስጢር አይደለም። የምዕራቦቹ ታማኝ ወዳጅና ባለሀብት በመሆኗም የሳውዲ ገዢዎች
ለአፍሪካ ያላቸው ንቀትና ዘረኝነት መረን ከለቀቀ ውሎ አድሯል ።
ሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሁሉ መኮንንና ማውገዝ ቀነ ቀጠሮ የማይሰጠው ግዳጅ ነው።
የሳውዲ ወዳጅ የሆኑት ምዕራባውያንም የሚፈጸመውን ግፍ እንዲያወግዙ ጥሪ ያስፈልጋችዋል--አውቀው የተኙ ቢሆኑም። ከዚህ
በተያያዘ ደግሞ ሰልፍና ተቃውሞው ጸረ ሕዝቡን ወያኔንም በዋና ተጠያቂነት የሚያጋልጥና የሚያወግዝ መሆን አለበት።
የሳውዲ አረብያ ጸረ ኢትዮጵያ ወንጀል የሚቀጣ ይሆናል!
ሳውዲ አረብያ ያሰረቻቸውን ሁሉ በአስቸኳይ ትልቀቅ፤ የግፍ እርምጃዋንም ታቁም፤ ገዳዮቹንም ለፍርድ ታቅርብ !
የወያኔ አገዛዝ ይውደም !!
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Posted By.Dawit Demelash
http://eprp.com/press_releases/Press-Release-November-12-2013.pdf
No comments:
Post a Comment