በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ3ኛ ዓመት የዲግሪ ተማሪ የሆነው ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በፅንፈኛው ወያኔ አባላት በጩቤ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ሟች ወጣቱ ያነሳቸው የነበሩ ጥያቄወች በስፋት መነሳት ጀምረዋል ሲል አወጋን ለዘ-ሐበሽ በላከው መረጃ አስታወቀ።
“ሟች አንተነህ ዘረኛው የወያኔ ወራሪ ቡድን በንፁሃን አማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ዉስጥ አየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ያለፍርሃት ይቃወም የነበረ ሲሆን ደካማው የወያኔ ቡድን የለመደውን ደም ማፍሰስ ተግባሩን ፈፅሞበታል” ያለው አወጋን “ወጣቱ የተገደለው በጩቤ ተወግቶ ሲሆን እሬሳው ከዳሽን ብራ ፋብሪካ በስተጀርባ ተጥሎ ተገኝቷል” ሲል ዘግቧል።“የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ እሄን አስከፊ የሆነ የጠባቦች ድርጊት አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን ወነጀለኞችን በተገኙበት ለመቅጣት ያለ እረፍት ይሰራል ወጣቱ ከዚህ መማር ያለበት ነገር ቢኖር የወንድማቺን የአንተነህ እጣ ሳይደርሰው ወያኔን ለማስወገድ የምናደርገውን ትግል በመቀላቀል የወገኖቻችን የስቃይ አመታት እናሳጥር በማለት መልክቱን ያስተላልፋል” ያለው አወጋን “ለሟች ቤተሰቦች መጥናናቱን ይስጥ” ሲል ሐዘኑን ገልጧል።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አሁንም ውጥረቱ እንዳየለ ነው ቢባልም የመንግስት ሚድያዎች አንዳችም መረጃ አልሰጡን።
Posted By.Dawit Demelash
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9859
No comments:
Post a Comment