Sunday, November 10, 2013

በሳዉዲ በወገኖቻችን ለይ እየደረሰ ያለዉን ሰቆቃ

መስፍን ሃዕለማርያም
ለጉዳዬ መነሻ የሆነኝ (facebook)የዉስጥ መስመሬ ከሳዉዲ አንዲት እህት የፃፈችልኝ አሳዛኙን በወገኖቻችን ለይ እየደረሰ ያለዉን ሰቆቃ የሚመለከት ነዉ፡፡
BY:Mesfin Habtemariam (11.11.2013)

ለጉዳዬ መነሻ የሆነኝ (facebook) የዉስጥ መስመሬ  ከሳዉዲ አንዲት እህት የፃፈችልኝ አሳዛኙን  በወገኖቻችን ለይ እየደረሰ  ያለዉን ሰቆቃ ሊረዳቸዉ የሚችል አካል ካለ  የበኩሌን እንዳደርግር የሚማፀን  መልክት ነዉ፡፡
የመልክቱ ይዘት አንዲህ ይነበባል፡በፖሊሶች  የሚደርስባቸዉ እንግልት፤ድብደባ እና ግድያ በተጨማሪ ተፈጥሮም እየተፈታተናቸዉ አንደሆነ ትናገራለች፡፡ እስር ቤት ዉስጥ ሰዉ በሰዉ ለይ ተደራርቦ ሞልቶ  አሰፓልት ላይ ብርድ እና ፀሀይ አያሰቀያቸዉ ነዉ ትላለች፡፡  በተለይ ሴቶች እህቶቻችን ያሉበት ሁኔታ  በጣም አንደሚያሳዝን እና ሊደርስላቸዉ የሚችል  ወገን  እንደሚፈልጉ መልእክት እንዳስተላልፍ ወይም የበኩሌን እንዳደርግ የሚጠይቅ ነዉ፡፡ ግን ምን ማድረግ እችላለሁ፤ ማድረግ ብችል ጥሩ ነበር፤ ዉስጤ በሀዘን እያነባ እህህ እንጂ ልደርስላቸዉ አልቻለኩም፡፡ አዝናለሁ ማድረግ የምችለዉ መረጃዉን ለሚችሉ ማስተላለፍ ብቻ፡፡
ዘም ብዬ በዚህ ጉዳይ ሰብከነከን የሀገራት የዲፐሎማሲ ግኑኝነቶች  (Diplomatic  Relations) ማለት ምት ማለት ነዉ አልኩ፡፡ ምክንያቱም ይህ ወዳጅነት ሀገራት እርስ በርስ በመከባበር በፖለቲካ፤በኢኮኖሚ፤በባህል እና በመሳሰሉት ለሀገራቸዉ ለወገኖቻቸዉ  በሚጠቅም መንገድ በጋራ በትብብር ሊሰሩ ወዳጅነት ይመሰርታሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒዉ አሁን የኢትዮጲያ ዜጎች ላይ እየተፈፀመ እንዳለዉ አይነት  ወንጀል ሲፈፀም የክብርና የሉአላዊነት ጉዳይ ስለሆነ መንግስታት ለሀገራቸዉም ለወገኖቻቸዉ ክብር ሲሉ ቅሬታ ያሰማሉ ወይም በአለም አቀፍ የህግ  አግባብ  እርምጃ ይወስዳሉ፡፡
ለነገሩ ኢትዮጲያ  ክብሯን የሚያስጠብቅላት መንግሰት ሲኖራት አይደል ዜጎች መብታቸዉ ሚጠበቀዉ፡፡ አበዉ ሲተርቱባለቤቱ ያቃለለዉን አሞሌ ጨዉ….አንዳሉት ወያኔ በአለም ፊት  ሰዉ የመሆን ክብራችንን አዋርዶት ሌሎች በስደት ሄደነባቸዉ እንዴት ሊየከብሩን  ይችላሉ?
ህዝባችን እረኛ እንደሌለዉ መንጋ ተበትኖ፤ ተዋርዶና ክብሩን ጥሎ  መኖር ከጀመረ እነሆ 23 አመታትን  አስቆጠረ፡፡ ዜጎቻችን  በቄያቸዉ በሰላም ሰርተዉ እንዳይኖሩ በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ  ተማረዉ በስደት የበረሀ፤ የባህር ሲሳይ እየሆኑ ከዛም የተረፉት ይኸዉ አሁን እንደምናየዉ ለጨካኝ አዉሬዎች እንደሰዉ ተፈጥረዉ አንደአዉሬ የሚንቀሳቀሱ ሰዉ በላ የአረብ ፖሊሶች እንግልት እና ሞት ተዳርገዋል፡፡

ዛሬ ዉሸት በማይታክተዉ ኢትዮጲያ ቴሌቪዥን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ቀርበዉ ስለ አረብ ሀገር ስደተኞች ተጠይቀዉ ሲመልሱ፤ በሳዉዲ ሀገር ያለዉን አምባሳደር አስጠርተዉ ስለጉዳዩ ሊጠይቁ እደሆነ ተናግረዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነዉ መጠየቃቸዉ ባያስከፋም ወገኖቻችን አሁን የሚያስፈልጋቸዉ አፋጣኝ ነፍስ የማዳን ምላሽ ነዉ፡፡ አሁን የሚያሰፈልገዉ በየትኛዉም መንገድ እንደ መንግስት ዜጎቻችን  ከእስር፤ ከድብደባ እና  ከግድያ  አንዲያመልጡ የሳዉዲን መንግስት ማስቆም ነዉ፡፡
ባለቤቱን ካልደፈሩ አጥሩን አይነቀንቁምአለ የሀገሬ ሰዉ፡ ሀላፊንት የሚሰማቸዉ ቢሆን  ወያኔዋች ዜጎች በየሀገሩ  በሄዱበት ሁሉ ሲዋረዱ የእነሱም ዉርደት አንደሆነ የገባቸዉ አይመስልም ወይም ጆሮ ዳባ ብለዋል፡፡ ለንገሩ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር Dr. ቴዎድሮስ አድሃኖም  ሳዉዲን በጎበኙበት ወቅት ከሳዉዲ ባለ ስልጣናት ጋር ህገወጥ የሚባሉትን ስደተኞች እንዲያሶጡና በምትኩ 40000 ህጋዊ ዜጎችን አንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ እንደ ያዙ ባለስልጣናቱ ይናገራሉ›› ይህ በጣም ሀላፊነት የጎደለዉ ጊዜዉ ሲደርስ ከተጠያቂነት ማምለጥ አንደማይቻል ሊያዉቁት ይገባል፡፡
በሰለጠነ ዘመን ወደሗላ እንደ ጋርዮሽ የጨለማ ዘመን ሰዉ በሚመስሉ  በሰዉ በላ አዉሬዎች በወገኖቻችን ላይ በአረብ ሀገር መንግስታት የሚደርሰዉን እንግልት የአለም አይን እና ጆሮ እንዲያይ እና እንዲሰማዉ የምንችል ሁሉ የበኩላችንን እናድርግ ጥሪዬ ነዉ፡፡

  Posted By,Dawit Demelash

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9220

No comments:

Post a Comment