Wednesday, December 25, 2013

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተባረሩ

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው፦ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲና የጤና ነክ ተማሪዎች ለውዝግብ የተዳረጉት በሚሰጠው ድግሪ ሲያሜ እንደሆነ ከቦታው የደረሰን ማስረጃ ያስረዳል፡፡ 1 እስከ 4ተኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች ሲመደቡ ዲግሪያቸው የጤና ሳይንስ መኮንን (Public Health Officer) እንደሚባል እንደተነገራቸው ገልፀው ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው አሁን የህብረተሰብ ጤና (Public Health) ብቻ የሚል ስያሜ እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጉዳዩን በማሳወቅ ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን “‹የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅየሚለው እናንተን አይመጥንምእንደተባሉ ገልጸዋል፡፡
በመልሱ ያልረኩት የዲፓርትመንቱ ተማሪዎች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከህዳር 28 ጀምሮ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው የዩኒቨርስቲው ኃላፊዎችና ለፕሬዚደንቱ ጥያቄ ቢያቀርቡምብትማሩ ተማሩ ባትማሩ ግቢውን ለቃችሁ ትወጣላችሁየሚል ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረባቸው አሳውቀዋል፡፡ ታህሣስ 05 ቀን 2006 . የተሰበሰበው የዩኒቨርስቲው ሴኔት 173 ተማሪዎች ከግቢ እንዲባረሩ ወስኗል፡፡

ከሰኞ ታህሣስ 7 ቀን 2006 . ጀምሮ መታወቂያቸውን በፖሊስ ተቀምተው ከግቢው እንዲባረሩ የተደረጉት 173 ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት ሜዳ ላይ ተበትነው እንደሚገኙና ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጡ በምሬት ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን ለማረጋገጥ የጤና ዲፓርትመንት ኃላፊ ወደ ሆኑት አቶ ዱቤ ጃራ ስልክ ደውለን የተባለው ነገር መከሰቱን ጠቅሰው ነገር ግንውሳኔው በአግባቡ ነው የተላለፈው፤ ይህ ስያሜ 1954 . ጀምሮ የነበረ ነው፤ ካሪኩለሙ ላይ ያለው የህብረተሰብ ጤና (Public Health) እንጂ የህብረተሰብ ጤና መኮንን (Public Health Officer) አይደለምብለዋል፡፡
አቶ ዱቤ በተደጋጋሚ የዲግሪው ስያሜአዲስ የተሰጠ ስያሜ አይደለምካሉ በኋላ በተጨማሪምተማሪዎቹ ያለ ትምህርት 11 ቀናት ግቢ ውስጥ መቀመጣቸው ተገቢ ስላልሆነ ከግቢ እንዲወጡ ተደርጓልብለዋል፡፡ በተያያዘ ጉዳይ ከጊቢው የተባረሩ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈቀደ አንድ ተማሪመጠለያ፣ ልብስና ምግብእጅግ እንደቸገራቸው ገልፆ በተለይ ሴት ተማሪዎቹ መጠለያ እንዲሰጣቸው ለምስራቅ ጎጃም ዞን የሴቶች ጉዳይ ቢያመለክቱምዩኒቨርሲቲው ያባረራቸውን ብንረዳ እንጠየቃለን፤ ስለዚህ ልንረዳቸው አንችልም ማለታቸው ታውቋል፡

  https://www.zehabesha.com/amharic/archives/11219




No comments:

Post a Comment