የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 20 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<...አገራችን እንግባ ብለን እጃችንን ሰጠን ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ አለን እስር ቤት አስገብተው ገና አሰሪና ስፖንሰር የሚባሉት ተጠይቀው ነው የምትሄዱት ይሉናል...ወገኖቻችን ይድረሱልን..>> በሳውዲ አገር አትገቡም የተባሉ ኢትዮጵአውያን እየደረሰባቸው ስላለው ለሕብር ሬዲዮ ከተናገሩት(ሙሉውን ያዳምጡ)
<... የኦሮሞ ምሁራን የሚደልቁት ከበሮ በሻዕቢያና ወያኔ የተቀነባበረ አማራና ኦሮሞን ለማጋጨት የተወጠነ ልቦለድ ነው...ጡት፣ መቁረጥ ብልት መስለብ የአማራ ሳይሆን የኦሮሞ ባህል ነበር። ለማጋጨት ማሰቡ ለማንም አይጠቅምም ። ወደፊት መመልከት አለባቸው አማራው ልናገር ካለ ብዙ የተፈጸመበት ግፍ አለ...>
የሞረሽ ወገኔ ሊቀመንበር አቶ ተክሌ የሻው በአገር ቤትና በውጭ ምነሊክን ለማጥላላትና አማራን ለማጥቃት በሻዕቢያና በወያኔ እየተካሄደ አለ ያሉትን ሴራ በተመለከተ ከሰጡን ማብራሪያ (ቃለ መጠይቁን ያዳምጡት)
ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያን ጨምሮ ጎረቤቶቿ (ከነጻነት እሰከ ጎሳ ግጭት )(ልዩ ጥንቅር)
<<...የሳውዲ ጉዳይ ሊዘነጋ አይገባውም ። በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን በመጮሃቸው ነው ዛሬ መንፉሃ ላይ ከዚህ በፊት ያየነውን ግፍ ማየት ያልቻልነው ። ዛሬም በሳውዲ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ትኩረት መሰጠት አለበት...>>
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ለህብር ከገለጸው የተወሰደ
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
- የኦሮሞ ምሁራን በሻቢያና ወያኔ የፈጠራ ልብ ወለድ ዳግማዊ ምኒልክን ከማጥላላት ይልቅ ለወደፊቱ ቢያተኩሩ ለተረጋጋ አገር ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ
- ግብጻዊው ዲፕሎማት ኢትዮጵያ ግብጽን ምድረ በዳ ልታደርግ ነው ሲሉ ከሰሱ
- ከሳውዲ በፍላጎታችን እንውጣ ያሉ ኢትዮጵአውያን እስር ቤት ግቡ መባላቸውን ተቃወሙ
- በቴዲ አፍሮ ላይ የተጀመረው የማጥላላት ዘመቻ ከኦሮሞ ተወላጆች ጀርባ ሕወሃትና ደጋፊዎቹ መሰለፋቸውን የሚያሳይ ምልክት መታየት ጀመረ
- በቬጋስ ታክሲ ውስጥ የተረሳውን ሶስት መጦ ሺህ ዶላር የመለሰው አሽከርካሪ የ10 ሺህ ዶላር ጉርሻ አገኘ
- ኤርትራውያን በእስራኤል እርስ በእርስ ተደባደቡ
- ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስ ለተከታዮቻቸው መልክት አስተላለፉ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን
No comments:
Post a Comment